Get Mystery Box with random crypto!

ሕንድ የስንዴ ምርት ከሀገሯ ዉጪ እንዳይሸጥ እገዳ ጣለች። ሕንድ በሀገሯ የምግብ እጥረት እንዳይከ | TIKVAH-MAGAZINE

ሕንድ የስንዴ ምርት ከሀገሯ ዉጪ እንዳይሸጥ እገዳ ጣለች።

ሕንድ በሀገሯ የምግብ እጥረት እንዳይከሰት በሚል የስንዴ ምርት ከሀገሯ ዉጪ እንዳይሸጥ እገዳ ጥላለች። የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው የሕንድን ውሳኔ የኮነኑ ሲሆን ውሳኔው በዓለም የስንዴ ገበያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ሲሉ አክለዋል።

ሕንድ በስንዴ ሽያጭ ላይ እገዳ መጣሏ በተለይም በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የስንዴ አቅርቦት የተቋረጠባቸው የአፍሪካ እና እስያ ሀገራት ሕንድን እንደ አማራጭ ለመጠቀም አስበው ነበር።

የሕንድን ውሳኔ ከተቃወሙ የአውሮፓ ሀገራት መካከል ጀርመን አንዷ ስትሆን ድርጊቱ ዓለም ወደ ከፋ የምግብ ቀውስ እንደሚያመራ በግብርና ሚኒስትሯ በኩል አስታውቃለች። (AlAin)

@tikvahethmagazine