Get Mystery Box with random crypto!

#Jimma በጅማ ዞን ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው በዘመናዊ ግብርና ሥራ ተሰማ | TIKVAH-MAGAZINE

#Jimma

በጅማ ዞን ከ2 ሺህ በላይ ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው በዘመናዊ ግብርና ሥራ ተሰማርተዋል። ለወጣቶቹ በ 111 ሚሊየን ብር የተገዙ 42 ትራክተሮች በረጅም ጊዜ በሚከፈል ብድር ተሰጥቷቸዋል ሲሉ የጅማ ዞን የሙያና የስራ እድል ፈጠራ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ካሳሁን አስታውቀዋል።

ባለፉት 9 ወራት በዞኑ በግብርና እና በሌሎች የሥራ መስኮች 98 ሺህ 500 ሥራ አጦችን ከ8 ሺህ በላይ በሆኑ ማህበራት በማደራጀት እና የ190 ሚሊየን ብር ብድርና የስራ ቦታ በማመቻቸት የስራ እድል መፍጠር ተችሏል ብለዋል፡፡ (FBC)

@tikvahethmagazine