Get Mystery Box with random crypto!

እግራቸው ለማይንቀሳቀስ ሰዎች እንዲራመዱ የረዳው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት የሥርዓተ ነር | ሁለገብ የቴክ ኢንፎ/hulgeb tech info®

እግራቸው ለማይንቀሳቀስ ሰዎች እንዲራመዱ የረዳው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት

የሥርዓተ ነርቭ አለመታዘዝ እክል ገጥሟቸው መራመድ የማይችሉ ሰዎች እጅግ ዘመናዊ በተባለ ሕብለ ሰረሰር ላይ በሚገጠም አነስተኛ መሣሪያ አማካኝነት መራመድ፣ መዋኘት እና ሳይክል መንዳት መቻላቸው ተገለፀ፡፡

ግለሰቦቹ ሆድ ውስጥ በሚቀበር ተጨማሪ አጋዥ መሣሪያ ላይ የተጫነው የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሥርዓት ሕብለ ሰረሰር ላይ የሚገጠመውን አነስተኛ መሣሪያ ይቆጣጠራል፡፡

በዚህም የእግር ጡንቻዎችን የሚያዘው የሕብለ ሰረሰር አካባቢን የነርቭ ሕዋሶች በማነቃቃት እና ወደስራ እንዲገቡ በማስቻል የእግር ጡንቻዎች መታዘዝ እንዲችሉ አድርጓል ሲል ዴይሊ ሜይል አስነብቧል፡፡

በሞተር ሳይክል አደጋ ምክንያት ከአራት ዓመታት በላይ በተሽከርካሪ ወንበር እንዲያሳልፍ ተገዶ ለነበረ ግለሰብ ቴክኖሎጂው ዳግም የመራመድ እድልን አጎናፅፎታል፡፡

የስዊዘርላንዱ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውጤት የሆነው ይህ ቴክኖሎጂ ለታማሚዎቹ ከተገጠመ ከአንድ ቀን በኋላ ግለሰቦቹ መቆም፣ መራመድ፣ ሳይክል መንዳት፣ መዋኘት እና አካላቸውን መቆጣጠር መቻላቸው ተመላክቷል፡፡



EIIA