Get Mystery Box with random crypto!

ነፃ ጥቅል ከኢትዮ ቴሌኮም ! - ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማ | የካሌብ ጽሑፎች

ነፃ ጥቅል ከኢትዮ ቴሌኮም !

- ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

- ይህም የእቅዱን 87.6 በመቶ ነው ብሏል።

- ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።

- ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።

በዚህም፦

- 1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

- 45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

- 100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

- የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል።

- (ማስታወሻ ፦ ዓለም አቀፍ የጥሪ ስጦታው የተበረከተው ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል፣ የጹሑፍና የኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ነው)

- ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።


══════❁✿❁ ═════════

ቻናሉን ለመቀላቀልና የተለያዩ ነገሮችን ለማግኘት

@TheHabesha0
@TheHabesha0