Get Mystery Box with random crypto!

ሐብት_ያላት_አትምረጥ!! ጀግና ልጅ ካገኘህ፤ ለተውሒድ ለሱና ለሐቅ የምትሰራ፡ አሟልቶ የሰጣት፤ | ሶሃቦች በቆሙበት ቁም!

ሐብት_ያላት_አትምረጥ!!
<---------------//-------------->
ጀግና ልጅ ካገኘህ፤
ለተውሒድ ለሱና ለሐቅ የምትሰራ፡
አሟልቶ የሰጣት፤
ሀብትና ውበትን በአንድነት አጣምራ፡
ፊትና እማይበግራት፤
ሁሉን ነገር ችላ በኒቃብ ያጌጠች፡
የማትደራደር፤
ከምንም ከማንም ድኗን ያስበለጠች፡
<------------------------------------------->
ያማረ ከሆነ አኽላቋ ፅናቷ፡
የተስተካከለ ውብ ከሆነ እምነቷ፡
ከቢዲዐ ከሽርክ ከፀዳ መንሀጇ፡
የሱናን ባንድራ ከጨበጠች በጇ፡

<------------------------------------>
እንደዚህ ከሆነች፤
አሏህ ወፍቆሀል ምክንያት አታብዛ፡
በዱዐህ ላይ በርታ፤
መልካም ነገር ሽጠህ መልካም ነገር ግዛ፡
አልያ ግን ወዳጀ፤
መንሀጅ የሌላት ልጅ ለትዳር አትበጅም፡
ፈፅሞ አትልፈስፈስ፤
በአቋምት ፅና ለምን አታረጅም፡
<-------------------------------------->
አወና____!!
<~~~~>
ገንዘብ አላት ብሎ፤
አቋም አልባ ፍጡር የማትሆንን ማግባት፡
ፍፃሜው ከንቱ ነው፤
መርህ አልባ ጉዞ ሚዛንን ማዛባት፡

<------------------------------------------>
ሲሳይ ከአሏህ ጠይቅ፤
መቼም ተስፋ አትቁረጥ፡
ለትዳርህ አስብ፤
ድን ያላትን እንጂ ሀብት ያላት አትምረጥ፡

በኑረዲን___!!


➘➘➘➘➘➘➘➘➘➘
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi