Get Mystery Box with random crypto!

ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ

የቴሌግራም ቻናል አርማ smu_gibi_gubae — ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ
የቴሌግራም ቻናል አርማ smu_gibi_gubae — ቅ/ማ/ዩኒቨርስቲ ግቢ ጉባዔ
የሰርጥ አድራሻ: @smu_gibi_gubae
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 696
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ማኅበረ ቅዱሳን አዲስአበባ ማዕከል የቅ/ማ/ዩ/ግ/ጉባዔ የቴሌግራም ቻናል ነው።
#በዚህ_ቻናል
👉ስለ ቅድስት ቤተክርስቲያን ወቅታዊ መረጃዎችን ፣መዝሙሮችን ፣ትምህርታዊ ጽሁፎችን እንዲሁም ስለ ግቢጉባዔያችን መረጃዎች እና ማስታወቂያዎች ይደርሳችኋል።
ይህንን ሊንክ በመጫን ለወዳጅዎ ያጋሩ!!
👉 @smu_gibi_gubae
መልእክት፣አስተያየትና ጥያቄ ካሎት 👉@DnHaileBot ላይ ላኩልን።

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-05 21:08:33 https://youtube.com/shorts/-WmcIsBH2Q8?feature=share
248 views18:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 19:11:40 ሰላም እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በነገው ዕለት (ቅዳሜ) የመዝሙር ጥናት ሰለሚኖረን ከ6-7 በመገኘት እንድንማር ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን እንዲሁም ያልሰሙ እኅት ወንድሞቻችሁን ወደ ግቢ ጉባኤያችን እንድትጋብዙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።


ቦታ የምእመናን መጠለያ (ገረገራ)

ይህን መልዕክት ላልሰሙ ጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉላቸው!!
285 views16:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 19:33:39 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
<< ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ >> ማቴ ፳፮ ፥ ፵፩

ሰላም ውድ የቅድስተ ማርያም ዩንቨርስቲ ግቢ ጉባኤ አባላት ተማሪዎች ነገ ማለትም ዓርብ ሀምሌ 29 2014 ዓ.ም ከ6:00 - 7:15 ሳምንታዊ የግቢ ጉባኤው የፀሎት መርሐግብር ስለሆነ ሁላችሁም በፀሎቱ መርሐግብሩ ላይ በመሳተፍ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ።
ቦታ: ቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያን አዲሱ ህንጻ 4ተኛ ፎቅ ወይም መሬት ላይ ያለው የጭቃ አዳራሽ
307 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 17:12:17
359 views14:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 17:11:55 ክፍል 2 ስልጠና ነገ ሐምሌ 28 2014 ዓ.ም ይቀጥላል ሰዓት ከ6:00 - 7:15
ቦታ አዲሱ ቢጫ ህንፃ 4ተኛ ፎቅ
333 views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 22:04:17 ሰላም እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች በነገው ዕለት ማለትም ሀምሌ 27 የአብነት ት/ት ጥናት ሰለሚቀጥል ከ6-7 በመገኘት እንድንማር ስንል በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን ያልሰሙ እኅት ወንድሞቻችሁንም ወደ ግቢ ጉባኤያችን እንድትጋብዙ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን። ሠናይ ምሽት ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን!!

ቦታ አዲሱ ቢጫ ህንጻ 4ተኛ ፎቅ ላይ ነው

ይህን መልዕክት ላልሰሙ ጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉላቸው
372 viewsedited  19:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:46:30
378 views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:46:18 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
አቡነ ሰላማ (ፍሬምናጦስ)
የመጀመሪያ ስማቸው ፍሬምናጦስ ሲሆን ትውልድ ሀገራቸው ሶርያ (ጢሮስ) ነው፡፡ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጳጳስ ሲሆኑ በትምህርታቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ ከገቢረ ኃጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ የመለሱ ሐዋርያዊ ናቸው፡፡
ከሶርያ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በፈቃደ እግዚአብሔር ነው፤ ይህም ነጋዴ ዘመድ የነበራቸው ሲሆን እርሳቸውንና ኤስድዮስን(ሲድራኮስን) አስከትሎ ለንግድ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ሲመለስ ከመንገድ ወንበዴዎች አገኙት፡፡ በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያ የሮምን ቅኝ ግዛት ትቃወም ስለነበር መልካቸው ሮማውያንን ስለሚመስል በአዶሊስ ባሕር አካባቢ ያሉ ጠባቂዎች ነጋዴውንና የመርከቡ ቀዛፊዎችን ገደሏቸው፡፡ ፍሬምናጦስና ሲድራኮስ ገና ትንንሽ ልጅ ስለነበሩ ማርከው በዘመኑ በኢትዮጵያ ለነበረው ንጉሥ አልዓሜዳ ሰጧቸውና ከንጉሥ አልዓሜዳ ልጆች ጋር አድገዋል፤ አልዓሜዳ የኢዛናና ሳይዛና (አብርሃ ወአጽብሃ) አባት ነው፡፡ ንጉሡም የፍሬምናጦስንና የሲድራኮስን ሥነ-ምግባራቸውንና ጽናታቸውን ተመልክቶ ሲድራኮስን ከቤተ መንግሥት ፍሬምናጦስን ደግሞ ከቤተ መዛግብት አስገባቸው፡፡ ንጉሥ አልዓሜዳ ከሞተ በኋላ ሚስቱ የቤተ መንግሥቱን ሥልጣን ተረክባ ሲድራኮስና ፍሬምናጦስ ከባዱን የመንግሥት አስተዳደር ልጆቿ እስኪደርሱ ድረስ እንዲረዷት ከዚያ በኋላ ከፈለጉ ወደ ሀገራቸው መመለስ እንደሚችሉ ስለለመነቻቸው የአስተዳደሩን ሥራ ሲረዷት ቆዩ፡፡
በኋላም ኢዛናና ሳይዛና አድገው ስመ ንግሥናቸው አብርሐ ወአጽብሐ ሆኖ ማስተዳደር ጀመሩ፡፡ አባ ፍሬምናጦስ ከአክሱም ገበዝ ከእንበረም ብሉይን ይማሩ ይመካከሩ ነበር፡፡ አንድ ቀን ‹‹አምናችኋል፣ ተገዝራችኋል ጥምቀትና ቁርባን ግን የላችሁም›› አሉት፤ እርሱም ‹‹ግዝረትን አባቶቻችን ሌዋውያን አምጥተውልናል እምነትንም ጃንደረባው ባኮስ አስተምሮን አምነናል፤ ለጥምቀት ለቁርባን ግን ሐዋርያ አልተላከልንም›› ቢላቸው ‹‹እስክንድርያ ቅርብ አይደለችምን? ለምን ሄዳችሁ አታመጡም?›› አሉት፡፡ ከዚያም ከቤተ መንግሥት ተማክሮ ‹‹አንተ ባወቅህ አምጣልን›› ብሎ 500 ወቄት ወርቅ ሰጥቶ ሰደዳቸው፡፡ አባ ፍሬምናጦስ እስክንድርያ በደረሱ ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ እለእስክንድሮስ ለኒቅያ ጉባኤ (325 ዓ.ም) ሄዶ ነበር፡፡ ሠለስቱ ምዕት አርዮስን አውግዘው ሲለያዩ አግኝተውት የመጡበትን ምክንያት ለእለእስክንድሮስ አስረዱት፡፡ አባ እለእስክንድሮስም ነገሩን ሰምቶ ደስ አለው፤ ሠለስቱ ምዕትን ሳላማክር አይሆንምና ብሎ ሰብስቧቸው ‹‹አንዲት ያለ ሐዋርያ ያመነች ሀገር አለች›› በማለት ነገራቸው፡፡ ሠለስቱ ምዕትም ‹‹ያንተ ዕጣ ናትና አንተን መስላ ትደር አንተ ሹምላት›› ብለው መለሱለት፡፡ አባ እለእስክንድሮስ ከጉባኤ ከተመለሰ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በ328 ዓ.ም ዐረፈ፤ ከእርሱ ቀጥሎ ጵጵስና የተሾመው ቅዱስ አትናቴዎስ ሲሆን ‹‹ባህላቸውን የለመደ ቋንቋቸውን ያወቀ ከአንተ ሌላ ወዴት ይገኛል?›› ብሎ ሐዲስ አስተምሮ ‹‹አባ ሰላማ ጳጳስ ዘአክሱም ወኲላ ኢትዮጵያ›› ብሎ በ330 ዓ.ም በአንብሮተ ዕድ ሾሞ ወደ ኢትዮጵያ ልኳቸዋል፡፡ ሰላማ ማለት ሰላማዊ ማለት ነው፡፡
ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ከእንበረም ጀምረው ቀሳውስትን ዲያቆናትን ሾመው ተዘዋውረው በማስተማር በበጉ መሥዋዕት ፈንታ የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም እንዲፈተት አድርገዋል፡፡ በደብተራ ኦሪት የነበሩትን ሰባቱን ዲያቆናት በቅዳሴ ጊዜ እንዲራዱ ሾመዋል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትንም ከሱርስት፣ ከጽርዕ እና ከዕብራይስጥ ወደ ግእዝ ቋንቋ ተርጉመዋል፡፡ የሳባውያንንም የፊደል አቀማመጥ (ግእዝን) በመለወጥ ከግራ ወደ ቀኝ የመጻፍና የማንበብ ዘዴን ያስገኙ አባ ሰላማ ናቸው፡፡ ሐዋርያዊ ተልእኳቸውን በትጋት ሲፈጽሙ ኑረው ሐምሌ 26 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡ በረከታቸው ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መዝገበ ታሪክ ፣ መድበለ ታሪክ
312 views13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:45:24
220 views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 16:45:11 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ዮሴፍ_አረጋዊ
አረጋዊው ዮሴፍ ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ከቤተ ዳዊት ሲሆን እግዚአብሔርን የሚፈራ፣ ለሰው የሚራራ ደግ ሰው ነበር፤ (ማቴ 1፥16-25 ፣ ሉቃ 1፥27)፡፡ ድግር ጠርቦ፣ ጥርብ አለዝቦ በመሸጥ ይተዳደር ነበር፤ ለዚህም ነው ኢየሱስ ክርስቶስን ‹‹የጠራቢው ልጅ አይደለምን?›› እያሉ የሚጠሩት፤ (ማቴ 13፥55-56)፡፡ ቅዱስ ዮሴፍ ማርያምን (የቅድስት ኤልሳቤጥና ቅድስት ሐና እመ ማርያም እኅት) አግብቶ ያዕቆብ፣ ዮሳ፣ ስምዖን፣ ይሁዳና ሰሎሜ የሚባሉ ልጆችን ወልዷል፡፡ ሚስቱ ከሞተችበት በኋላ አይሁዳውያን በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ላይ በጠላትነት ተነሥተው ከቤተ መቅደስ ትውጣልን ባሉ ጊዜ ወስዶ ከቤቱ አስቀምጧታል፡፡ ከዚህ በኋላ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ በደስታዋም በኀዘኗም ጊዜ አልተለያትም፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በወለደች ጊዜም ዳስ ሠርቶ አገልግሏታል፡፡
ሄሮድስ ሕፃናትን በሰይፍ በአስፈጀ ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ለማዳን ወደ ግብፅና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ ረሃቡን፣ ጥሙን፣ የቀን ሐሩሩን፣ የሌሊት ቁሩን ታግሣ በረሀ ለበረሀ በተንከራተተችበት ወቅት አልተለያትም፤ (ማቴ ምዕራፍ 2)፡፡
ከስደት ከተመለሱ በኋላም ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አባት ሆኖ አሳድጎታል፤ አይሁዳውያን ጌታን የዮሴፍ ልጅ የሚሉትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሴፍ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ከኒቆዲሞስ ጋር ገንዞ በአዲስ መቃብር አኑረውታል፤ (ዮሐ 19፥38)፡፡ አረጋዊው ዮሴፍ በ104 ዓመቱ ሐምሌ 26 ቀን ዐርፏል፡፡ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ጸጋና በረከት ይደርብን አሜን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ
255 views13:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ