Get Mystery Box with random crypto!

#Update የ ' ፍትህ መጽሔት ' ማኔጂግ ዳሪክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ' የሀገር መከላከ | TIKBAH-ETH

#Update

የ " ፍትህ መጽሔት " ማኔጂግ ዳሪክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ " የሀገር መከላከያ ሰራዊትን በህዝብ ዘንድ አመኔታ ለማሳጣትና ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት ወንጀል " መጠርጠሩን መርማሪ ፖሊስ ዛሬ ለፍ/ቤት ገልጿል።

ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገን በተጠረጠረበት ሁከትና አመጽ ማስነሳት ወንጀል በምስክር ለማስመረጥና የምስክር ቃል ለመቀበል ተጨማሪ ማስረጃ ለመሰብሰብ እና የምርመራ ስራውን አጠናክሮ ለመቅረብ 14 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲሰጠው ችሎቱን ጠይቋል።

የጋዜጠኛ ተመስገን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ መከላከያን መተቸት እምነት ማሳጣት አለመሆኑን ጠቅሶ ተከራክሯል።

በምስክር ማስመረጥ ለተባለውም ቢሆን ተመስገን አገር የሚያውቀው በመሆኑ ማስመረጥ ጥያቄው ተገቢ እንዳልሆነ ገልጿል።

ጠበቃው አክሎም ጋዜጠኛ ተመስገን የሚሰራበት ሚዲያ ፍቃድ ያለው ህጋዊ ተቋም እንደመሆኑ ወንጀል ሰራ እንኳ ቢባል በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ እንጂ በጊዜ ቀጠሮ ሊጠየቅ እንደማይገባ ተከራክሯል።

ፖሊስ በዩቱዩብ ቃለመጠይቅ እያደረገ ከሌሎች አካላት ጋር ሁከትና አመጽ የማነሳሳት ስራ እየሰሩ ነው ሲል ባቀረበው የመነሻ ምርመራ ሪፖርትን በተመለከተ ጋዜጠኛ ተመስገን ከ4 አመት ወዲህ ምንም አይነት ከማንም ጋር ቃለመጠየቅ እንዳላደረገ ጠበቃ ሄኖክ አብራርቷል።

 በሚሰሩበት ሚዲያ የሀገር መከላከያ ተቋምም ቢሆን ተተችቻለው በህዝብ ዘንድ እምነት አጣሁ ብሎ አለመቅረቡን  ጠቅሰው ቢቀርብ በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ መሰረት በሚሰራበት ሚዲያ ማስተካከያ ከማድረግ እንደማይታለፍ መከራከሪያ ነጥቡ ጠቅሷል።

ያንብቡ
https://telegra.ph/Tarik-Adugna-05-27

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia