Get Mystery Box with random crypto!

☞ወር በገባ በ16 ርዕሰ ገዳማውያን የአባ ጳውሊ ወርሀዊ መታሰቢያው ነው፡፡ ☞የአባ ጳውሊ አባታቸው | ጥበብ በእርስው

☞ወር በገባ በ16 ርዕሰ ገዳማውያን የአባ ጳውሊ ወርሀዊ መታሰቢያው ነው፡፡
☞የአባ ጳውሊ አባታቸው የገንዘብ መጠን እንኳን የማያውቁት እጅግ ባለጸጋ
ነበሩ፡፡ አባታቸው ከሞቱ በኃላ ወንድማቸው ጴጥሮስ ንብረታቸውን በትክክል
አላከፍላቸው ሰላል ተጣልተው ወደ ዳኛ ሄዱ፡፡
☞በመንገድ ላይ ሳሉ አንድ ሰው ሞቶ ሊቀብርቱ ሲወስዱት አይተው አባ ጳውሊ
አገኟቸው፡፡ የሞተው ማን እንደሆነም ሲጠይቁ የሞተው ሰው እጅግ ባለጸጋ
እንደነበረ በኃጢአት ውስጥ ሆኖ እንደሞተ ተነገራቸው፡፡
☞ከዚህም በኃላ አባ ጳውሊ የዚህ የኃላፊ ዓለም ገንዘብ ለእኔ ምኔ ነው ?
ብለው ወደ ወንድማቸው ዞረው ወደ ዳኛ መሄዳቸውን ትተው ወደ ቤት
እንዲመለሱ ለመኑት፡፡ የአባታቸውንም የተትረፈረፈ ሀብትና ንብረት
እንደማይፈልጉት ነገሩት፡፡
☞ከወንድማቸው ተደብቀውና ሸሽተው በመውጣት በአንዲት መቃብር ቤት
ገብተው መጸለይ ጀመሩ፡፡ በ4ተኛው ቀናቸው የታዘዘ መልክ መጥቶ ነጥቆ ወስዶ
ከአንድ በረሃ ውስጥ አደረሳቸው፡፡
☞አባ ጳውሊ ወደ አንዲት ኩርፍታ ገብተው ተጋድሎአቸውን ጀመሩ፡፡ በዚያች
ዋሻ ውስጥም የሰው ፊት ሳያዩ በጾም በፀሎት ብቻ ተወስነው 80 ዓመት ኖሩ፡፡
☞ልብሳቸውም ከሰሌን ቅጠል የተሠራ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንደ ነቢዩ ኤልያስ
ቁራን እየላከ ምግባቸውን ይሰጣቸው ነበር፡፡
☞ከዚያ በኃላ ጌታችን የጳውሊን ክብር ይገለጥ ዘንድ መልአኩን ወደ አባ እንጦስ
ዘንድ ላከው፡፡ አባ እንጦስም በበረሃው ውስጥ በታላቅ ተጋድሎ ከኖሩ በኃላ
በበረሃ መኖር የጀመሩት እሳቸው እንደሆኑ በልባቸው ማሰብ ጀምረው ነበር፡፡
☞መልአኩም ተገልጦላቸው እንጦስ ሆይ ከአንተ የሁለት ቀን ጎዳና ርቆ በበረሃ
ውስጥ የሚኖር ሰው አለ፤ የዓለም ሰዎች ከሚረግጥባቸው የእግሩ ጫማዎች
አንደ አንዲቱ ሊሆኑ የማይገባቸው ስለ እርሱም ጸሎት ዓለም ተጠብቆ የሚኖር
ነው እያለ የአባ ጳውሊን ክብር ነገራቸው፡፡
☞አባ እንጦስም የአባ ጳውሊ በዓት ፈልገው አግኝተው ሄደው በብዙ ምልጃ
በሩን ከፍተውላቸው ተገናኝተው ሁለቱም አብረው ከጸለዩ በኃላ ስለ
ተጋድሎአቸው ስለ አኗኗራቸው ተወያዩ፡፡
☞የታዘዘው ቁራ ሌላ ጊዜ የጳውሊን ምግብ የሚያመጣው ግማሽ እንጀራ ነበረ
ዛሬ ግን ሙሉ እንጀራ ሰላመጣለቸው ሁለቱም ቅዱሳን ደስ ተሰኝተው
እግዚአብሔር አመሰገኑ፡፡
☞አባ እንጦንስም ሥጋ ወደሙን ከወዴት እንደሚቀበሉ አባ ጳውሊን
ሲጠይቋቸዎ በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ መልአክ እያመጣ ሥጋ ወደሙን
እንደሚያቀብላቸው ነገሯቸው፡፡
☞ከዚህም በኃላ አባ አንጦስ ይህን አሰኬማ በምድር ላይ ይበዛ እንደሆነ ወይም
አለመብዛቱ ትነግረኝ ዘንድ እሻለሁ አላቸው፡፡ አባ ጳውሊ ወደ ፊት ሰለሚመጡ
መነኮሳት በመጸለይ ወደ ሰማይ ካዩ በኃላ በመጀመሪያ ፈገግ አሉ፡፡ አባ እንጦስ
ምን አየህ ቢላቸው አባ ጳውሊ ነጫጭ ርግቦች በጠፈር መልተው አንተ
እየመራሃቸው ተከትለውህ ሲሄዱ አየሁ አላቸው፡፡
☞ይህስ ምንድነው ቢላቸው እነዚህማ በዚህ ቆብ የምትወልዳቸው ንጹሐን
ጻድቃን ልጆችህ ናቸው፡፡
☞ሁለተኛም አመልክትልኝ አሏቸው፡፡ ጳውሊም ካመለከቱ በኀላ አዝነውና
ተከፍተው ተመለከቷቸው፡፡ ምነው ቢሏቸው በክንፋቸው ጥቁር ተቀላቅሎባቸው
አየሁ አሉ ምንድን ናቸው ቢሏቸው ጽድቅና ኃጢአት እየቀላቀሉ የሚሠሩ ልጆችህ
ናቸው አላቸው፡፡
☞ሦስተኛም አመልክትልኝ አሏቸው አባ ጳውሊ በድንጋጤ ቃላቸውን ከፍ
አድርገው ጮኹ አባ እንጦስም ምንድነው ቢሏቸው አባ ጳውሊ እንዲህ አሉ ነገር
ግን በመጨረሻ ዘመን የሚነሡት እንደ ቁራ ጠቁረው አየሁዋ ምንድናቸው?
ሹመት ፈላጊዎች ፤ገንዘብ የሚወዱ በፍጻሜ ዘመን የሚነሡ ኅጥአን ልጆችህ
ናቸው አሏቸው፡፡
☞ከዚያም አባ እንጦስም አባ ጳውሊ የተሰወረውን ሁሉ በማወቃቸው አደነቁ፡፡
ዳግመኛ አባ ጳውሊ ቆቡ አባ እንጦስን እንግዲህ ይህን ከራስህ ያደረግኸውን
ለእኔ ስጠኝ ላንተ ሌላ ስሠርተህ አድርግ አላቸው፡፡
☞አባ እንጦስም ይህን እንዳልሰጥህ ከባለቤቱ ተቀብያለሁ፡፡ነገር ግን ሥራውን
ለምጄዋለሁ እና ሌላ ሠርቼ ላምጣልት አላቸው፡፡
☞አባ እንጦስም የ2 ሰአት መንገድ ወደ በዓተቸው ሄደው ቆቡን ሠርተው ይዘው
ሲመጡ አባ ጳዉሊ ዐርፈው ነፍሳቸውን መላእከተ ብርሃን ይዘዋት ሲያርጉ
ተመለከቱ፡፡
☞መላዕክቱም አባ ጳውሊ ዐርፏል ሄደህ ቅበረው አሏቸው፡፡ ይህንስ የያዝኩትን
ቆብ ልተወውን ቢሏቸው አትተው አድርግለት ብለ መለሱላቸው፡፡
]አባ እንጦስም ቢሄዱ አባ ጳውሊ መጽሐፋቸውን ታቅፈው አጽፋቸውን ተጎናጽፈው
ከበዓታቸው ዐርፈው አገኟቸው፡፡
☞እርሳቸውም የአባ ጳውሊን ሥጋ በልብስ ሸፍነው በጸሎታቸው እንዲያስቧቸው
እየተማጸኑ አለቀሱ፡፡ የሥጋቸውን መቃብር ጉዳይ እንዳልተማከሩ አባ እንጦስ
እያሰቡ ሳሉ የታዘዙ አንበሶች መጥተው እጅ ነስተው እግራቸውን ከላሱ በኃላ አባ
እንጦስ የአባ ጳውሊን ሥጋ የሚቀበሩበት ቦታ አሳይተዋቸውአንበሶቹ ቆፎረው
ሰጨርሱ ወጥተው ሰግደውላቸው ሄዱ፡፡
☞አባ እንጦስ በክብር ከቀበሯቸው በኃላ ወደ እስክንድርያ ሄደው ለአባ
አትናቴዎስ የሆነውን ሁሉ ከነገሯቸው በኃላ የሰሌን አጽፋቸውን ሰጧቸው፡፡
☞የከበረ ሊቀ ጳጳሳት አትናቴዎስ ያችን የአባ ጳውሊን አጽፍ በክብር
አስቀምጠው ሦስት ጊዜ ብቻ ማለትም በልደት፤ በጥምቀትና በትንሣኤ በዓል
ብቻ ይለብሷት ነበር፡፡ በሞትም ሰው ላይ ጥለዋት ሙት አሰነሥተውባታል፡፡
የአባታች የአጳውሊ በዓለ ዕረፍታቸው የካቲት 2 ሲሆን ወር በገባ በ16 ደግሞ
ወርሀዊ መታሰቢያቸው ነው፡፡
☞(መዝገበ ቅዱሳን መጻሐፍ ገጽ516-517)
☞የአባ ጳውሊ የአባ እንጦስ የጸሎታቸው በረከት በሁላች ላይ ይደር