Get Mystery Box with random crypto!

ጠይቅ ፨፨፨ ሐሳብ ሲለዋወጥ፡ሰው ከሰው ሲመክር ቤተሰብ ይጸናል: ትቆማለች ሀገር ሲጠያየቅ ሰዉ: | መንፈሳዊ ግጥሞች

ጠይቅ
፨፨፨
ሐሳብ ሲለዋወጥ፡ሰው ከሰው ሲመክር
ቤተሰብ ይጸናል: ትቆማለች ሀገር
ሲጠያየቅ ሰዉ: የማያውቅ ከሚያውቀው
ፍቅርንም ይጨምራል,  ይበልጥ ተዋውቀው።

እንዲሁ ቢቀመጥ,  አውቃለሁ እያሉ
በሰው ፊት ያፍራሉ፡  የታለ ቢባሉ

አንብብ ለምን ብለህ ጠይቅ
በጎውን ቁምነገር : አብጠርጥረህ እወቅ
ትደርሳለህ አንተም: ከደቂቅ ወደ ሊቅ።

ካላወቁ አይሰሩ: ይሄነን ጠንቅቁ
ትሩፋት ደግነትን: ካልሰሩም አይጸድቁ

ከተሰወረችው ለማግኘት: ጥበብን
አምላክን ጠይቀው: እንደ ሰሎሞን።

ስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን
#Orthodox #Christianity #Inspiration-towards-the-heaven , #Jusus-is-God, #St.Mary-God's-Mother
#ኦርቶዶክስ-ክርስቲያን
#ወደ-አባቶቻችን-ርስት-አይናችን-እናቅና
#ክርስቶስ-እግዚአብሔር-ነው
#ቅድስት-ማርያም-የአምላክ-እናት ናት።
@spritualpoem
    @spritualpoem
    @spritualpoem