Get Mystery Box with random crypto!

በቴሌግራም ሚስጥራዊ መልዕክቶች እንዴት መለዋወጥ እንችላለን? ቴሌግራም አፕሊኬሽን ስልክ ከማስደወ | Techopia Tube

በቴሌግራም ሚስጥራዊ መልዕክቶች እንዴት መለዋወጥ እንችላለን?

ቴሌግራም አፕሊኬሽን ስልክ ከማስደወል በተጨማሪ መልዕክት፤ፎቶ፤ቪዲዮ፤ዶክመንቶች መለዋወጥ የሚያስችል በጣም ምቹ ሲሆን በአሁን ሰዓት ከ550 ሚሊዮን በላይ ወርሃዊ ተጠቃሚዎች ያፈራ ምርጥ አፕሊኬሽን ነው፡፡
ቴሌግራም ብዙ የማናውቃቸው ሚስጥራዊ አገልግሎቶች አሉት፡፡ ከነዚህም መካከል ሰዎች ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ መልዕክት መለዋወጥ ያስችላል፡፡ ይህ አገልግሎት አንዳንድ ሰዎች የሚለዋወጣቸው መልዕክቶች ከፍተኛ ሚስጥራዊነት የሚፈልጉ በመሆኑ ቴሌግራም እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች መልዕክታቸውን ሳይሳቀቁ መለዋወጥ እንዲችሉ ያስችላል፡፡
ይህ Secret chats ተብሎ የሚጠራው የቴሌግራም አገልግሎት ስትጠቀሙ
1ኛ፡- መልዕክት(ቻት) ስትለዋወጡ መልዕክታችሁን ከናንተ እና ከላካችሁለት ሰው በስተቀር ማንም ሰው ማየት አይችልም፡፡
2ኛ፡ በዚህ የቴሌግራም አገልግሎት አማካኝነት የላካችሁት መልዕክት የላካችሁለት ሰው ወደ ሌላ ሰው መልዕክቱን ማስተላለፍ አይችልም፡፡ በተጨማሪም የላካችሁት መልዕክት እናንተ ጋር ስታጠፉት የላካችሁለት ሰው ጋርም እንዲጠፋ ያደርጋል፡፡
ይህ ብቻ አይደለም Secret chats ላይ በጣም ሚስጥራዊ መረጃ ከላካችሁ የላካችሁለት ሰው የላካችሁለት ዶክመንት ካየው በሁዋላ መልእክቱ ከነ ዶክመንቱ እንዲጠፋ ማድረግ ይቻላል፡፡
ለምሳሌ አንድ ፎቶ ላካችሁ እንበል፡፡ፎቶ የላካችሁለት ሰው ፎቶውን እንዳየው ከላካችሁለት ሰው ስልክ ላይ እንዲጠፋ ማድረግ ይቻላል፡፡ ይህ አገልግሎት self-destruct messages
እስቲ እነዚህ የቴሌግራም አገልግሎቶች ማለትም Secret chats እና self-destruct messages እንዴት መጠቀም እንደምንችል በስቴፕ ላሳያችሁ፡፡
Secret chats ለመጠቀም የሚከተሉትን ስቴፖችን በመከተል መጠቀም ትችላላችሁ
1. ቴሌግራም አፕሊኬሽን ትከፍታላችሁ
2. ሚስጥራዊ መረጃ መለዋወጥ የምትፈልጉትን ሰው ከኮንታክት ላይ መምረጥ
3. የመረጣችሁት ሰው ፕሮፋይሉ ውስጥ መግባት
4. የሰውየው ፕሮፋይል ላይ ሆናችሁ ከላይ በቀኝ በኩል 3 ነጥቦች አሉ፤ እነሱን ክሊክ ስታደርጉ ከሚመጥት ምርጫዎች Start Secret Chat የሚለውን መምረጥ
5. በቃ ከዛ ሰው ጋር ሚስጥራዊ መልዕክቶችን መለዋወጥ ጥችላላችሁ

self-destruct messages ወይም የምትልኩት መልዕክት የላካችሁለት ሰው ካየው በሁዋላ ከስልኩ እንዲጠፋ ለማድረግ
1. ከላይ ከ 1 እስከ 4 ስቴፖችን በመከተል የSecret chats አገልግሎት መጀመር
2. ሚስጥራዊ መልዕክት የምትልኩለት ሰው መልዕክት ለመላክ ስትፈልጉ መልዕክት የምንፅፍበት ቦታ ሆናችሁ ከላይ በቀኝ በኩል 3 ነጠብጣቦችን ክሊክ ማድረግ
3. 3ቱ ነጥብጣቦች ክሊክ ስታደርጉ ከሚመጡት አማራጮች መካከልል set self-destruct timer የሚለውን መምረጥ
4. ከዛ የግዜ ሰሌዳ ይመጣል ከሰሌዳው ላይ ብትፈልጉ አንድ ደቂቃ ወይም አንድ ቀን ወይም አንድ ሳምንት ወይም የፈለጋችሁትን ግዜ ስጡት እና #Done; የሚለውን መንካት፡፡ በቃ ያስቀመጣችሁት የግዜ ገደብ ሲደርስ የላካችሁት መልዕክት ከላከላችሁለት ሰው ሞባይል ይጠፋል ማለት ነው፡፡

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
━━━━━━━━━━━━━━━
@techopiatube1
@techopiatube2