Get Mystery Box with random crypto!

TeleDoc home based health care service

የቴሌግራም ቻናል አርማ teledocc — TeleDoc home based health care service T
የቴሌግራም ቻናል አርማ teledocc — TeleDoc home based health care service
የሰርጥ አድራሻ: @teledocc
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 253
የሰርጥ መግለጫ

Home Care Health Service
Call us 6311 or 0913003395

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-07 11:17:08
t.me/teledocc
565 views08:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-02 21:31:34
649 views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-30 10:46:33
742 views07:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-29 08:37:47
#rent #sale #teledoc
633 views05:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 11:55:51
An accurate reading of a person's blood pressure is a vital tool in managing illness. #sale #homecare #nursingcare #physiotherapist
596 views08:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-28 11:38:20
#Sale #rent #medicalequipment
531 views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 11:05:47
t.me/teledocc
823 views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-09 11:05:40 የሆድ ድርቀት

የሕመሙ ምልክቶች፡-
•የሆድ መነፋት
•የምግብ ፍላጎት ማጣት
•መጥፎ የአፍ ጠረን
•የራስ ምታት
•መጨናነቅ
•ብጉር
መንስኤ፡
•ፋይበር ያነስው የአመጋገብ ስርአት
•ውሀ አለመጠጣት
•ሰአቱን ያልጠበቀ የመፀዳጃ አጠቃቀም
•የሰውነት እንቅስቃሴ አለማድረግ

ድርቀትን በቤት ውስጥ እንዴት ማከም ይቻላል
1.የሎሚ ጁስን ጠዋት በባዶ ሆድ እና ማታ መጠጣት
2.ግማሽ የሻይ ማንኪያ ቁንዶበርበሬ ከ 1 ብርጭቆ የሞቀ ውሀ ጋር አደባልቆ
መጠጣት
3.ቁልቋል/በለስን ከ 1 ብርጭቆ ውሀና ከ 1 የሻይ ማንኪያ ማር ጋር በመደባለቅ
ማታ ማታ መጠጣት
4.ሁለት የሻይ ማንኪያ የጉሎ ዘይትን በባዶ ሆድ መጠጣት
5.ሁለት የሻይ ማንኪያ ማር በቀን 3 ጊዜ መውሠድ
6.የወይን ፍሬን መመገብ
7.ጎመን፣ሠላጣ እና ቆስጣን አዘውትሮ መመገብ
8.የሽንኮራ አገዳን መመገብ
9.ተልባን መመገብ
10.ዘቢብን መመገብ
11.በቀን ከ8-10ብርጭቆ ንፁህ ውሃ መጠጣት
12.የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ
ለሌሎች አካፍሉት t.me/teledocc
714 viewsedited  08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 12:45:25
የቤት ለቤት ህክምና
638 viewsedited  09:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-03 12:20:13 በእርግዝናሽ ወቅት ወሲብ መፈጸም ያለብሽ መቼ ነዉ?? ከወሊድስ በኋላ መቼ ወሲብ መጀመር ትችያለሽ??
*****
አንዳንድ ንዶች የሴቷ ርገዝ በወሲብ ህይወታቸው ላይ ምንም አይነት ለውጥ ባይፈጥርባቸውም በአብዛኛው እርግዝና የወንዱንም ሆነ የሴቷን የወሲብ ፍላጎት ይቀይረዋል። የተወሰኑ ጥንዶች እርግዝና የተሻለ የወሲብ ህይወት እንደሰጣቸው ሲመሰክሩ ሌሎች ከባድ ጊዜ ሊያሳልፉ ይችላሉ። ሆኖም በተለይ ከወሊድ በኋላ ብዙዎች ረዘም ያለ እረፍት ይወስዳሉ።

በዚህ ወቅት በፊት የነበራችሁ ጥሩ የወሲብ ህይወት በጣም እንዳይቀየር ዋናው መፍትሄ ስለምትፈልጉት እና ስለሚሰማችሁ ነገር በግልፅ መወያየት ነው። ሁለታችሁንም የሚያረካ መፍትሄ ፈልጉ። ከዚህ በታች ብዙ ጥንዶች ስለ ወሲብ የሚያሳስቧቸው ነገሮች ተዘርዝረዋል። በሃገራችን ባህል ስለነዚህ ጉዳዮች በግልጽ ማውራት ሊከብድ ይችላል። ይህ ከሆነ ከባለቤትሽ/ባለቤትህ ጋር በመሆን ይህንን ፅሁፍ ማንበብ ነገሮችን ሊያቀል ይችላል።

የግብረ ሥጋ ግንኙነት በእርግዝና ወቅት በእናቲቱ ወይም በልጁ ላይ ችግር ይፈጥር ይሆን?
ይህ ጥያቄ ብዙዎችን የሚያሳስብ ነው። በአጠቃላይ መልሱም በፍፁም ነው። ሴቷ በወሲብ ወቅት በምትረካበት ጊዜ በማህፀን ላይ የመኮማተር (የመጫን) ስሜት ሊፈጥር ይችላል። የእምስ ግርግዳ ስለሚሳሳ በግንኙነት ወቅት በትንሹ ሊደማ ይችላል። እኚህ ሁኔታዎች ባይመቹም በብዛት አደጋ የላቸውም። ለመጀመሪያ ጊዜ የደማሽ እንደሆነ ወይም አደማምሽ ካሳሰበሽ ሃኪምሽን አማክሪ። የደማሽው መጠኑ ብዙ ከሆነ ግን በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ሂጂ።

በባለቤትሽ ብልትና በልጅሽ መካከል ብዙ ርቀት ስላለ በተጨማሪም ልጅሽ በማህፀን ግርግዳ፣ እንዲሁም የማህፀን በሩን ዘግቶ ባክቴሪያና የውንዱ የዘር ህዋስ እንዳይገባ በያዘው ዝልግልግ መድፈኛ ከዚያም አልፎ በክርታሱና ውስጡ ባለው የሽርት ውኃ ተከልሎ ስለሚገኝ ወሲብ ልጅሽ ላይ የሚፈጥርበት ችግር አይኖርም።

ጥሩ ግንኙነት ስለመፈፀም

ብዙ እናቶች በእርግዝና ምክንያት በሰውናታቸው ውስጥ ባሉ ሆርሞኖች አማካኝነት እና የብልት ግርግዳዎች ስለሚለሰልሱ በወሲብ ወቅት በቀላሉ ለመራስ ይችላሉ። ስለዚህም በዚህ ጊዜ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ማድረግ ይመቻቸዋል። በጣም ጥሩው ጊዜ በተለይ የመጀመሪያው ሶስት ወር (ብዙ ማቅለሽለሽ የሚሰማበት) ካለፈ በኋላ ፅንሱ ትልቅ ሆኖ ሆድ በጣም እስከሚገፋ በመኃል ያለው ነው።

ሆድሽ ወደፊት ሲገፋስ?

ሆድሽ በሚገፋበት ጊዜ ለወሲብ የሚመች አኳኋን ማግኘት ከባድ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ዋናው ነገር የሚመቻችሁን አይነት መንገድ እስክታገኙ መሞከር ነው። ሴቷ በጎኗ ብትተኛ ወይም በጉልበቷ ብትንበረከክ የበለጠ ሊመቻችሁ ይችላል።

ወደ እርግዝና መጨረሻ

በዚህ ጊዜ የበለጠ ጥንቃቄ ማድረግ ያሻል። ጉልብት የበዛው ግንኙነት ማድረግ አይመከርም። ቢሆንም አንደኛው ወገን ወሲብ ማድረግ ፈልጎ ሊላኛው ወገን ባይፈልግ ሌሎች ፍቅርን ለመግለፅ ሊደረጉ የሚችሉ ነገሮች አሉና መረሳት የለባቸውም።

ከወሊድ በኋላ
ወሊድ በእያንዳንዷ እናት ላይ የሚፈጥረው ስሜት ይለያያል። ቀላል ወሊድ ከነበረ በቶሎ ወደነበረው ሁኔታ ለመመለስ ይቀላታል። ከባድ ወሊድ ያሳለፈች እናት ደግም አእሮዋም ሆነ ሰውነቷ ዝግጁ እስኪሆን ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድባት ይችላል።

በወሊድ ወቅት የማህፀን መውጫ እና አካባቢው ሊቆስልና ህመም ሊሰማ ይችላል። ሆኖም ይሄ የሚድን ሁኔታ ነውና ሊያሳስብሽ አይገባም። በሰውነትሽ ውስጥ ያለው የኤስትሮጅን መጠንም ይቀንሳል። በዚህ ምክንያትም እንደበፊቱ እርጥበት ላይሰማሽ ይችላል፤ ነገር ግን ይሄ የተለመደ ነው። ሊረዳሽ የሚችል ቅባት በፋርማሲዎች ስለሚገኝ ሐኪምሽን ማማከር ትችያለሽ።

ከወሊድ በኋላ ግንኙነት ማድረግ የሚቻለው መቼ ነው?
ከአራት እስከ ስድስት ሳምንት በኋላ ሁኔታዎች በፊት እንደነበሩት ለመመለስ ቢችሉም ብዙ ጥንዶች የበለጠ ጊዜ ይወስድባቸዋል።፡አዲስ ወላጆች እንደመሆናቸው በቤታቸው ለመጣው እንግዳ ህይወት ብዙ ትኩረት ስለሚሰጡ ላያስባቸውም ይችላል።

አብሮ በመተኛት እና በመጨዋወት ቀስ በቀስ ድሮ ወደነበረው ፍቅራቸው በሂደት መመለስ ይችላሉ። ይህ እንደገና ለመላመድ እድል ይሰጣቸዋል። ስለስሜታቸው በግልፅ መወያየት በጣም ጥሩ ነው። በተጨማሪ ስለዚህ ጉዳይ ሐኪምን ማማከር ይቻላል። t.me/teledocc
593 views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ