Get Mystery Box with random crypto!

መልኬ ያምር ይሆን ፨፨፨ ታበጥራለህ ትታጠባለህ ትቀባለህ ትስተካከላለህ ከዛ በመስታውት ታያለህ አ | መንፈሳዊ ግጥሞች

መልኬ ያምር ይሆን
፨፨፨
ታበጥራለህ ትታጠባለህ ትቀባለህ
ትስተካከላለህ
ከዛ በመስታውት ታያለህ
አንተው ራስህ ብትሆንም ግን ጽድት ታረገዋለህ።
እንዴት ነኝ አምራለሁ ? ብለህም ለሰዎች ራስክን አስተያየት እንዲሰጡህ ትጠይቅም ይሆናል

መልክህን እንዳሳመርከው እንዳስዋብከው
በመስታወት እንዳየኸው
በሰው እንዳሰገመገምከው
አንተነትክንስ? አስተሳሰብህንስ እንዴት ነው ውብ ምታደርገው?
ምታስገመግመውስ?

መጽሐፍት የአንተን ሚዛን ይነግሩሃል የአንተነትህን ሚዛን ይነግሩኻል።

የራስን መልክ ለማየት መስታውት እንደሚያስፈልግ ሁሉ....
የራስህን አስተሳሰብ ለመገምገም መጽሐፍት ያስፈልጋሉ
@spritualpoem
    @spritualpoem
    @spritualpoem