Get Mystery Box with random crypto!

በደንዲ ሀይቅ ላይ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጂ ሊገነባ ነው። የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆ | TIKVAH-MAGAZINE

በደንዲ ሀይቅ ላይ ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም ሎጂ ሊገነባ ነው።

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል በሆነው በደንዲ ሀይቅ ላይ ዘመናዊ ኢኮ-ቱሪዝም ሎጂ ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ። የወንጪና የደንዲ ሐይቅ የልማት ፕሮጀክቶችን የሚያገናኘው የመንገድ ግንባታም እየተከናወነ ነው።

የኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የጣልያኑ "ዊ ቢውልድ" ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ፔትሮ ሳሊኒ እና የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

የምዕራብ ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉታ በፕሮጀክቱ የደንዲ ሐይቅንና አካባቢውን የልማትና የቱሪዝም ማዕከል በማድረግ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት ይከናወናሉ ብለዋል።

የደንዲ ሐይቅ ልማት ፕሮጀክት ግንባታው የሚያከናውነው ሳሊኒ ኢምፕረጂሎ ኩባንያ ነው።

የወንጪ-ደንዲ ሐይቅ ኢኮ ቱሪዝም ልማት ፕሮጀክት በ"ገበታ ለሐገር" መርሐ ግብር ከሚከናወነው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ሲሆን የወንጪ ደንዲ የተቀናጀ ኢኮ ቱሪዝም ፕሮጀክት የግንባታ ስራው በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ መጀመሩ ይታወሳል። (EPA)

@tikvahethmagazine