Get Mystery Box with random crypto!

ግድያ በመፅሀፍ ቅዱስ -=-=-=-=-=-=-=---=-=- ብዙ ግዜ ክርስቲያን ወገኖች ነብዩ ሙሐመ | 1 ነት ጀምአ

ግድያ በመፅሀፍ ቅዱስ
-=-=-=-=-=-=-=---=-=-

ብዙ ግዜ ክርስቲያን ወገኖች ነብዩ ሙሐመድ (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) በአመፀኛና ፀረ እዉነት በሆኑ ሰዎች ላይ የወሰዷቸዉን ተገቢና ምክንያታዊ የሆኑ እርምጃዎችን በመጥቀስ እስልምና ገዳይና አራጅ እንዲሁ የሰዉ መብት የሚነፍግ ሀይማኖት ነዉ በማለት የተሳሳተና የእንቶ ፈንቶ ድምዳሜ ሲሰጡ ይስተዋላል።

ይህን ሲናገሩ ለሰማቸዉ ክርስትና በፈጣሪዉ ባመፀ ሰዉ ላይ ምንም አይነት ምድራዊ ቅጣትና እርምጃ እንደማይወስድ ያስመስላሉ ግን እዉነታዉን ጠጋ ብለን ስናይ እንደ መፅሀፍ ቅዱስ የዘር ጭፍጨፋን የሚያዝና የሰዉ ደም ያለ አግባብ እንዲፈስ የሚያበረታታ መፅሀፍ በምድራችን ላይ የለም።

አረመኔዉ ንጉስ ሂትለር ቢያያቸዉ እንኳ የሚቀናባቸዉ የሆኑ የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፆችን በጥቂቱ ከጥቂት ማብራሪያ ጋር ላስቃኛቹ:-

ሕዝቅኤል 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁵ እኔም እየሰማሁ ለሌሎቹ፦ እርሱን ተከትላችሁ በከተማይቱ መካከል እለፉ ግደሉም፤ ዓይናችሁ አይራራ አትዘኑም፤
⁶ ሽማግሌውንና ጐበዙን ቈንጆይቱንም ሕፃናቶቹንና ሴቶቹን ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወዳለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።

ይህንን ከላይ የለጠፍኩላቹን ሁለት የመፅሀፍ ቅዱስ አንቀፅ በመፅሀፍ ቅዱስ ትንቢተ "ሕዝቅኤል" ምእራፍ ዘጠኝ ከ5-6 ታገኙታላቹ እናም አዉደ ንባቡን ወደላይ ወጣ ብላቹ ብታነቡት ይህ ፍርድ የተፈረደባቸዉ ሰዉች ለጌታ ትተዉ ለፀሀይ በመስገዳቸዉ ነዉ ይህን ከተማመንን አሁን ላይ ክርስቲያኖች እንደሚሉት በክርስትና አስተሳሰብ ሰዉ የፈለገዉን የማምለክ መብት የለዉም። ይህን ካደረገ ይገደላል ማለት ነዉ። ይህ መሆኑ ደሞ በዉሸት ክርስትና ሰዉ የፈለገዉን ቢያመልክ እርምጃ አይወስድበትም መብት ሰቶታል በማለት የሰፉትን ድሪቶ አፈር አባቱን አብልቶ ይቀደዋል ማለት ነዉ።

ከዛ በተጨማሪ ደግሞ በነዚህ አንቀፆች ክርስትና ሴቶችንና ለጋ ህፃናትን እዲጨፈጨፉ እንደሚያዝ አይተናል ይህ ደግሞ የግፍ ግፍ ነዉ ምክንያቱም ሴት ልጅ ደካማ ነች እንደወንድ አትታገል ለምን ትገደላለች ህፃናትስ ምን አቅም ኖሯቸዉ ምን ያዉቁና ነዉ የሚገደሉት?

ይህን አይነቱን የሴትና የህፃናት ጅምላ ጭፍጨፋ እስልምና አጥብቆ ይከለክላል።

ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ መፅሀፍ ቅዱስ ኤልያስ የሚሉት ነብይ በዉሸት ነብይ ነን የሚሉ ሰዎችን እንዳሳረዳቸዉ ይነግረናል አንቀፁን እንካቹ:-
“ኤልያስም፦ ከበኣል ነቢያት አንድ ሰው እንዳያመልጥ ያዙ አላቸው። ያዙአቸውም ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ ወስዶ በዚያ አሳረዳቸው።”
— 1ኛ ነገሥት 18፥40

አንቀፆች አሁንም ልድገምላቹ:-

2 ዜና 13
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ የእስራኤልም ልጆች ከይሁዳ ፊት ሸሹ፥ እግዚአብሔርም በእጃቸው አሳልፎ ሰጣቸው።
¹⁷ አብያና ሕዝቡ ታላቅ አመታት መቱአቸው፤ ከእስራኤልም አምስት መቶ ሺህ የተመረጡ ሰዎች ተገድለው ወደቁ።

ሌላ ተጨማሪ አንፅ:-

1ኛ ነገሥት 21
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁸ የእግዚአብሔርም ሰው ቀርቦ የእስራኤልን ንጉሥ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሶርያውያን፦ እግዚአብሔር የተራሮች አምላክ ነው እንጂ የሸለቆ አምላክ አይደለም ብለዋልና ይህን ታላቅ ጭፍራ ሁሉ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ አለው።
²⁹ እነዚህም በእነዚያ ትይዩ ሰባት ቀን ያህል ሰፈሩ፤ በሰባተኛውም ቀን ተጋጠሙ፥ የእስራኤልም ልጆች ከሶርያውያን በአንድ ቀን መቶ ሺህ እግረኛ ገደሉ።

አሁን ከላይ በጠቀስኩላቹ "በ2ኛ ዜና 13" ላይ ከ16-17 ባሉት ሁለት አንቀፆች እና "በ1ኛ ነገስት 21 " ላይ ከ28-29 ባሉት አንቀፆች እንድታሰምሩበት የምፈልገዉ ጉዳይ በእግዝአብሄር ትእዛዝ በተደረጉት በጠቀስኳቸዉ ሁለት ጦርነቶች የተገደሉትን ሰዎች ብዛት ነዉ አንቀፆቹን መለስ ብላቹ ካስተዋላቹሀቸዉ በአንደኛዉ ጦርነት ግማሽ ሚሊዮን (500,000) ሰዎች በሁለተኛ ደግሞ መቶ ሺ (100,000) መገደላቸዉን ታያላቹ ይህን ካስተዋላቹ አንድ አንፃራዊ ነገር እንድታነሱና እንድታስተዉሉ እጠይቃለዉ እሱም ነብዩ ሙሀመድ (ሰለሏሁአለይሂ ወሰለም) ተገደዉ እራሳቸዉን ለመከላከል ባደረጓቸዉ ከ10 በላይ ጦርነት ላይ የሞቱት ሰዎች ቁጥር "756" መሆኑን ነዉ ይህ መሆኑ ኢስላም የሰዉ ዉድመት እንዳይፈጠር ምን ያህል እንደሚጠነቀቅ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

እና ታድያ በሁለት ጦርነት ብቻ ስድስት መቶ ሺ (600,000)ሰዎችን የጨፈጨፈዉ ክርስትና ወይንስ ከ"10" በላይ በሆኑ ጦርነቶች "756" ሰዎች የሞቱበት እስልምና ከሁለቱ ማነኛቸዉ ናቸዉ የሰዉ መዉደም የማያሳስባቸዉና አራጅ???

እንግዲህ ዉድ አንባቢያን ይታያቹ ክርስቲያኖች ይህንን ሁሉ ግፍ አምቀዉ ነዉ ዛሬ ላይ መተዉ ራሱን ለመከላከል ብቻ ሲል ጦርነት ያወጀዉን እስልምናን የሚተቹት "የራሷ አሮባት የሰዉ ታማስላለች ይለሀል ይህ ነዉ።


ኢብኑ አብራር

ቻናላችንን ለመቀላቀል

https://t.me/joinchat/YlCprY3U05wzNWY8