Get Mystery Box with random crypto!

#ማንም_የሚጎትትህ_አትሁን! አንድ ቀጠሮ ያለበት ሰው በመንገድ እየተጣደፈ ሲጓዝ ሌላ ነገረኛ ሰው | The Motivator

#ማንም_የሚጎትትህ_አትሁን!

አንድ ቀጠሮ ያለበት ሰው በመንገድ እየተጣደፈ ሲጓዝ ሌላ ነገረኛ ሰው ገጠመው። ነገረኛው ቀጠሮ የረፈደበትን በስድብ ያጣድፈው ጀመር። ሰውየው ሰአቱን ይመለከታል፣ የቀጠሮውም ሰዓት ሊረፍድበት ሆነ። እናም ድምጹን ከፍ አድርጎ -

"ወዳጄ አሁን ሰዓት ረፍዶብኛል። የቀረህ ስድብ ካለ ስመለስ ትጨርሰዋለህ" ብሎ ትቶት መንገዱን ቀጠለ።

የዚህ ሰው እጣ ፈንታ በነገረኛው ሰው አልተወሰነም። ጸብ መፍጠር ይችላል።

ሲሰዳደብም እዛው መዋል ይችላል። ሆኖም የእሱ እጣ ፈንታ በማንም አልፎ ሂያጅ የሚገደብ አልነበረም።

ከመንገዱም አላስቀረውም።

የብዙዎቻችን ህይወት ከዚህ በተቃራኒ ነው። ሰዎች ከመንገዳችን እያስወጡ ወደራሳቸው አቅጣጫ ይወስዱናል። አንዱ ይመጣና ወደዚህ ይወስድሃል፣ ሌላው ወደዚያ ይጎትትሃል።

በዚህ አይነት መንገድ ምንም ነገርን ማሳካት አትችልም።

ለመጥፎ ሰዎች ንግግር ምላሽን መስጠት ስትጀምር ለእነሱ ተገዢ ባሪያ ትሆናለህ።

እንደፈለጉትም ያደርጉሃል።

ማንም የሚጎትትህ አትሁን!

@the_motivators
@the_motivators