2022-07-23 23:05:01
እውነተኛው ጓደኛህ ማነው ?
የከበቡህ ፣ ረጅም ጊዜ አብረውህ የሚያሳልፉ ሰዎች በሙሉ ጓደኞችህ #አይደሉም ።
በጓደኝነት ግንኙነት ውስጥ ብዙ አይነት ጓደኝነት አለ ።
ነገር ግን የልብ ጓደኝነት ከየትኛውም አይነት ይበልጣል ። እራሱን ለማዳን ወይም ያንተን ውድቀት ስለሚፈልግ ብቻ አንተን አሳልፎ የሚሰጥህ ጓደኛ እንደመኖሩ መጠን ላንተ ብሎ እራሱን የሚሰጥም የልብ ወዳጅ ጓደኛ አለ ።
አዎ! ጀግናዬ..! እውነተኛው ጓደኛህ ማነው ? በቀላሉ የሚረዳህ ፣ መንገድህን የሚጠርግልህ ፣ ሃሳብህን ፣ ህልምህን ፣ ራዕይህን የሚደግፍልህ ፣ ተግባርህን ለማወቅ የሚጥር ፣ ያንተን ቦታ ብትሰጠው እንኳን ባንተው ስሜት ሃሳብህን የሚፈፅምልህ ፣ የሚታመንልህ እርሱ ማነው ? አሁን ከጎንህ አለን ?
አዎ! ብዙ ሰው ብዙ ጓደኞች አሉት ፤ ከብዛታቸው ያተረፈው ነገር ግን የለም ። ጉዳይህ ጉዳዩ ፣ እንድገትህ እድገቱ ፣ ስኬትህ ስኬቱ ፣ ደስታህ ደስታው ያልሆነ ሰው መቼም ጓደኛህንና የልቤ የምትለው ሰው ሊሆን አይችልም ። ማንም ምንም ሊል ይችላል ጓደኛህ ግን ያንተ ጉዳይ የእርሱም ሊሆን ይገባል ። ሁሉን አቀፍ የሆነ ተግባቦትና እድገት ለጓደኝነት ቁልፍ ነገር ነው ። አንተ ወደህ የጀመርከውና ያስደሰተህ አዲስ ነገር እርሱንም ሊያስደስተው ይገባል ።
አዎ! ጓደኝነት ሁሉም ነገር ነው ። ጓደኝነት ወንድማማችነት ነው ፤ እህትማማችነት ነው ፤ መደጋገፍ ፣ መበረታታት ፣ አለኝታ መሆን ነው ። በየትኛውም መመዘኛ የእድገትህ ማነቆ ፣ የስኬትህ ቀበኛ ፣ የለውጥህ ተግዳሮት የሆነ ጓደኛ በህይወትህ ሊኖር አይገባል ። ሳትጠይቅ የሚደግፍህ የእራስ ሰው ባለበት አለም አስፈላጊነቱን ነግረሀው ፣ እንዲደግፍህ ተማፅነሀው እንኳን ፊቱን የሚያዞርብህ ጭራሽ በምትኩ አንተን ጥሎህ ለማለፍ የሚሽቀዳደው ጓደኛ ፣ ጓደኛ ሳይሆን ቀበኛህ ነውና ጊዜ ሳታጠፋ መንገድህን ከእርሱ ለይ ። እየሳቀ ከሚጥልህ እየተቆጣ ፣ እየገሰፀ የሚያስተካክልህ ሰው ላንተ ትልቅ ስፍራ አለው ።
የእኔ የምትለው ማንኛውም ሰው ያንተ ለመሆኑ ማረጋገጫ መስፈርትና መመዘኛ አስቀምጥ ። በአፉ እየደለለ በተግባር አብሮህ ካልሆነ ፣ ምርጫ በማትሰጠው ከንግግር ይልቅ ተግባር የመመዘን መርህ ፣ መስፈርቱን ባለማለፉ ቢኖርም ከማይጠቅምህ ፣ ቢሄድም ከማይጎዳህ ሰው መለየት ይኖርብሃል ። ራቀው ፣ ሽሸው ፣ መኖሩ ትርጉም ካልሰጠህ ፣ ምንም ካልፈየደህ በመሄዱ መፀፀት አያስፈልግምና ዙሪያህን ማጥራት ጀምር ፣ ትክክለኛና እውነተኛ በምትላቸው የልብ ሰዎች አካባቢህን ማጠር ጀምር ፤ ህይወትህንም ጥራት ባላቸው ሰዎች ሙላ ።
168 views@Teka Yeliju, 20:05