Get Mystery Box with random crypto!

በቦረና ከ165ሺህ ኪ.ግ በላይ የሚመዝን አደንዛዥ ዕጽ በቁጥጥር ስር ዋለ በኦሮሚያ ክልል ቦረና | TIKVAH-MAGAZINE

በቦረና ከ165ሺህ ኪ.ግ በላይ የሚመዝን አደንዛዥ ዕጽ በቁጥጥር ስር ዋለ

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የሚኦ ወረዳ ፖሊስ ከ165 ሺህ ኪ.ግ በላይ ካናቢስ የተሰኘ አደንዛዥ እጽ በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳዉ ፖሊስ የወንጀል መከላከል እና ፀጥታ ማስከበር ዲቪዥን ሃላፊ ዋና ሳጅን ሮባ ገልገሎ ተናግረዋል ፡፡

አደንዛዥ ዕፁ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው በኬንያ በኩል ለማስወጣት ከ አራት ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ገንዘብ ለገበያ ለማቅረብም አዘዋዋሪዎቹ ስምምነት ላይ ደርሰው እንደነበረም ተገልጿል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው አንድ መቶ ስልሳ አራት ሺህ በላይ የሚመዝነው ካናቢስ የተባለው አደንዛዥ እጽ በጸጥታ አካላት እንዲቃጠል መደረጉን ብስራት ሬድዮ ዘግቧል፡፡

@tikvahethmagazine