Get Mystery Box with random crypto!

《ማድረግ የሌለብዎ ነገር》 --------------~------------- ... ☞ የባትሪ ቻርጅ | Techopia Tube

《ማድረግ የሌለብዎ ነገር》
--------------~-------------
...
☞ የባትሪ ቻርጅ በጣም ሎው ሲሆን፣ ወይም ሲቀንስ (20% በታች) ስልኩን ያለመጠቀም ልማድ ይኑርዎ፡፡ ምክንያቱም ቻርጅ ሲቀንስ የሚረጨው የጨረር መጠን ይጨምራል።
...
☞ ሞባይል ተጠቃሚ ከሆኑ ሲነጋገሩ ወደ ጆሮዎ እና ጭንቅላትዎ እጅግ በጣም አያስጠጉ ፡፡ ከቻሉ ቢያንስ ከ5 ሳንቲ ሜትር በላይ ራቅ በማድረግ ኤሌክትሮማግኔቲክ ራዲየሽን ከተባለው አደገኛ ጨረር ራስዎን ይጠብቁ፡፡
...
☞ የሞባይል ስልኮን # ታቅፈው አይተኙ፡፡ በእንቅልፍ ወቅት ባትሪውን ያጥፉ ወይም ከአልጋዎ 1.8 ሜትር በማራቅ ማታ ሲደወል ከሚለቀቀው ኤሌክትሮማግኔትክ ራስዎን በተቻለ መጠን አያጋልጡ፡፡
...
☞ ነፍሰጡር እናቶች ሞባይል ሲይዙና ሲጠቀሙ ይጠንቀቁ፡፡ የጽንሱ ሕዋሳት ለኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽን እጅግ በጣም አለርጂክ ናቸው፡፡ ስለዚህ አቀማመጡንም ሆነ አጠቃቀሙን ከጽንሱ ራቅ ባለ ሥፍራ ይሁን፡፡ አላስፈላጊ አጠቃቀምን ለምሳሌ ረጅም ሰዓት ማውራት እና ቶሎ ቶሎ መደዋወል መቀነስ አለበዎት፡፡
...
☞ ብረት ነክ ነገሮች ባሉበት ሥፍራ ሞባይል መጠቀም አያዘውትሩ፡፡ ብረት የኤሌክትሮማግኔቲክ ራድየሽኑን ወይም የጨረሩን ጉልበት ያጠነክረዋል፡፡ ስለዚህ መኪና ውስጥ፣ አውሮፕላን ውስጥ፣ ሊፍት ውስጥ፣ ባቡር ውስጥ፣ ብረት አጥር ወይም በር አካባቢ፣ የብረታብረት ወርክሾፕ ውስጥ፣ ጋራዥ ውስጥ ወዘተ አስቸኳይ ወይም አጣዳፊ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር በተቻለ መጠን ሞባይል አይጠቀሙ፡፡ የሚጠቀሙም ከሆነ ለአጭር ደቂቃ ብቻ ይሁን፡፡
...
☞ በተለይ! በተለይ!!! ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ወጣት ልጆች ሞባይልን ባይጠቀሙ ወይም ባያዘወትሩ ይሻላል፡ ጨረሩ የጭንቅላት ሴሎቻቸውን እጅግ በጣም ይጎዳዋል፤ ለካንሰርም ያጋልጣቸዋል፡፡
...
☞ በበለጸጉት አገሮች ከ15 ዓመት በታች ባሉ ልጆች ውስጥ ለሚከሰተው ሞት በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ምክንያት የጭንቅላት እጢ ነው፡፡ ወላጆች ይህንን እውነታ በመገንዘብ አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር ሞባይል መጠቀምን በመደበኛነት ልጆች አዘውትረው እንዳይለምዱት ማድረግ ይገባቸዋል፡፡
...
☞ አዲስ የተወለዱ ጨቅላ ሕፃናት ዕድሜያቸው ከ2 ዓመት በታች የሆኑት ሁሉ የጭንቅላታቸው ራስ ቅል በጣም ስስ ነው፡፡ ስለዚህ ጨረሩ ሙሉ ለሙሉ በስሱ አጥንት በኩል ወደ አንጎላቸው ሰርፆ ስለሚገባ ጥንቃቄ አድርጉ፡፡
...
☞ ጨቅላ ሕፃናትና ትናንሽ ልጆች አጠገብ ሁነው ሞባይል አዘውትረው የሚነጋገሩ ከሆነ ለአደጋ ስለሚያጋልጣቸው አጠቃቀሙንና አቀማመጡ ከእነርሱ ራቅ ባለ ሁኔታ ላይ ያድርጉት፡፡

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
━━━━━━━━━━━━━━━
: @techopiatube2
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬ Share