Get Mystery Box with random crypto!

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በማዕድን ዘርፍ ከ458 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ። የሕ | TIKVAH-MAGAZINE

በበጀት ዓመቱ ዘጠኝ ወራት በማዕድን ዘርፍ ከ458 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱ ተገለጸ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

ኢንጂነር ታከለ ዑማ ለምክር ቤቱ የተቋማቸውን የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡት ወቅት እንደገለጹት በተጠቀሰው ጊዜ ከማዕድን ዘርፍ ከ458 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፡፡

ከምክር ቤት አባላት የግንባታ ዕቃዎች ዕጥረት እና የዋጋ ንረትን በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄ “የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምንም እንኳን ተመሳሳይ ቴክኖሎጂ ቢኖራቸውም ማሽኖቹን የሚያንቀሳቅሱ እጆች ልዩነት ስላላቸው የማምረት አቅማቸው ይለያያል” ብለዋል።

በዚህም የተነሳ ለዘርፉ የሚሆን ክህሎት የያዘ ሙያተኛ ለማፍራት በሆለታ የ TVET ማዕከል እንደሚገነባ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

@tikvahethmagazine @tikvahmagbot