Get Mystery Box with random crypto!

ስኬት(how to succede)

የቴሌግራም ቻናል አርማ success_love_unity — ስኬት(how to succede)
የቴሌግራም ቻናል አርማ success_love_unity — ስኬት(how to succede)
የሰርጥ አድራሻ: @success_love_unity
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 792
የሰርጥ መግለጫ

አነቃቂ ሀሳቦችን ለማግኘት አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ🙏

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-23 19:32:21 ለትልቁ እያዘጋጀህ ነው !

የሰው ልጅ በህይወት እስካለ ድረስ ፈተና አያጋጥመውም በህይወቱ ላይ ምንም አይነት ጥያቄ አይፈጠርበትም ማለት አይደለም ፤ ሁላችንም ጋር የጠበቅነውም ይሁን ያልጠበቅነው የተለያዩ አጋጣሚዎች ሊፈጠሩብን ይችላሉ በነሱ ፈተናዎች የመቆምና ያለ መቆም ግን የኛ ድርሻ ነው ።

አንዳንዴ ፈጣሪ ለጠየቅነው ትልቅ ጥያቄ ምላሽ ሊሰጠን ሲፈልግ ትናንሾቹን ጥያቄዎቻችንን ችላ ይለናል ስለዚህ ባጋጠመህ ነገር አትረበሽ ይልቅ ለሚሰጥህ ትልቅ ስጦታ ራስህን አዘጋጅ !

ፀሎታችን የሚሰማበት ምሽት ተመኘን
@success_love_unity
271 viewsMatias Derso, 16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 08:56:11 ራስህን አክብር!

ሰዎች ባንተ ከማመናቸው በፊት አንተ በራስህ እመን! ሙሉ ሆነህ እንደተፈጠረህ ካመንክ የማንንም ማረጋገጫ አትፈልም፤ ምክንያቱም አንተ ራስህን ስትቀበል ሁሉም ይቀበልሀል። እውነተኛ ታላቅነት ከውስጥህ የሚመነጭ እንጂ ማንም የሚሰጥህ አይደለም!

እንከን የለሽ መሆን አይጠበቅብህም፤ ራስህ ላይ ህግ አታብዛ! ሰዎች የሚያከብሩህ ራስህን ከነጉድለትህ ስታከብረው ነው፤ ፈተናዎች ቀላል የሚሆኑት ብርቱ እንደሆንክ ስታምን ነው። የህይወትህ ተፅናኖ ፈጣሪ ማንም አይደለም፤ አንተው ራስህ ነህ!

የሚያረካ ሀሙስ ተመኘንላችሁ
@success_love_unity
266 viewsMatias Derso, 05:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 19:38:20 አጋጣሚ ነው !

ሰዎች ቃለ መጠይቅ ሲጠየቁ አስቸጋሪ የህይወት አጋጣሚ ካላችሁ አካፍሉን ተብለው እንጂ ህይወትህን አይባሉም ምክንያቱም ህይወት ሌላ የህይወት አጋጣሚ ሌላ ናቸው። በህይወት አጋጣሚ ህይወትህን አትለካ !

ማራኪ ምሽት ተመኘን
@success_love_unity
248 viewsMatias Derso, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:31:10 በምስጋና ጀምር!

በተቻለህ አቅም ሁሌም አመስጋኝ ሁን፤ በጎ በማሰብህ ብቻ ምናልባትም የህይወትህን አቅጣጫ እስከመጨረሻው ሊቀይር የሚችል ነገር አይምሮህ ላይ ሊከሰት ይችላል። በሀሳብ መልካም ነገር ከዘራህ በህይወት መልካም ነገር ታጭዳለህ!

ትንሽዬ ክብሪት የጀመረችው እሳት ነው ጫካ የሚያነደው፤ ጠዋትህን በምስጋና ስትጀምር ትንሿ በጎ ሀሳብህ ቢያንስ ቀንህን ውብ ታደርገዋለች።

ልዩ ረቡዕ ተመኘንላችሁ
@success_love_unity
241 viewsMatias Derso, 06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 20:46:57 ተነስና አድርገው!

መዋኘት እያማረህ መርጠብ ግን አትፈልግም! መለወጥ ትፈልጋለህ መጀመር ግን አልቻልክም! ተኝተህ ፈጣሪ ያውቃል አትበል! ካልተነሳህ ፈጣሪ የሚያውቀው እንቅልፋም እንደሆንክ ነው። በራስህ መታገል አለብህ! ብቻህን ስንፍናህን ማሸነፍ አለብህ! እንጂ ነገሮች ሁሌም አይመቻቹም፤ ሁሌም ሙድ ውስጥ አትገባም! ሰበበኛውን ቅበረው!

መርፌ የሚፈውስህ እያሳመመ ነው፤ እየደበረህ ስትጀምረው እየቀፈፈህ ከአልጋ ስትነሳ ማቆም እየፈለክ መተው እያመረህ ስትቀጥል ባይፃፍልህም ታሪክ እየሰራህ ነው፤ ድርሳን ላይ ባይሰፍርም ጀብዱ እየፈፀምክ ነው፤ ወዳጄ ቢያስጠላህም ማድረግ ያለብህን ተነስና አድርገው!

አስገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ
@success_love_unity
252 viewsMatias Derso, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 09:23:00 ትኩረትህን ቀይር!

ግራንት ካርደን የተባለ ሚሊየነር "በጣም የሚያበሳጭ ነገር በገጠመኝ ቁጥር ወረቀት አውጥቼ ትልቁ ህልሜን እፅፈዋለው፤ ከዛ እንደገና አዲስ ጉልበት እና ሀይል እሞላለሁ" ይለናል። አይንህን ከትናንሾቹ ችግሮችህ ንቀልና ትልቁ መድረሻህ ላይ አድርግ!

ትኩረትህ ወዳለበት ጉልበትህ ይፈሳል፤ ከጥቃቅን ድክመቶችህ እና ሰው ምን ይለኛል ከሚለው ጭንቀትህ ይልቅ ስለ ትልቁ ፍላጎትህ ማሰቡ ብርታት ይሰጥሀል። በህይወት ወሳኙ የገጠመህ ችግር አይደለም...ወሳኙ ያንተ ምላሽና ቆራጥነት ነው!

የደስታ ማክሰኞ ተመኘንላችሁ
@success_love_unity
254 viewsMatias Derso, 06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 18:57:45 ራስን ማወዳደር!

ከሰዎች ጋር ንፅፅር ያለህን እንዳታይ እንዳታመሰግን እውር ያደርግሀል! ለማን ብለህ ነው ህይወትህን ከሌሎች ጋር የምታወዳድረው?! አንተ ባትሆን ያን ከባድ ጊዜ ማን ያልፍ ነበር? ወዳጄ ከራስህ ትላንት ጋር ብቻ ተወዳደር!

የሚገርም ምሽት ተመኘንላችሁ
@success_love_unity
261 viewsMatias Derso, 15:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 08:01:28 ቀን ሮጦ አያውቅም !

በየትኛውም መስፈርት ብትለካው አሁን የምትለውን ሩጫ ቀኑ አይሮጠውም ፤ ቀንህን የምትቆጣጠረው አንተው እራስህ ነህ በየቀኑ ማድረግ የምትፈልገውን የምትወስነው አንተው ራስህ ነህ በተሳሳተ አመለካከት ራስህ አትሸውድ ። ቁጭ በል እና ነገ ምን ማድረግ እንደምትፈልግ ዛሬ ወስን የወሰንከውን ደግሞ ነገ አድርገው አለቀ !

ምችት ያለ ሰኞ ተመኘንላችሁ
@success_love_unity
265 viewsMatias Derso, 05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 19:30:52 የፈጣሪ ስጦታ!

"ፈጣሪ ስጦታ ሊሰጥህ ሲል የስጦታው መሸፈኛ ችግር ነው፤ ትልቁ የፈጣሪ ስጦታ ሊሰጥህ ሲል በትልቅ ችግር ተጠቅልሎ ይደርስሀል" ይለናል ደራሲ ኖርማል ቪንሰንት ፔል

የሚገጥምህ ችግር የማይታለፍ ቢመስልም ብዙ ስጦታዎች ይዞ እንደሚመጣ አትጠራጠር!

ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ
@success_love_unity
279 viewsMatias Derso, 16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 08:35:05 ራስን ማድመጥ!

ታላቅነት የሚፀነሰው መፃህፍትን በማንበብ፣ የሚበልጡህን ሰዎችን በማማከርና ልምድ በመውሰድ ሲሆን ታላቅነት የሚወለደው ግን ራስን በማድመጥ ነው።

ምን እንደምትፈልግ ለማሰብ ጊዜ ውሰድ፤ የሚያስደስትህን የምታምንበትን ለማድረግ አንድ እርምጃ ጀምር ከዛ የምትፈልገው ነገር እስኪፈጠር ድረስ ጥረትህን አታቁም ምክንያቱም የተሸነፍከው ያቆምክ ዕለት ነው!

ሰናይ ሰንበት ተመኘንላችሁ
@success_love_unity
293 viewsMatias Derso, 05:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ