Get Mystery Box with random crypto!

መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ! • ፈራችሁም አልፈራችሁም መኖራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እሞ | ሚሥጢሩ(The Secret)

መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ!

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መኖራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እሞታለሁ በሚልፍ ፍርሃት ታስራችሁ ከምትኖሩ ቀና ብላችሁ ብትኖሩ ይመረጣል፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መነገዳችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና እከስራለሁ በሚል በፍርሃት ታስራችሁ ከምትነግዱ በአዎንታዊነት ተነቃቅታችሁ በትነግዱ ይሻላል፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም መማራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ፈተና እወድቃለሁ በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምትማሩ እችለዋለሁ በሚል እምነትና ትጋት ብትማሩ የላቀ ነው፡፡

• ፈራችሁም አልፈራችሁም አንድን ሰው ማፍቀራችሁ ካልቀረ፣ ገና ለገና ይገፉኛል በሚል ፍርሃት ታስራችሁ ከምታፈቅሩ ጤናማ በራስ መተማመን ይዛችሁ ብታፈቅሩ እጅግ ተመራጭ ነው፡፡

መፍራት ስትጀምሩ መኖር ታቆማላችሁ! ቀና ብላችሁ መኖር ስትጀምሩ ደግሞ መፍራት ታቆማላችሁ!

ቀና ብላች ኑሩ እንጂ አትፍሩ!

@Abresh129
@the_law_of_attraction1