Get Mystery Box with random crypto!

#መንገድህን_ቀጥል!!! 1. የምትኖርበት ቤት ማንነትህን አይወክልም! አሁን ያለህበት ቤት ወደ | The Motivator

#መንገድህን_ቀጥል!!!

1. የምትኖርበት ቤት ማንነትህን አይወክልም!

አሁን ያለህበት ቤት ወደፊት የምትኖርበትን ስፍራ እስክታዘጋጅ መቆያህ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የምትኖርበት ቤት ማንነትህን እንዲተረጉመው ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡ 

2. የምትሰራበት ስፍራ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን የምትሰራው ስራ ጨዋና የስራ ሰው የመሆንህ ማሳያና ለወደፊት ማዳበር ለምትፈልገው ነገር መሸጋገሪያ ድልድይ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የምትሰራው ስራህ የማንነትህ መለኪያ እንዲሆን ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

3. የምታገኘው ደሞዝ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን የምታገኘው የገቢ መጠን ራእህን በመከታተል ላይ ሳለህ ለጊዜው ያለህን ፍላጎት ማሟያና ቀዳዳ መድፈኛ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ ደሞዝህ የማንነትህን ደረጃ እንዲመድብ ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

4. የትምህርት ደረጃህ ማንነትህን አይወክልም!

አሁን በጭንቅላትህ ውስጥ ያለው እውቀት ወደፊት ማወቅ ለምትፈልገው ነገር መነሻ፣ እንዲሁም ጥበብን ጨምረህበት የወቅቱን ሁኔታህን መግፊያ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ የትምህርት ደረጃህ ሰው የመሆንህን ዋጋ እንዲጨምረውና እንዲቀንሰው ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

5. ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ነገር ማንነትህን አይወክልም!

ሰዎች ስለአንተ የሚያስቡት ሃሳብ በመላ ምት ላይ የተመሰረተ፣ ከራሳቸው ምልከታ፣ ውስንነትና ልምምዳቸው ጋር የተዛመደ፣ ማመን የሚፈልጉትን ነገር እንደምክንያት የሚጠቀሙበት ሁኔታ ነው እንጂ ከማንነትህ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ ስለዚህ ሰዎች ማንነትህን እንዲተረጉሙት ባለመፍቀድ መንገድህን ቀጥል፡፡

ከላይ የዘረዘርኳቸውን እውነታዎች በሚገባ ስትገነዘብ በዙሪያህ ካሉ ሁኔታዎች ባሻገር ዘልቀህ የመሄድ አቅም ይሰጥሃል፡፡ ይህንን ሃሳብ በመታጠቅ ቀና ብለህ ራእይን ተመልከት፣ እቅድን አውጣ፣ ባለህ አቅም የመጀመሪያዋን እርምጃ ተራመድ፣ ግራና ቀኝ ሳትል በርትተህ መንገድህን ቀጥል . . . ትደርሳለህ !!!

ዶ/ር ኢዮብ ማሞ


@the_motivators
@the_motivators