Get Mystery Box with random crypto!

#የሕይወት_ቤንዚን_ቀመርህን_ፈልግ! እውነተኛ ታሪክ የጀርመን ኦርጋኒክ ኬሚስት ፍሬድሪክ ቮን ስ | The Motivator

#የሕይወት_ቤንዚን_ቀመርህን_ፈልግ!

እውነተኛ ታሪክ

የጀርመን ኦርጋኒክ ኬሚስት ፍሬድሪክ ቮን ስትራዶኒትዝ የቤንዚን ቀመር ውስጥ የሚገኙትን ስድስት ካርበኖች እና ስድስት አቶሞች ለማስተካከል ለብዙ ዓመታት በትጋት ቢጥርም ጉዳዩን ለመፍታት የሚያስችል ትክክለኛ መዋቅር ማግኘት አልቻለም።

በድካም እና በመሰልቸት ጥያቄውን ወደ ድብቁ አእምሮው አዞረ። ብዙም ሳይቆይ የገዛ ጅራቱን ነክሶ እንደ ፒን ዊል የዞረ እባብ በድንገት ወደ አእምሮዉ ብልጭ አለለት።

ይህ ከስውር አእምሮው የተሰጠው መልስ ለረጅም ጊዜ ሲፈለግው የነበረውን የአተሞች 'ቤንዚን ሪንግ' ተብሎ የሚጠራውን መፍትሄ ሰጠው።

#በአጭሩ- የምትፈልገው ነገር ምንም ይሁን ምን፣ በድብቁ አእምሮህ ሃይል በእውነት የምታምን ከሆነ ድብቁ አእምሮህ ሁልጊዜ ሊኖርህ ወደማይችሉ መልሶች ሊመራህ ይችላል።

ንኡስ አእምሮህ የወሳኝ የአካል ክፍሎችህን ተግባር ብቻ ሳይሆን፣ ችግሮችን የመፍታት ብቃትም አለው- ልክ ለታዋቂው ኦርጋኒክ ኬሚስት እንዳደረገው።

የአንተስ የሕይወት ቤንዚን ቀመር ምን ይሆን? እስቲ ለድብቁ ለአእምሮህ ስጠውና እንዲፈታው አድርግ፡፡

ድብቁ አእምሮህን ኃይል ለማወቅና በትክክል ለመጠቀም ደግሞ ድብቁ አእምሮህ ድብቁ ኃይልህ መጽሐፍን እንድታነብ ትመከራለህ፡፡
በየመጽሐፍት መደብሩና በአዟሪዎች እጅ ይገኛል፡፡

#ድብቁ_አእምሮህ_ድብቁ_ኃይልህ መጽሐፍ


@the_motivators
@the_motivators