Get Mystery Box with random crypto!

Temarilink

የቴሌግራም ቻናል አርማ temarilink — Temarilink T
የቴሌግራም ቻናል አርማ temarilink — Temarilink
የሰርጥ አድራሻ: @temarilink
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12
የሰርጥ መግለጫ

በኢትዮጵያ ያሉ የትምህርት ተቋማትን፣ ተማሪዎችን፣ መምህራንንና ባለሙያዎችን ባንድ ቦታ የሚያገኙበት-Chat, profile,friend,follow,post,like,comment,videos,Study materials,jobs,forums.
https://TemariLink.com
advertainment - for advert

0936290305

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-10-05 21:20:17
#ሰሜንሸዋ

በሰሜን ሸዋ ዞን በአንኮበር፣ ጣርማበር፣ ቀወት እና በረኸት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ መከሰቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

እስካሁን 1 ሺህ 21 ሔክታር የማሽላ ሰብል ላይ ጢንዝዛ የተከሰተ ሲሆን÷ 966 ሔክታሩን በባህላዊ መንገድ ቀሪውን 55 ሔክታር ደግሞ በኬሚካል የመከላከል ሥራ መሠራቱ ተገልጿል፡፡

የቀበሌና የወረዳ ባለሙያዎች ጢንዚዛው በሰብሉ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ÷ በባህላዊ ዘዴ በመልቀም፣ ማሽላውን በማወዛወዝና ጭስ በማጨስ እንዲሁም በኬሚካል የመከላከል ሥራ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ጢንዚዛው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ እንደሚችል ትንበያ የተጠቆመ ሲሆን ወደ አጎራባች ወረዳዎች እንዳይዛመት ሁሉም አርሶአደርና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያ የመከላከል ሥራው ላይ እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል፡፡(FBC)

@TemariLink
@TemariLink
1.0K viewsedited  18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 22:28:25 Do you need scholarship?
432 views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 12:04:20
#ሰሜንሸዋ

በሰሜን ሸዋ ዞን በአንኮበር፣ ጣርማበር፣ ቀወት እና በረኸት ወረዳዎች የማሽላ ጢንዚዛ መከሰቱን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።

እስካሁን 1 ሺህ 21 ሔክታር የማሽላ ሰብል ላይ ጢንዝዛ የተከሰተ ሲሆን÷ 966 ሔክታሩን በባህላዊ መንገድ ቀሪውን 55 ሔክታር ደግሞ በኬሚካል የመከላከል ሥራ መሠራቱ ተገልጿል፡፡

የቀበሌና የወረዳ ባለሙያዎች ጢንዚዛው በሰብሉ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ÷ በባህላዊ ዘዴ በመልቀም፣ ማሽላውን በማወዛወዝና ጭስ በማጨስ እንዲሁም በኬሚካል የመከላከል ሥራ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ጢንዚዛው ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ እንደሚችል ትንበያ የተጠቆመ ሲሆን ወደ አጎራባች ወረዳዎች እንዳይዛመት ሁሉም አርሶአደርና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያ የመከላከል ሥራው ላይ እንዲረባረብ ጥሪ ቀርቧል፡፡(FBC)

@TemariLink
822 viewsedited  09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 11:58:58
#ETHIOPIA

ዛሬ የኢትዮጵያ ሳይንስ ሙዚየም በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተመርቆ ተከፍቷል።

ከሙዚየሙ ምርቃት ባለፈ ጠቅላይ ሚስትሩ የቴክኖሎጂ ዐውደ ርእይ አስጀምረዋል።

በተጨማሪም #የመጀመሪያው የፓን አፍሪካን አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኮንፈረንስን ከፍተዋል።

አጭር መረጃ ስለ ኢትዮጵያ የሳይንስ ሙዚየም ፦

- በ6.78 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ሙዚየሙ ሁለት ግዙፍ ህንጻዎች አሉት።

- ትልቁ ህንጻ ከ15 ሺህ ሜትር ካሬ በሚበልጥ መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን አጠቃላይ ስፋቱ 132 ሜትር ያህል ነው።

- በሙዚየሙ ውስጥ ቋሚ እና ጊዜያዊ አውደ ርዕይ ማሳያዎች አሉት።

- ሙዚየሙ ሳይንስ ጥበባዊ በሆነ መንገድ የሚገለጽበት ጥበብም ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የሚታይበት ነው።

- ከተፈጥሮ ስርዓት ጋር ተስማሚ ሆኖ የተገነባው ሙዚየሙ ከጸሐይ ብርሀን የኤኤሌክትሪክ ሀይል የሚያገኝ ሲሆን የሙዚየሙ ውጫዊ ክፍል የቀለበት እና የጉልላት ቅርጽ እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ነው፡፡

ፎቶ ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት እና Zaho Zhiyuan (በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር)

@TemariLink
@TemariLink
668 viewsedited  08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 09:13:50
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሰላም እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ፌደራል ፖሊስ ገልጿል።

ፌደራል ፖሊስ ከሁሉም ክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽኖች ጋር በመቀናጀት ብሔራዊ ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል።

ፈተናው ከማንኛውም የፀጥታ ችግር ነፃ ሆኖ ተፈታኞች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው መፈተን እንዲችሉ የፀጥታ መዋቅሩ ፈተናውን አጅቦ ለማጓጓዝ እና ጠንካራ ፍተሻዎችን ለማድረግ በቂ ዝግጅት ማድረጉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገልጸዋል።

@TemariLink
937 views06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 09:13:14
#AmharaRegion

በአማራ ክልል የ12ኛ ክፍል ፈተና በ10 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በሚገኙ 31 ማዕከላት ይሰጣል፡፡

ፈተናው ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

በክልሉ ሁሉም የመፈተኛ ተቋማት እና ማዕከላት በቂ የጸጥታ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ምክትል ኮሚሽነር እንየው ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ ወረዳን ማዕከል አድርጎ ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተቀመጠው ጊዜ ለማድረስ በቂ የትራንስፖርት አገልግሎት ዝግጅት ማድረጉን የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ውቤ አጥናፉ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች የወረዳ ትራንስፖርት ቢሮ በሚያወጣው መርሃ ግብር መሰረት በጊዜ እየተገኙ እንዲስተናገዱ ጠይቀዋል፡፡

ሀገራዊ ግዴታቸውን በአግባቡና በሀላፊነት የማይወጡ የትራንስፖርት ማህበራትና ባለሀብቶች በትራንስፖርት መመሪያ እና በሕግ ይጠየቃሉ ብለዋል፡፡

ተማሪዎች በሚጓጓዙባቸው ቀናት መደበኛ ትራንስፖርት ስለማይኖር ሕዝቡ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንዲተባበር ጥሪ አድርገዋል፡፡

ምንጭ፦ አሚኮ

More : @TemariLink
721 viewsedited  06:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 09:11:23
የአልሻባብ መስራች የነበረው አብዱላሂ ናድር ተገደለ!!

ከአልሻባብ መስራቾች አንዱ የነበረው አብዱላሂ ናድር መገደሉን የሶማያ መንግስት አስታወቀ።

ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ አልሻባብን ለማጥፋት መጠነ ሰፊ ጥቃት የከፈተች ሲሆን የሽብር ቡድኑ መስራች የነበረው አብዱላሂ ናድር መግደሏን አስታውቃለች። የሶማሊያ መንግስት የጸጥታ ሀይል እየወሰደ ባለው ጥቃት ከዚህ በፊት በሽብር ቡድኑ ይዞታ ስር የነበሩ ቦታዎችን አስለቅቋል ተብሏል።

አኣሻባብም በተለይም የአጥፍቶ ማጥፋት ጥቃቱን የቀጠለ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ብቻ ባደረሳቸው ሁለት ጥቃቶች የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል።ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚገለጸው አልሻባብ መስራች የነበረው አብዱላሂ ናድር ከዚህ በፊት የሽብር ቡድኑን ሲመራ የነበረው እና በቅርቡ የተገደለው አህመድ ድርዬን ለመተካት በሂደት ላይ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።

የሶማሊያ የኢንፎርሜሽን ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ የአብዱላሂ ናድር መገደል አልሻባብ ከሶማሊያውያን ላይ እንደ እሾህ ተነቅሎ እንዲወጣ ያደርገዋል ብሏል።ይህ የሽብር ቡድኑ አመራር እንዲገደል ሶማሊ ህዝብ እና ለዓለም አቀፍ ወዳጆች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናውን የሶማሊያ መንግስት አቅርቧል።አልሻባብ ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን እንደገደለ የገለጸው የሶማሊያ መንግስት፤ ዓላማው ሶማሊያን እና ጎረቤት ሀገራትን ማወክ እንደነበርም ተገልጿል።

@TemariLink
736 viewsedited  06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 23:24:27
የሰው ዓይን በማጥፋት የ8 ሺህ ብር የሞባይል ስልክ የወሰደው ግለሰብ ...

ተከሳሽ ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ላይ በቦሌ ክ/ከ/ ወረዳ 09 ልዩ ቦታው ቀጠና 01 አካባቢ የግል ተበዳይ ወደ ቤቱ በመሄድ ላይ እያለ መንገድ ላይ ጠብቆ ጭንቅላቱን በድንጋይ በበምታትና በጩቤ ግራ አይኑ በመውጋት የግራ ዓይኑ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ በማድረግ እንዳይከላከል ጥቃት ያደርስበታል።

ከዚያም በኋላ የግል ተበዳይ ይዞት የነበረውን ሳምሰንግ ሞባይል የዋጋ ግምቱ 8,000 ብር የሚገመት ቀምቶ ይዞ በመሮጥ ላይ እያለ በአካባቢው ሰዎች ተይዞ በፈፀመው ከባድ የውንብድና ወንጀል ይከሰሳል፡፡

ይሁን እንጂ ተከሳሽ ” እኔ ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፋተኛም አይደለሁም ”ሲል ክዶ የተከራከረ ሲሆን ዐቃቤ ህግ የምስክሮች ቃል እና የሰነድ ማስረጃዎችን በበቂ ሁኔታ ለችሎቱ በማስረዳቱ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት በተከሳሽ ላይ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት ተከሳሽ ከዚህ በፊት የጥፋተኝነት ሪከርድ የሌለበት߹ መሆኑን ጨምሮ ሰባት የቅጣት ማቅለያዎች ተይዘውለት በ12 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የፍትህ ሚንስቴር መረጃ ያመላክታል።

@TemariLink
677 viewsedited  20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 23:22:10
ለጤና አደገኛ የሆነ ኬሚካል ከጤፍ ጋር ተደባልቆ ተያዘ።

መስከረም 19 መነሻውን አማሮ ኬሌ አድርጎ በኮንሶ በኩል ወደ አርባምንጭ በህገ ወጥ መንገድ አደገኛ ኬሚካል ከጤፍ ጋር ደባልቆ ጭኖ ሲያልፍ የነበረው የሰሌዳ ቁጥር 47327 ኦሮ አይሱዙ መኪና መያዙን የካራት ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

መኪናው ጤፍ ብቻ  የጫነ በማስመሰል በህገ ወጥ መንገድ "ፕሮምፖክሱር "የተባለ አደገኛ ኬሚካልን ጭኖ በኮንሶ በኩል ወደ አርባምንጭ ለማለፍ ሲሞክር በተደረገ ፍተሻ ኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ከምሽቱ 1 ሰአት ተኩል አከባ መያዙን ነው የከተማው አስተዳደር ፖሊስ  አዛዥ ምክትል እንስፔክቴር ጌታቸው ጉደታ የገለጹት።

ከ96ቱ ኩውንታሎች ውስጥ በ40 ጤፍ ኩውንታሎቹ በ40 ፌስታሎች ውስጥ በየፌስታል ተቋጥረው የነበሩት አደገኛ ከረሚካሎቹ ባጠቃላይ  200 ኪሎ ግራም እንደሆነ የገለጹት የፖሊስ አዛዡ የተጠረጠሩት 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ጉዳያቸው በህግ አግባቦት እንደሚጣራ አስረድተዋል።

ጤፍና አደገኛ ኬሚካል በአንድ ላይ ደባልቆ መጫን ለጤና አደገኛ መሆኑን ገልጸው አንድ ሰው በህጋዊ መንገድ እንደዚህ አደገኛ ኬሚካል ለመጫን ቢፈልግ እንኳ ፍጹም ለምግብነት ከሚውሉ ነገሮች  ነጻ መሆን እንደሚያስፈልገው የዞኑ ጤና መምሪያ ጤናና ጤና ነክ እንስፔክሽን ባለሙያ አቶ ካላኖ ኩሴ ተናግረዋል።

@TemariLink
573 viewsedited  20:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-03 23:19:51
166 የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ!!


በመስቀል የደመራ ሥነስርዓት እንዲሁም በአዲስ አበባ እና በቢሾፍቱ በተከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ የሽብር ተግባር በመፈጸም ሀገራዊ ቀውስ እንዲፈጠር በህቡዕ ሲያሴሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ለመገናኛ ብዙኃን በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ አሸባሪ ቡድኖች በመስከረም ወር በሚከበሩት የአደባባይ በዓላት ላይ ሁከትና ብጥብጥ በመቀስቀስ ሀገራዊ ይዘት ወዳለው ቀውስ እንዲሸጋገር በህቡዕ ሴራ ሲጠነስሱ ነበር፡፡
ይሁንና የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል የአደባባይ በዓላቱ ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ባደረገው ጠንካራ ቅድመ ዝግጅትና ምስጢራዊ ክትትል ሴራውን ከውጥኑ ማክሸፍ ተችሏል፡፡

በዚህም 166 የህወሓት፣ የሸኔ፣ የአይ ኤስ እንዲሁም የኢመደበኛ አደረጃጀት አባላት በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጓል፡፡

የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በሽብር ቡድኖች እና በተጠርጣሪ ግለሰቦች ህቡዕ እንቅስቃሴና የግንኙነት መረብ ላይ ሲያደርግ በነበረው ምስጢራዊ ክትትልም የአደባባይ በዓላቱን ወደ ቀውስ ለመቀየር ለታቀደው እኩይ ተልዕኮ መፈጸሚያ የሚሆኑ የቡድንና የነፍስ ወከፍ የጦር መሣሪያዎች፣ ተቀጣጣይ ፈንጂዎች፣ ቦምቦች እና በርካታ ጥይቶችን መያዙን ገልጿል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከአይ ኤስ የሽብር ቡድን ጋር በጋራ እንደሚሠሩና ከአሸባሪው ህወሓት ተልዕኮ ተቀብለው ሲንቀሳቀሱ እንደ ነበር የሚያስረዱ የሰነድ ማስረጃዎችም ተገኝተዋል ብሏል፡፡ በዓላቱ ሰላማዊ ድባብ የሰፈነባቸው እንዲሆኑ መላው ኅብረተሰብ ላሳየው ከፍተኛ ተሳትፎም ልባዊ ምስጋውን አቅርቧል።
     @TemariLink
493 viewsedited  20:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ