Get Mystery Box with random crypto!

❝ ወንድሜ አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ የዩናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ። ከፍራቻ ትገላገላለህ። መከራው | ቅድስት ፌብሮኒያ


ወንድሜ አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ የዩናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ። ከፍራቻ ትገላገላለህ። መከራው እግዚአብሔር ጸጋውን ሊያበዛልህ ስለፈለገ ያዘጋጀው ዓሣ ነባሪ እንደሆነ የምታውቅበት ጊዜ ይመጣል። የዚህ ዓለም የባሕር ዓሣዎች ብዙ ስለሆኑ ስትዋጥ እንዳይከፋህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል። የመጀመሪያው ባህታዊ ጻድቁ አባ ጳውሊ የተናገረውን መዘንጋት የለብህም "ከመከራ መራቅ የሚወድ ከእግዚአብሔር ይርቃል" ብሏል። በእውነት መከራ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። "በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ጮኽሁ እርሱም ሰማኝ። በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ። ቃሌንም አደመጠ" ዮናስ 2፥3

አባታችን አቡነ ሽኖዳ