Get Mystery Box with random crypto!

#ፌዴራል_ፖሊስ_ወንጀል_ምርመራ የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መ | TIKBAH-ETH

#ፌዴራል_ፖሊስ_ወንጀል_ምርመራ

የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ሙሊሳ አብዲሳ የሰጡት ማብራሪያ ፦

" ህግ ማስከበር ሲባል ብሄርን አይለይም፤ ሃይማኖትን አይለይም ፤ የፖለቲካ status አይለይም ፤ የሚዲያ አክቲቪስት ማንም ማንም ይሁን የSocial Status ፣ ሃይማኖቱ ምንም መሰረት አያደግም።

ህግ ለሁሉም እኩል ነው። እንደ ፖሊስ ሞያዊ ነፃነቱን ጠብቀን የምርመራ ስራ ጥቆማ ሲደርሰን በየትኛውም አካል ላይ ህግ የማስከበር ስራ እየተሰራ ነው የሚገኘው።

እንደሚታወቀው በአሁን ሰዓት ብዙ የሚዲያ ተከታይ ያላቸው ሰዎች ብሄርን ከብሄር የሚያጋጩ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጩ ፣ ጥርጣሬን የሚፈጥሩ የህዝቦቻችንን ፣ አጠቅላይ የኢትዮጵያን ህዝብ አብሮነት የሚፈታተኑ እነሱ ጥቅም የሚያገኙበትን በሚዲያ ዘመቻ የሚያደርጉትን በሽብር ድርጊት ውስጥ የተሳተፉትን ሰዎች በማስረጃ ላይ ሆነን መረጃ በመሰብሰብ በህግ ቁጥጥር ስር በማዋል ወደ ህግ እያቀረብን ነው።

ስለዚህ የሆነ ሚዲያ ወይ ጋዜጠኛ የሆነ ምንም ቢሆን እንደ defense ሊቀርብ አይችልም። በወንጀል ውስጥ የተሳተፈ መረጃ የተገኘበት ማንኘውም ሰው ላይ እርምጃ ይወሰዳል፤ በህግ ይጠየቃል፤ ግልፅ በሆነ ነፃ በሆነ ፍርድ ቤት አቅርበን ምርመራ ስራ እንሰራለን።

ስለዚህ በአሁን ሰዓት የሚዲያ ስራ ላይ የተሳተፉ ሰዎች እሱን እየተጠቀሙ አጠቃላይ stability እንዳይኖር የሆነ title እየሰጡ እንደ ገቢ ምንጭ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልተረዳው ነገር እነኚህ አክቲቪስት የተባሉ ታሰሩ የተባሉ ግለሰቦች እንደ ገቢ ምንጭ የሚጠቀሙት አይነት ነው ያለው።

በምርመራ እንዳገኘነው አንድ ግለሰብ ከ4 ዩትዩበሮች ጋር ውል አስሯል፣ ከአንዱ ዩትዩበር 25 ሺህ ብር ነው የሚከገለው በአንድ ጊዜ እስከ 100 ሺህ ነው የሚከፈለው፤ ይሄን ለማድረግ ተመልካች እንዲያገኝ ለማድረግ ብሄርን ከብሄር የሚያጋጭ፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጭ ፣ ወይም የመንግስትን ተቋም ፣ ወይም የመንግስትን ተሿሚዎች በሚያሸማቅቅ መልኩ ግልፅ በሆነ መልኩ characterize በማድረግ title እየሰጡ እንዲህ እያደረጉ ተመልካችን፣ like , share በብዛት እንዲያገኙ ብዙ ነገር በማድረግ ይሄን መሰረት በማድረግ destabilize በማድረግ የተለያዩ የወንጀል ድርጊቶችን፣ የሃሰት የውሸት ፕሮፖጋንዳዎችን በመልቀቅ ህዝቦች አብረው እንዳይኖሩ ሀገሪቱ በሰላም ተረጋግታ እንዳትኖር አጠቃላይ የማወክ ስራ እና ጥርጣሬ በሚፈጥር መልኩ ጥላቻን በውሸት ዘመቻ እያደረጉ ህዝቡ ላይ ይሄን እየጫኑ ለራሳቸውን የገቢ ምንጭ አድርገው ሀገሪቷን አደጋ ላይ ለመጣይ የሚሰሩ አካላት ናቸው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ይሄንን ደግሞ ፖሊስ ህግን መሰረት በማድረግ ፍርድ ቤት በማቅረብ የጊዜ ቀጠሮ በመጠየቅ በራሳቸው ፍላጎት በሚፈልጉት ጠበቃ ተወክለው በቤተሰቦቻቸው እየተጠየቁ ይሄን የምርመራ ስራ ፣ የህግ ማስከበር ስራ በደንብ እየተሰራ ነው።

ስለዚህ በአጠቃላይ ማንኛውም ሰው ከህግ በታች ነው።

ከህግ በታች እስከሆነ ድረስ ጥቆማ የቀረበበትን እንደፖሊስ ሙያን መሰረት አድርጎ የህግ የማስከበሩን ስራ ማንኛውም ሰው ላይ በየትኛውም ላይ ብዙ እሱን የሚከተል ሰው ሊኖር ይችላል ከዚህ በፊት እንደተደረገው ፣ የሃይማኖት ሰው ሊሆን ይችላል፣ ማንኛውም ሰው ሊሆን ይችላል ዋናው መሰረት የህግ ስህተት አለ ? ወይስ የለም ? የሚለው ነው። ስለዚህ እስካሁን ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ስም ብዙ ነገሮች ተችለዋል በአሁን ሰዓት ግን የለየለት የሽብር ስራ ፣ የሽብር ፈጠራ ፣ ሀገርን የማፍረስ ስራ ፣ ህግ የሌለ እስከማስመሰል ፣ የፍትህ ተቋማት እርምጃ መውሰድ አይችሉም የሚያስብል ደረጃ ላይ ደርሶ ሀገርን የማፍረስ ተልዕኮ ላይ እየሰሩ ያሉት አካላት ላይ የህግ የበላይነት ለማስከበር ከምን ጊዜውም በላይ የፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የፍትህ ተቋማት ጋር በመሆን የምርመራ ስራን እየሰራ ይገኛል። "

@tikvahethiopia