Get Mystery Box with random crypto!

_ሁለተኛ ሚስት ማግባት ያሰኘው ሰው ለሚስቱ ይቺን( የኢብኑ ባዝ) መልክት እንድታነብ ይስጣት ፡፡_ | አስ–ሱናህ

_ሁለተኛ ሚስት ማግባት ያሰኘው ሰው ለሚስቱ ይቺን( የኢብኑ ባዝ) መልክት እንድታነብ ይስጣት ፡፡_
_
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ይሄን ጥያቄ ተጠየቁ ፡

ጥያቄ፡- ክቡር ሸኽ አንዲት ሚስት አለችኝ፡ ከእሷም ልጆች አሉኝ፡ ሁለተኛ ሚስት ለማግባት በጣም እፈልጋለው፡ ግን ስለዚህ ጉዳይና ማግባት እንደምፈልግ ሚስቴን በነገርኳት ቁጥር አይሆንም ትለኛለች ፡ ካገባህ ትቼህ እሄዳለው ልጆችህንም ጭምር እያለች ትዝትብኛለች፡ ሸይኽ እኔንም እሷንም ምን
ትመክሩናላችሁ


መልስ፡- አንቺ የአላህ ባሪያ ሆይ ! በዚህ ተግባርሽ አላህን ልትፈሪው ይገባል፡ ማግባት የባል መብት (ሃቅ) እንጂ የሚስት አይደለም ፡ ባል ሁለተኛም፣ ሶስተኛም፣ አራተኛም ማግባት ቢፈልግ ሚስት መከልከል አትችልም ፡፡ ይሄን የደነገገው ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው (አላህ ሱብሃነሁ ወተኣላ) ነው፡፡ አላህ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች የሚበጀውን ያውቃል፡፡ ለዚህም ነው አላህ ይሄን የፈቀደው ለብዙ ጥቅሞች ሲል ነው፡ ከፊሎቹ ጥቅሞች ለራሷ ለሚስት ሲሆኑ ፡ ...... ከዚህ ሁሉ ዋናውና አሳሳቢው
ነገር ግን ባልሽ ሁለተኛ ማግባቱን መጥላትሽ ይህ በአንቺ ላይ በጣም ከባድ የሆነ አደጋ ነው ፡ አላህ በቁርአኑ ላይ ካወረደው ህግ ከፊሉን በመጥላትሽ መልካም ስራወችሽ እንዳይታበሱብሽ የሚያስፈራ ከባድ አደጋ ነው፡ ምክኒያቱም አላህ ግልፅ በሆነ የቁርአን አንቀፅ እስከ አራት ድረስ ሚስትን መደጋገም አዟል ፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانْكِحُوا مَا طَابَ لَكُمْ مِنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا
" ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሶስት ሶስትም፣ አራት አራትም አግቡ ፡
[ ምዕራፍ፡ ኒሳዕ፣ አንቀፅ 3 ]
አላህ በቁርአን ላይ ያወረደውን ህግ መጥለት መልካም ስራወችን የግድ ያሳብሳል፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-" ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው ስለዚህ ስራወቻቸውን አበላሸባቸው "
[ምዕራፍ፡ ሙሃመድ፣ አንቀፅ 9]
መልካም ስራን ለማሳበስ የግድ ሁሉንም አላህ ያወረደውን ማስተባበል አይጠበቅብሽም፡ አንዲትም
ብትሆን በቂ ናት
፡፡


( _ፈትዋ ኑሩን አለ - ደርብ_)

https://t.me/tewihd/