Get Mystery Box with random crypto!

ተነስና አድርገው! መዋኘት እያማረህ መርጠብ ግን አትፈልግም! መለወጥ ትፈልጋለህ መጀመር ግን አል | ስኬት(how to succede)

ተነስና አድርገው!

መዋኘት እያማረህ መርጠብ ግን አትፈልግም! መለወጥ ትፈልጋለህ መጀመር ግን አልቻልክም! ተኝተህ ፈጣሪ ያውቃል አትበል! ካልተነሳህ ፈጣሪ የሚያውቀው እንቅልፋም እንደሆንክ ነው። በራስህ መታገል አለብህ! ብቻህን ስንፍናህን ማሸነፍ አለብህ! እንጂ ነገሮች ሁሌም አይመቻቹም፤ ሁሌም ሙድ ውስጥ አትገባም! ሰበበኛውን ቅበረው!

መርፌ የሚፈውስህ እያሳመመ ነው፤ እየደበረህ ስትጀምረው እየቀፈፈህ ከአልጋ ስትነሳ ማቆም እየፈለክ መተው እያመረህ ስትቀጥል ባይፃፍልህም ታሪክ እየሰራህ ነው፤ ድርሳን ላይ ባይሰፍርም ጀብዱ እየፈፀምክ ነው፤ ወዳጄ ቢያስጠላህም ማድረግ ያለብህን ተነስና አድርገው!

አስገራሚ ምሽት ተመኘንላችሁ
@success_love_unity