Get Mystery Box with random crypto!

As A Man Thinketh” -By James Allen ክፍል “የአስ | ሰው መሆን...

As A Man Thinketh” -By James Allen

ክፍል

“የአስተሳሰባችን ተጽዕኖ”
"Effect of Thought on Circumstances"

የሰው ልጅን አይምሮ ልክ እንደ እርሻ መውሰድ ይቻላል። በብልሃት የሚገራ ወይም ቸል ተብሎ የሚተው ለም መሬት። መሬቱን ተንከባከብነውም ሆነ ቸል አልነው፤ የሆነ ነገር ማብቀሉ አይቀርም። የማይጠቅም ዘር ከተበተነበት  የማይጠቅሙ ፍሬዎችን ያፈራል። የማይጠቅሙት ፍሬዎችም ሌላ ተመሳሳይ ዘር በመስጠት የማይጠቅም ትውልድ ይቀጥላሉ።

መልካም ገበሬ መሬቱን እንደሚንከባከብ፤ አረሞችን ተከታትሎ እንደሚነቅል፤ መልካሙን የሚጠቅመውን ዘር እንደሚዘራ ሁሉ፤ የሰው ልጅም አይምሮውን በትጋት መንከባከብ አለበት። ለአይምሮው መልካም ገበሬ በመሆን፤ የማይሆኑትን አስተሳሰቦች፤ የማይጠቅሙትን እምነቶች፤ ቀና ያለሆኑ አመለካከቶችን እያረመ መንቀል ይገባዋል። በምትኩ የጽድቅ ሃሳቦችን፤ ቅን አመለካከቶችን እየዘራ አይምሮው መልካም ፍሬን እንደሚያፈራ ለም መሬት ሊያደርገው ይችላል።ይህንን መንገድ ከተከተለ፤ አንድ ሰው ህይወቱ በራሱ ሃላፊነት ስር እንዳልች ይረዳል። በጥልቁ ሲያስተውልም፤ አስተሳሰቡ እንዴት ማንነቱን፤ ህይወቱን እጣፋንታውን እንደሚወስንበት ይመለከታል።

ባህሪ እና አስተሳስብ አንድ ናቸው። ባህሪ ወስጣዊ አስተሳሰብ በውጫዊ መልኩ ሲገለጽ ነው። በውጪ የሚታየው ገጽታችን እና አኳኋናችን በአብዛኛውን ጊዜ የውስጣችን ነጸብራቅ ነው። ይህ ማለት በማንኛውም ሰዓት ያለው የአንድ ሰው ሁኔታ ባጠቃላይ የባህሪው ነጸብራቅ ነው ማለት አይደለም። ነገር ግን ብዙዎቹ የህይወት አጋጣሚዎቹ፤ ድብቅ ከሆነው አስተሳሰቡ ጋር ትልቅ ቁርኝት አላቸው።

ሁሉም ሰው አሁን ያለበት ቦታ የደረሰው፤ ማንነቱ በሚመራበት ህግ ነው። ባህሪውን የገነባባቸው አስተሳሰቦቹ ናቸው አሁን ያለበት ቦታ ያደረሱት ወይም የመሩት። በአጋጣሚ ሳይሆን፤ ስህተት በሌለው የህይወት ህግ ። ይህ ከራሳቸው ጋር ተጣጥመው መኖር ላቃታቸውም ሆነ፤በራሳቸው ምሉዕ ለሆኑ ሰዎችም ጭምር እውነት ነው።

ሁሌም በለውጥ ወጀብ ከመመታት የማይተርፈው የሰው ልጅ፤ በህይወት ጉዞው እራሱን በመለወጥ ህልውናውን ማሳደግ እንደሚችል የሚረዳበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ከሚያጋጥሙት የህይወት አጋጣሚዎችም፤ ልምድ እየቀሰመ እና እየተማረ ከሄደም ፤ ሁኔታዎች ሁሉ እያለፉ ቦታቸውን ለሌላ የህይወት አጋጣሚ መልቀቃቸው የማይቀር መሆኑን ይረዳል።

ህይወቱ ከራሱ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ነገር እንደሚወሰን የሚያምን ሰው ግን፤ እራሱን ባልመረጣቸው አጋጣሚዎች እና ሁኔታዎች ውስጥ ማግኘቱ አይቀርም። ነገር ግን እራሱ የህይወቱ ፈጣሪ መሆኑን ሲረዳ እና በውስጡ ያለውን ሃይል ሲያውቅ፤ በነፍሱ ውስጥ የተቀበረውን ዘር ፍሬ እንዲያፈራለት ማድረግ ይቻለዋል፤ ያኔ ትክክለኛ የራሱ ጌታ ሆነ ማለት ነው። አንድ ሰው በዙሪያው ያሉ ነገሮች ሲለወጡ፤ በእርግጥም ለውጣቸው መሰረቱ ከራሱ አይምሮ ነው። ለምሳሌ መጥፎ ባህሪውን ለማከም የወሰነ ሰው ከወደቀበት አዘቅት ውስጥ ራሱን ጎትቶ ማውጣት ይችላል።

ነፍስ ወደራሷ እንደማግኔት የምትስባቸው ነገሮች፤ አንድ ሰው በውስጡ ካለው ድብቅ አስተሳስብ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችን ነው። በሰው አይምሮ ውስጥ የሚወድቅ እያንዳንዱ የአስተሳሰብ ዘር፤ ስሩን ሰዶ ህይወት መዝራቱ አይቀርም። እድሉን አመቻችቶም  በሁኔታዎች እና አጋጣሚዎች በኑሮዋችን ውስጥ ሲከሰት እናየዋለን። መልካም ሃሳቦች መልካሙን ፍሬ ይሰጡናል፤ መጥፎ ሃሳቦች መጥፎ ፍሬዎችን ይሰጡናል። የዘራውን እንደሚያጭድ ገበሬም፤ ሰው ከደስታው እና ከሃዘኑ የኑሮ ልምዱን ይቀስማል።

ይቀጥላል ......

@TIBEBnegni
@TIBEBnegni
@TIBEBnegni