Get Mystery Box with random crypto!

Nehemiah Tube ✝️ ነሕምያ ትዩብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo_bete — Nehemiah Tube ✝️ ነሕምያ ትዩብ N
የቴሌግራም ቻናል አርማ tewahedo_bete — Nehemiah Tube ✝️ ነሕምያ ትዩብ
የሰርጥ አድራሻ: @tewahedo_bete
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.71K
የሰርጥ መግለጫ

Subscribe to our YouTube channel;
https://www.youtube.com/c/NehemiahTube2013
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ለዘላለም ትኑር!

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

3

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-20 19:33:05 መምህር ዲ/ን መኳንንት ረቡማ አዲስ ዝማሬ «ስለ ድንግል ብለህ»



1.9K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-01 19:13:02 የተመረጡ በአብይ ጾም የሚዘመሩ የንስሐ መዝሙሮች ስብስብ /፪/

በ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ


ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ያዳምጡ ፥ ቻናላችንንም Subscribe ያድርጉ!








6.5K views16:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-14 19:33:34 የተመረጡ በአብይ ጾም የሚዘመሩ የንስሐ መዝሙሮች ስብስብ /፩/

በ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ያዳምጡ ፥ ቻናላችንንም Subscribe ያድርጉ!








2.4K views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-28 09:25:58 ባሕረ ሀሳብ መተግበርያ
2.5K viewsedited  06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-24 18:50:52 የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓል በአምቦ ከተማ

Kabaja Ayyaana Yaadannoo Abbaa keenya Abuna Gabra Manfas Qidduus Magaalaa Ambootti

ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ያዳምጡ!









2.3K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-17 16:13:42 Faarfannaa Haaraa Ortodoksii Tawaahidoo Afaan Oromoo laphee nama qabbaneessu «Kennaan kan guutamtee»

Karaa Nehemiah Tube qofaa!

Link kana tuquun dhageeffadhaa!








4.7K views13:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-14 18:10:27 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች

ክፍል 5 ፭

/31/ የመስፍኑ ኢያሱ የመጀመሪያ ስሙ ማን ይባላል? ኢያሱ
ብሎ ስም ያወጣለት ማን ነው? ኢያሱ ማለትስ ምን ማለት ነው?
ኢያሱ የመጀመሪያ ስሙ አውሴ ሲሆን ኢያሱ ብሎ ስም
ያወጣለትም ነብዩ ሙሴ ነበር፤ ሙሴ ማለት የተወለደ ማለት
ሲሆን ኢያሱ ማለት መድኀኒት ማለት ነው።
[ዘኁልቍ 13:16]
/32/ ቅ/ጳውሎስ የመዳን ቀን አሁን ነው [1ኛ ቆሮ 6: 1] እንዳለ
አንድ መስፍንም እንዲህ ብሎ ነበር፦ “አነ ወቤትየ
እግዚአብሔርን ነአመልክ” ይህን ቃል የተናገረው መስፍን ማን
ይባላል? የግዕዙ ትርጉምስ ምን ማለት ነው?
“አነ ወቤትየ እግዚአብሔርን ነአመልክ”
/እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን/
ያለው መስፍኑ ኢያሱ ነው።
/33/ እኔ ማነኝ? መስፍኑ ኢያሱ ፪ ሰላዮችን ኢያሪኮን እንዲሰልሉ
በላከ ግዜ የከተማዋ ወታደሮች ሰዎቹን ሊገድሉ ሲፈልጉ እኔ ግን
ከቤቴ ጣሪያ ላይ በረበረብኩት የተልባ እግር ውስጥ ደበኳቸውና
ወታደሮቹን በሌላ አቅጣጫ ልኬ አስመለጥኳቸው፤ ልክ እንደ
አንዲት እስራኤላዊት ሴት ሆኜ ስላገለገልኳቸው እነዚያ ሰዎች
ከተማዋን ስንቆጣጠር እንድናውቅሽና ምልክትም እንዲሆነን ቀይ
ፈትልሽን በመስኮትሽ ላይ እሰሪ አሉኝ፤ እኔም እነ ኢያሱ ኢያሪኮን
በተቆጣጠሩ ግዜ ቀዩን ፈትሌን በመስኮቴ ላይ አስሬ ነበርና
የከተማዋ ሰዎች ሲጠፉ እኔ ግን ተረፍኩ፤ ቅ/ጳውሎስም ዝሙት
አዳሪዋ ሰላዮችን በሠላም ስላስተናገደች ከማይታዘዙት ጋር
ያልጠፋችው በእምነቷ ነው ብሎ በዕብራዊያን 11ኛው ምዕራፍ
ላይ ስለ ታላቁ እምነቴ የተናገረልኝ እኔ ማን ነኝ?
እኔ “ረዓብ” ነኝ [ኢያሱ 2: 1] [ዕብራዊያን 11:31]
/34/ እኛ ማን ነን? መስፍኑ ኢያሱ ኢያሪኮንና ጋይ የተባለችውን
ከተማ በታላቅ ሃይል እንደደመሰሰ ሰማን፤ ቀጥሎም ወደ እኛ
እንደሚመጣ ስላወቅን “ለእባብ እግር የለው ለሞኝ ብልኀት
የለው” እንዳንባል ቀድመን ዘዴ ፈጠርን፤ ያረጀ ልብስ ለበስን!
የያዝነው ስንቅ ሁሉ የሻገተና የደረቀ እንጀራ ነበር! መስፍኑ ኢያሱ
ጋር ቀረብንና ጌታችን ሆይ እኛ ዝናችሁን ሰምተን ከሩቅ ሃገር
የመጣን እንግዳ ነንና እንዳትጎዱን በእግዚአብሔር ስም ቃል
ግቡልን አልናቸው። እስራኤላዊያንም ቃል ገቡልን፤ ይሁን እንጂ
ከ፫ ቀን በኋላ እኛ የዛው ከተማ ነዋሪ እንደሆንንና
እንዳታለልናቸው አወቁብን፤ ቃል ስለገቡልን ግን አልጎዱንም። እኛ
ማን ነን?
ያረጀ ልብስ ለበስን! የያዝነው ስንቅ ሁሉ የሻገተና የደረቀ እንጀራ
ነበር! መስፍኑ ኢያሱ ጋር ቀረብንና ጌታችን ሆይ እኛ ዝናችሁን
ሰምተን ከሩቅ ሃገር የመጣን እንግዳ ነን ብለን እስራኤላዊያንን
ያታለልናቸው “የገባዖን ሰዎች” ስንሆን በዚህ ምክንያትም ኢያሱ
ውሃ ቀጂና እንጨት ሰባሪ አድርጎናል [ኢያሱ 9:1]
መፅሐፈ መሳፍንት
/35/ * አንድ መስፍን “ጦርነት ወጥቼ በድል ብመለስ ሊቀበለኝ
የሚወጣውን ማንኛውንም ሰው መስዋዕት አድርጌ አቀርባለሁ”
አለ፤ እንዳለውም ከጦርነቱ በድል ሲመለስ ለዓይኑ ማረፊያ
የሆነችው አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና ከበሮ እየመታች
ልትቀበለው ሮጠች፤ ያ ሰው ግን ከሩቅ አያትና አዘነ! ልጁንም
መስዋዕት ትሁን ብሏልና አቃጠላት! ይህ ልመና የማይችልበት
ሰው ማን ይባላል?
ዮፍታሔ ነው፤ አዬ ልመና አለመቻል ስንት መለመን ሲቻል ዮፍታሔ
ግን ከንቱ ሥዕለትን ተሳለ፤ ጌታችንም የምትለምኑትን አታውቁም
ያለው ይህንን መሳይ ሥዕለት ነው። መሳፍንት [11: 31]
/36/ *ንጉሥ ሲሳራ እስራኤልን ለ20 አመት አስጨንቆ ገዝቷት
ነበር፤ አንዲት ሴት ነብይም ባርቅን አስጠርታ ተነሳ እግዚአብሔር
ሢሳራን በእጅህ ጥሎልሃል አለችው፤ ባርቅም አንቺ አብረሽኝ
ካልሄድሽ አልነሳም አለ። ያቺ ሴት ነብይም ባርቅን አስከትላ ወደ
ታቦር ተራራ ወጣችና ሢሳራን ድል አደረጉ። ይህች ሴት ነብይ
ማን ትባላለች?
ዲቦራ ናት፤ የስሟ ትርጉም ንብ ማለት ነው። ይህን ታሪክ በድል
መዝሙር ላይ ዲቦራና ባርቅ እያልን በብዛት እንዘምረዋለን።
መሳፍንት [4: 1]
/37/ በመፅሐፍ ቅዱስ ፮ መሳፍንት አሉ፤ እነሱም ጎቶንያል ፣
ናዖድ ፣ ጌዲዮን ፣ ዮፍታሔና ሶምሶን ሲሆኑ ብቸኛዋ ሴት መስፍን
ማን ትባላለች?
ዲቦራ ናት፤ የስሟ ትርጉም ንብ ማለት ነው።
* /38/ እኔ ማን ነኝ?
ምዳማዊያን እስራኤልን ሲወሩ እንዳልታይ በወይን መጭመቂያው
ስፍራ ስንዴ አበጥር ነበር፤ የእግዚአብሔር መልአክም ተገለጠና
“አንተ ኃያል ሰው እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው” አለኝ፤ መልአኩ
ተገልጦ “እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው” ስላለኝም ምዳማዊያንን
በ300 ችቦ ድል አደረኳቸው!!! ይህ ሁሉ ታሪክ ያለኝ እኔ ማን ነኝ?
ጌዴዮን
/39/ የሶምሶም ኃይል በፀጉሩ ላይ እንደሆነ ሚስጢር
ያወጣችበት ሴት ማን ትባላለች?
ደሊላ
/40/ ዮርዳኖስን ተቆጣጠሩና በዚያ የሚያልፉትን ሰዎች “አንተ
ኤፍሬማዊ ነህን”? ይሉታል፤ አይደለሁም ካለ “እስኪ ሺቦሌት
በል” ይሉታል “ሲቦሌት” ቢል እዛው ይገድሉታል። እነዚህ ሰዎች
ማን ይባላሉ? ፍንጭ መሳፍንት [12: 5]
ገለዓዳዊያን ናቸው፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምስራቅ ያሉ እስራኤላዊያን
መነሻውን ጠበቅ አድርገው “ሺቦሌት” ይላሉ ትርጉሙም ጎርፍ
ማለት ነው፤ በስደት ሀገር በከነዓን ያሉ እስራኤላዊያን ግን
ቋንቋቸው ስለከበዳቸው “ሲቦሌት” ነበር የሚሉት፤ በዚህ
ምክንያት እየታወቁ ይገደሉ ነበር። ወላጆች ሆይ ልጆቻችሁን
ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና ሐይማኖታቸውን በሚገባ አስተምሩ።
/41/ የእግዚአብሔር መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ተገልጦ
“የምትወልዱት መስፍን ታላቅ ነው፤ ናዝራዊም ይባላል” አላቸው።
ማኑሄም “የተናገርከው ሲደርስ እንድናከብርህ ስምህ ማን
ይባላል”? ብሎ ጠየቀው፤ መልአኩም “ስሜ ድንቅ ነው” አለው፤
ማኑሄም መስዋዕትን ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ መልአኩም
መስዋዕቱን አሳረገለት፤ እሳታዊ መሆኑን ሲያስረዳም በነበልባሉ
ውስጥ ዐረገ። እንደ መጥምቁ ዩሐንስ በመልአክ አብሳሪነት
የተወለደው ታላቁ መስፍን ማን ይባላል?
ሶምሶን ነው፤ የስሙ ትርጉም ፀሐይ ማለት ነው።
መሳፍንት [13: 15]
/42/ ታላቁ መስፍን አንበሳን በክንዱ አደቀቀ ከመንጋጋው
ከሰፈሩት ንቦችም ማር እየወቆረጠ መንገድ ለመንገድ በላ፤
“ከበላተኛው መብል ከብርቱም ጣፋጭ ነገር ወጣ” እያለም
ለፍልስጤማዊያን እንቆቅልሽ ጠየቃቸው፤ ደሊላ የተባለችው ሴት
ግን ይህ ሁሉ ኃይሉ በፀጉሩ ላይ እንደነበር ለጠላቶቹ ነገረችበት፤
ፀጉሩም ተላጨ ኃይሉም ከንቱ ሆነ፤ ይህ የማኑሄ ልጅ ማን
ይባላል?
ሶምሶን ነው፤ የስሙ ትርጉም ፀሐይ ማለት ነው።
መሳፍንት [14:14]
መፅሐፈ ሩት
/43/ መሳፍንት በሚገዙበት ዘመን በምድሪቱ ላይ ረሃብ ሆነ፤
በዚህም ምክንያት አቤሜሌክ የተባለ ፩ድ ሰው ፪ ልጆችንና
ኑኃሚን የተባለችውን ሚስቱን ይዞ ተሰደደ። ከጥቂት ግዜ በኃላ
ግን ኑኃሚን ባሏና ልጆቿ ሞተው በስደት ሃገር ብቻዋን ቀረች፤
ወደ ሀገርዋ ስትመለስ “ሕዝብሽ ሕዝቤ አምላክሽ አምላኬ” ብላ
እስከ መጨመሻው ድረስ አልለይሽም ያለቻት ታማኝ ሴት ማን
ትባላለች?
ሩት የስሟ ትርጉም ወዳጅ ማለት ነው።
፩ኛ ሳሙኤል
ታላቁ ነብይ ሳሙኤል ሳሙኤል ሳሙኤል ተብሎ ተጠራ
/44/ የመጀመሪያዎችን 2 የእስራኤል ነገሥታት /ሳዖልንና
ዳዊትን/ የቀባው ታላቁ ነብይ ማን ይባላል?
ሳሙኤል፤ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
/45/ ለመጥምቁ ዮሐንስ እናትና አባቱ ዘካርያስና ኤልሳቤት
ከተባሉ ለሳሙኤል ማን ይባላሉ? ፍንጭ 1ኛ ሳሙ [1:1]
ሕልቃና እና ሐና

ይቀጥላል!

ይቀላቀሉ Join @tewahedo_bete
@tewahedo_bete
2.2K views15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-06 06:12:10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች

ክፍል 4 /፬/

/21/ ነብዩ ሙሴ ወደ ሲና ተራራ ሲወጣ መስፍኑ ኢያሱ ግን
ከተራራው ግርጌ ነበር እንጂ ወደ ተራራው አልወጣም ነበር፤
ይህም የሆነበት የራሱ ምክንያት አለው፤ ኢያሱ ወደ ሲና ተራራ
ያልወጣው በምን ምክንያት ይሆን?
ሙሴን የሚረዱ 70 ሽማግሌዎች ነበሩ፤ እነዚህ 70
ሽማግሌዎች የሙሴ መንፈስ አድሮባቸው ትንቢት ሲተነብዩ ኢያሱ
ግን በቅንአት ሙሴ ሆይ! ለምን ዝም እንዲሉ አትከለክላቸውም?
ብሎ ተቆጣ፤ በዚህም ምክንያት ኢያሱ በሲና ተራራ ሳይወጣ
እስከ ተራራዋ ግርጌ ብቻ ለመጓዝ ተገዷል።
፪ቱ ነብያትና ፫ቱ አእማደ ሐዋርያት ብቻ በታቦር ተራራ ላይ
ሲወጡ ይሁዳ “እኔ እኮ ጌታን የሸጥኩት በታቦር ተራራ ላይ
ስላልወጣሁ ነው” ብሎ ምክንያት እንዳያቀርብ ይሁዳን ጨምሮ
ቀሪዎቹ ሐዋርያት በተራራው ግርጌ ነበሩ፤ ይሁዳም ወደ ታቦር
ተራራ ያልወጣው በከንቱ ስራው ምክንያት ነው። ተራራ
የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናትና ወደዚህች ተራራ የሚወጡት ሁሉን
ነገር አራግፈው ነው። መስፍኑ ኢያሱም ከስህተቱ ከተማረ በኋላ
የሙሴ ተተኪ የሆነ ታላቅ መሪ ሆኗል! [ዘኁልቍ 11:28]
/22/ በመፅሐፍ ቅዱስ ስማቸው አንድ አይነት ሆነው ስራቸው
ግን እጅግ ተቃራኒ የሆኑ ፊንሐስ የሚባሉ 2 ሰዎች አሉ፤ ይህ
ተቃራኒ ተግባራቸው ምንድን ነው?
ፍንጭ ዘኁልቅ [25: 1-14]
የመጀመሪያው ፊንሐስ፦ የሙሴ ወንድም የአሮን ልጅ አልዓዛር
ነው፤ የአልዓዛር ልጅም ፊንሐስ ነው። ፊንሐስ ለእግዚአብሔር
ቀናተኛ ስለነበር ክህነት ለዘሩ ወይንም ለሌዋውያን እንዲሆን
አድርጓል። ፊንሐስ የክህነት ቃል ኪዳኑን እንዴት እንዳገኘ ዘኁልቅ
[25: 1-14] ማየት ይቻላል።
ሁለተኛው ፊንሐስ፦ ይህ ደግሞ የዔሊ ልጅ ሲሆን ከወንድሙ ጋር
አፍኒንና ፊንሐስ ተብለው ሲጠሩ ይበልጥ ይታወቃሉ።
የመጀመሪያው ፊንሐስ በመገናኛ ድንኳኑ ዝሙት የሚፈጽሙትን
በጦር ወግቶ የገደለው ነው፤ ሁለተኛው ፊንሐስ ግን በመገናኛ
ድንክን ዝሙት የፈጸመው ነው፤ አይ የስም መመሳሰልና የተግባር
ልዩነቱ!
/23/ በአንድ ወቅት ዳታን ፣ አቤሮን ፣ ቆሬና 250 ሰዎች ሙሴን
የተቃወሙ፤ እነዚህ ሰዎች የተቀቱት እንዴት ነበር? እነዚህ ሰዎች
ሙሴና አሮንን ሲቃወሙ እግዚአብሔር እንዴት ጠበቃቸው?
ለሰዎቹ የመጣው መቅሰፍትስ እንዴት ቀረላቸው? ፍንጭ [ዘኁልቍ
16:1]
* ሙሴንና አሮንን ተቃወመው ራሳቸውን እንደ ካህን የቆጠሩ
ቆሬና 250 ሰዎች በአንድ ቀን በእሳት ተቃጥለው ሞቱ; እነሱን
የተባበሩ ዳታንና አቤሮን ደግሞ ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው።
ዘኁልቊ 16:31-36 ፤ ሲነጋም እስራኤላዊያን ህዝቡን
አስገደላቹ ብለው በድንጋይ ሊወግሯቸው ተነሱ; ሙሴና አሮን
ወደ ደብተራ ኦሪት ሸሹ። እግዚአብሔርም አምደ ብርሐን ከልሎ
አዳናቸውና ሁለቱን ወንድማማቾች ከእስራኤላዊያን ማህበር
ፈቀቅ በሉ; በቅስፈት አጠፋቸዋለሁ ብሎ በአንድ ቀን 14ሺ 700
ሰዎች ሞቱ። አሮን ልብሰ ተክህኖ ለብሶ ማዕጠንተ ወርቁን ይዞ
ቢጸልያላቸው መቅሰፍቱ ተወገደ ዘኁ.16:41
*የተመረጠው ሙሴ በፊቱ ባይቆም ኖሮ በመቅሰፍቱ ባጠፋቸው
ነበር ይላል; መዝ 105:23።
(ማክበር ለበረከት አለማክበርም ለመቅሰፍት ነውና)
/24/በሀገራችን በዓል በሆነ ግዜ የበግ ደም በሣህን ተጠራቅሞ
ይበላል፤ በገጠሩ ደግሞ በሬው ገና ሳይሞት ከእነ ህይወቱ እያለ
በሹል ነገር አንገቱን እየበጡ ደም የሚጠጡ አሉ! ይህ ባህል
በመፅሐፍ ቅዱስ ይደገፋል ወይስ የተከለከለ ነው? ለምን?
ታንቆ የተገኘውን ወይም አውሬ የዘነጠለውን መብላት ፣
የእንስሳትን ደም መጠጣት እጅግ የተከለከለ ነው፤ [ዘሌዋውያን
ምዕ 17:1-16] ከመ ነፍስ ዘይኃድር በደም እንዲል በደም
ውስጥ የእንስሳት ህይወት ስላለ ደም መጠጣት እጅግ የተከለከለ
ነው።
መፅሐፈ ኢያሱ
እስራኤላዊያን
በኢያሱ መሪነት ዮርዳኖስን ሲሻገሩ
/25/ እኔ ማን ነኝ? የመጀመሪያ ስሜ አውሴ ነው፤ በወጣትነቴ
የግብጽን ባርነት የቀመስኩ፣ የኤርትራ ባሕር ሲከፈል በዓይኔ
ያየሁ፣ ከካሌብ ጋር ምድር ርስትን የሰለልኩ ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ
የሙሴ አገልጋይ የነበርኩ እኔ ማን ነን?
“ኢያሱ”
/26/ እኛ ማነን? ሰማይን 3 1/2 ዓመት የዘጋን ፀሐይን በገባዖን
ያቆምን የእግዚአብሔር አገልጋይ እኛ ማነን?
ኤልያስና ኢያሱ ናቸው፤ ኤልያስ ማለት እግዚአብሔር አምላኬ
ነው ማለት ሲሆን ኢያሱ ማለት ደግሞ መድኃኒት ማለት ነው።
*/27/ ምድረ ርስት ከንዓንን የወረሱት ፪ቱ ሰዎች እነማን ናቸው?
ኢያሱና ካሌብ
* /28/ እነ ኢያሱ ታበተ ፅዮንን ይዘው ዮርዳኖስን ሲሻረሩ ወንዙ
ሞልቶ ነበር፤ ይህም የሆነው ከአንድ ተራራ ላይ ከሚቀልጠው
የበረዶ ግግር ምክንያት ሲሆን እመቤታችንም ስትወለድ ይህ
ተራራ እንደ ችቦ ከሩቅ ያበራ ነበር፤ ይህ ተራራ ማን ይባላል?
የሊባኖስ ራስ የአርሞንኤም ተራራ ነው።
/29/ እኔ ማን ነኝ? መስፍኑ ኢያሱ ጋይ የተባለችውን ከተማ
ከመደምሰሱ በፊት እኔ ከዛች ከተማ እርም የሆነውን የወርቅ
ቡችላና የሚያምር ካባ አይቼ ሰረኩና በድንኳኔ ውስጥ ደበኩት፤
በእኔ ኃጢአትም እስራኤላዊያን በጋይ ሰዎች ተሸነፉ፤ እኔ ማን
ነኝ? እኔ የተቀጣሁትስ እንዴት ነበር?
ፍንጭ [ኢያሱ 7: 19]
እኔ “አካን” ስሆን የተቀጣሁትም በድንጋይ ተወግሬ ነበር። [ኢያሱ
7: 19]
/30/ መስፍኑ ኢያሱ በሌዋውያን ካህናትን ታቦተ ጽዮንን
አስከትሎ የ፩ዲት ከተማን ግንብ ፯ ግዜ ሲዞር ያቺ ከተማ
በ፯ኛው ፈረሰች፤ ይህች ከተማ ማን ትባላለች? የከተማዋ ስም
ትርጉሙ ምን ማለት ነው?
ኢያሪኮ ስትሆን የኢያሪኮ ሰዎች ጨረቃን ስለሚያመልኩ
ከተማቸውን ኢያሪኮ ብለው ጠሯት፤ ኢያሪኮ ማለት የጨረቃ
ከተማ ማለት ነው።

ይቀጥላል!

ይቀላቀሉ Join @tewahedo_bete
1.9K views03:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-30 18:40:59 እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርኃዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የተመረጡ ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ የተዘመሩ መዝሙሮች ስብስብ


ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት ያዳምጡ ፥ ቻናላችንንም Subscribe ያድርጉ!








1.7K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-01-29 07:59:32
ጽዮን ሆይ | ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

Join @tewahedo_bete
1.5K views04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ