Get Mystery Box with random crypto!

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች ክፍል 5 ፭ /31/ የመስፍኑ ኢያሱ የመጀመሪያ ስሙ ማን ይባላል? ኢያ | Nehemiah Tube ✝️ ነሕምያ ትዩብ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች

ክፍል 5 ፭

/31/ የመስፍኑ ኢያሱ የመጀመሪያ ስሙ ማን ይባላል? ኢያሱ
ብሎ ስም ያወጣለት ማን ነው? ኢያሱ ማለትስ ምን ማለት ነው?
ኢያሱ የመጀመሪያ ስሙ አውሴ ሲሆን ኢያሱ ብሎ ስም
ያወጣለትም ነብዩ ሙሴ ነበር፤ ሙሴ ማለት የተወለደ ማለት
ሲሆን ኢያሱ ማለት መድኀኒት ማለት ነው።
[ዘኁልቍ 13:16]
/32/ ቅ/ጳውሎስ የመዳን ቀን አሁን ነው [1ኛ ቆሮ 6: 1] እንዳለ
አንድ መስፍንም እንዲህ ብሎ ነበር፦ “አነ ወቤትየ
እግዚአብሔርን ነአመልክ” ይህን ቃል የተናገረው መስፍን ማን
ይባላል? የግዕዙ ትርጉምስ ምን ማለት ነው?
“አነ ወቤትየ እግዚአብሔርን ነአመልክ”
/እኔና ቤቴ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን/
ያለው መስፍኑ ኢያሱ ነው።
/33/ እኔ ማነኝ? መስፍኑ ኢያሱ ፪ ሰላዮችን ኢያሪኮን እንዲሰልሉ
በላከ ግዜ የከተማዋ ወታደሮች ሰዎቹን ሊገድሉ ሲፈልጉ እኔ ግን
ከቤቴ ጣሪያ ላይ በረበረብኩት የተልባ እግር ውስጥ ደበኳቸውና
ወታደሮቹን በሌላ አቅጣጫ ልኬ አስመለጥኳቸው፤ ልክ እንደ
አንዲት እስራኤላዊት ሴት ሆኜ ስላገለገልኳቸው እነዚያ ሰዎች
ከተማዋን ስንቆጣጠር እንድናውቅሽና ምልክትም እንዲሆነን ቀይ
ፈትልሽን በመስኮትሽ ላይ እሰሪ አሉኝ፤ እኔም እነ ኢያሱ ኢያሪኮን
በተቆጣጠሩ ግዜ ቀዩን ፈትሌን በመስኮቴ ላይ አስሬ ነበርና
የከተማዋ ሰዎች ሲጠፉ እኔ ግን ተረፍኩ፤ ቅ/ጳውሎስም ዝሙት
አዳሪዋ ሰላዮችን በሠላም ስላስተናገደች ከማይታዘዙት ጋር
ያልጠፋችው በእምነቷ ነው ብሎ በዕብራዊያን 11ኛው ምዕራፍ
ላይ ስለ ታላቁ እምነቴ የተናገረልኝ እኔ ማን ነኝ?
እኔ “ረዓብ” ነኝ [ኢያሱ 2: 1] [ዕብራዊያን 11:31]
/34/ እኛ ማን ነን? መስፍኑ ኢያሱ ኢያሪኮንና ጋይ የተባለችውን
ከተማ በታላቅ ሃይል እንደደመሰሰ ሰማን፤ ቀጥሎም ወደ እኛ
እንደሚመጣ ስላወቅን “ለእባብ እግር የለው ለሞኝ ብልኀት
የለው” እንዳንባል ቀድመን ዘዴ ፈጠርን፤ ያረጀ ልብስ ለበስን!
የያዝነው ስንቅ ሁሉ የሻገተና የደረቀ እንጀራ ነበር! መስፍኑ ኢያሱ
ጋር ቀረብንና ጌታችን ሆይ እኛ ዝናችሁን ሰምተን ከሩቅ ሃገር
የመጣን እንግዳ ነንና እንዳትጎዱን በእግዚአብሔር ስም ቃል
ግቡልን አልናቸው። እስራኤላዊያንም ቃል ገቡልን፤ ይሁን እንጂ
ከ፫ ቀን በኋላ እኛ የዛው ከተማ ነዋሪ እንደሆንንና
እንዳታለልናቸው አወቁብን፤ ቃል ስለገቡልን ግን አልጎዱንም። እኛ
ማን ነን?
ያረጀ ልብስ ለበስን! የያዝነው ስንቅ ሁሉ የሻገተና የደረቀ እንጀራ
ነበር! መስፍኑ ኢያሱ ጋር ቀረብንና ጌታችን ሆይ እኛ ዝናችሁን
ሰምተን ከሩቅ ሃገር የመጣን እንግዳ ነን ብለን እስራኤላዊያንን
ያታለልናቸው “የገባዖን ሰዎች” ስንሆን በዚህ ምክንያትም ኢያሱ
ውሃ ቀጂና እንጨት ሰባሪ አድርጎናል [ኢያሱ 9:1]
መፅሐፈ መሳፍንት
/35/ * አንድ መስፍን “ጦርነት ወጥቼ በድል ብመለስ ሊቀበለኝ
የሚወጣውን ማንኛውንም ሰው መስዋዕት አድርጌ አቀርባለሁ”
አለ፤ እንዳለውም ከጦርነቱ በድል ሲመለስ ለዓይኑ ማረፊያ
የሆነችው አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና ከበሮ እየመታች
ልትቀበለው ሮጠች፤ ያ ሰው ግን ከሩቅ አያትና አዘነ! ልጁንም
መስዋዕት ትሁን ብሏልና አቃጠላት! ይህ ልመና የማይችልበት
ሰው ማን ይባላል?
ዮፍታሔ ነው፤ አዬ ልመና አለመቻል ስንት መለመን ሲቻል ዮፍታሔ
ግን ከንቱ ሥዕለትን ተሳለ፤ ጌታችንም የምትለምኑትን አታውቁም
ያለው ይህንን መሳይ ሥዕለት ነው። መሳፍንት [11: 31]
/36/ *ንጉሥ ሲሳራ እስራኤልን ለ20 አመት አስጨንቆ ገዝቷት
ነበር፤ አንዲት ሴት ነብይም ባርቅን አስጠርታ ተነሳ እግዚአብሔር
ሢሳራን በእጅህ ጥሎልሃል አለችው፤ ባርቅም አንቺ አብረሽኝ
ካልሄድሽ አልነሳም አለ። ያቺ ሴት ነብይም ባርቅን አስከትላ ወደ
ታቦር ተራራ ወጣችና ሢሳራን ድል አደረጉ። ይህች ሴት ነብይ
ማን ትባላለች?
ዲቦራ ናት፤ የስሟ ትርጉም ንብ ማለት ነው። ይህን ታሪክ በድል
መዝሙር ላይ ዲቦራና ባርቅ እያልን በብዛት እንዘምረዋለን።
መሳፍንት [4: 1]
/37/ በመፅሐፍ ቅዱስ ፮ መሳፍንት አሉ፤ እነሱም ጎቶንያል ፣
ናዖድ ፣ ጌዲዮን ፣ ዮፍታሔና ሶምሶን ሲሆኑ ብቸኛዋ ሴት መስፍን
ማን ትባላለች?
ዲቦራ ናት፤ የስሟ ትርጉም ንብ ማለት ነው።
* /38/ እኔ ማን ነኝ?
ምዳማዊያን እስራኤልን ሲወሩ እንዳልታይ በወይን መጭመቂያው
ስፍራ ስንዴ አበጥር ነበር፤ የእግዚአብሔር መልአክም ተገለጠና
“አንተ ኃያል ሰው እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው” አለኝ፤ መልአኩ
ተገልጦ “እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነው” ስላለኝም ምዳማዊያንን
በ300 ችቦ ድል አደረኳቸው!!! ይህ ሁሉ ታሪክ ያለኝ እኔ ማን ነኝ?
ጌዴዮን
/39/ የሶምሶም ኃይል በፀጉሩ ላይ እንደሆነ ሚስጢር
ያወጣችበት ሴት ማን ትባላለች?
ደሊላ
/40/ ዮርዳኖስን ተቆጣጠሩና በዚያ የሚያልፉትን ሰዎች “አንተ
ኤፍሬማዊ ነህን”? ይሉታል፤ አይደለሁም ካለ “እስኪ ሺቦሌት
በል” ይሉታል “ሲቦሌት” ቢል እዛው ይገድሉታል። እነዚህ ሰዎች
ማን ይባላሉ? ፍንጭ መሳፍንት [12: 5]
ገለዓዳዊያን ናቸው፤ ከዮርዳኖስ በስተ ምስራቅ ያሉ እስራኤላዊያን
መነሻውን ጠበቅ አድርገው “ሺቦሌት” ይላሉ ትርጉሙም ጎርፍ
ማለት ነው፤ በስደት ሀገር በከነዓን ያሉ እስራኤላዊያን ግን
ቋንቋቸው ስለከበዳቸው “ሲቦሌት” ነበር የሚሉት፤ በዚህ
ምክንያት እየታወቁ ይገደሉ ነበር። ወላጆች ሆይ ልጆቻችሁን
ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና ሐይማኖታቸውን በሚገባ አስተምሩ።
/41/ የእግዚአብሔር መልአክ ለማኑሄና ለሚስቱ ተገልጦ
“የምትወልዱት መስፍን ታላቅ ነው፤ ናዝራዊም ይባላል” አላቸው።
ማኑሄም “የተናገርከው ሲደርስ እንድናከብርህ ስምህ ማን
ይባላል”? ብሎ ጠየቀው፤ መልአኩም “ስሜ ድንቅ ነው” አለው፤
ማኑሄም መስዋዕትን ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ መልአኩም
መስዋዕቱን አሳረገለት፤ እሳታዊ መሆኑን ሲያስረዳም በነበልባሉ
ውስጥ ዐረገ። እንደ መጥምቁ ዩሐንስ በመልአክ አብሳሪነት
የተወለደው ታላቁ መስፍን ማን ይባላል?
ሶምሶን ነው፤ የስሙ ትርጉም ፀሐይ ማለት ነው።
መሳፍንት [13: 15]
/42/ ታላቁ መስፍን አንበሳን በክንዱ አደቀቀ ከመንጋጋው
ከሰፈሩት ንቦችም ማር እየወቆረጠ መንገድ ለመንገድ በላ፤
“ከበላተኛው መብል ከብርቱም ጣፋጭ ነገር ወጣ” እያለም
ለፍልስጤማዊያን እንቆቅልሽ ጠየቃቸው፤ ደሊላ የተባለችው ሴት
ግን ይህ ሁሉ ኃይሉ በፀጉሩ ላይ እንደነበር ለጠላቶቹ ነገረችበት፤
ፀጉሩም ተላጨ ኃይሉም ከንቱ ሆነ፤ ይህ የማኑሄ ልጅ ማን
ይባላል?
ሶምሶን ነው፤ የስሙ ትርጉም ፀሐይ ማለት ነው።
መሳፍንት [14:14]
መፅሐፈ ሩት
/43/ መሳፍንት በሚገዙበት ዘመን በምድሪቱ ላይ ረሃብ ሆነ፤
በዚህም ምክንያት አቤሜሌክ የተባለ ፩ድ ሰው ፪ ልጆችንና
ኑኃሚን የተባለችውን ሚስቱን ይዞ ተሰደደ። ከጥቂት ግዜ በኃላ
ግን ኑኃሚን ባሏና ልጆቿ ሞተው በስደት ሃገር ብቻዋን ቀረች፤
ወደ ሀገርዋ ስትመለስ “ሕዝብሽ ሕዝቤ አምላክሽ አምላኬ” ብላ
እስከ መጨመሻው ድረስ አልለይሽም ያለቻት ታማኝ ሴት ማን
ትባላለች?
ሩት የስሟ ትርጉም ወዳጅ ማለት ነው።
፩ኛ ሳሙኤል
ታላቁ ነብይ ሳሙኤል ሳሙኤል ሳሙኤል ተብሎ ተጠራ
/44/ የመጀመሪያዎችን 2 የእስራኤል ነገሥታት /ሳዖልንና
ዳዊትን/ የቀባው ታላቁ ነብይ ማን ይባላል?
ሳሙኤል፤ የስሙ ትርጉም እግዚአብሔር ሰማኝ ማለት ነው።
/45/ ለመጥምቁ ዮሐንስ እናትና አባቱ ዘካርያስና ኤልሳቤት
ከተባሉ ለሳሙኤል ማን ይባላሉ? ፍንጭ 1ኛ ሳሙ [1:1]
ሕልቃና እና ሐና

ይቀጥላል!

ይቀላቀሉ Join @tewahedo_bete
@tewahedo_bete