Get Mystery Box with random crypto!

ለተሻለ ውጤት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የምትጠቀመው አነስተኛ ካሜራ የዘመኑ ካሜራዎች ከሚያነሱት | ሁለገብ የቴክ ኢንፎ/hulgeb tech info®

ለተሻለ ውጤት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን የምትጠቀመው አነስተኛ ካሜራ

የዘመኑ ካሜራዎች ከሚያነሱት የተሻለ ምስልን ማስቀረት የምትችል የጨው ቅንጣት መጠን ያላት ካሜራ በፕሪንስተን እና ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እውን መሆኗ ተነገረ፡፡

ሌሎች የካሜራዋ ቴክኖሎጂዎች ከብርሃን ጋር በሚኖራቸው መስተጋብር የሚፈጠረውን ሂደት በመጠቀም የማሽን ለርኒንግ ስልተቀመሮች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ምስሎችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ መዋላቸው ተመላክቷል፡፡

ባለ ሙሉ ቀለም ምስሎችን ማስቀረት የምትችለው ካሜራ ለሕክምና ከሚውሉ ሮቦቶች ጋር በመጣመር ለአገልግሎቱ ተጨማሪ ግብዓት እንደምትሆን ዘኢንዲፔንደንት ዘግቧል፡፡

መደበኛ ካሜራዎች ከሚሰሩበት በተለየ መልኩ የኮምፒዩተር ቺፕ የሚዘጋጅበት የቴክኖሎጂ ሂደት ካሜራዋን ለመስራት ውሏል፡፡

ፈጠራው በስማርት ስልኮች ላይ የሚታየውን ከአንድ በላይ ካሜራ የማካተት ፍላጎት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ምስሎችን መቅረጽ በሚችል አንድ ካሜራ የመተካት ተጨማሪ ዓላማ አካቷል፡፡


EIIA