Get Mystery Box with random crypto!

ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ማንንም አላገኝም ፣ ከአንተ ጋር | ቅድስት ፌብሮኒያ

ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ማንንም አላገኝም ፣ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጢሬን አዋይሃለሁ። ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላሰተውል ደካማ ነኝና ፣ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ። ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፊኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን ብቼኝነት አይሰማኝም ። ያለ አንተ ግን ባዶነቴ ያስጨንቀኛል ። ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከአለምና በአለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል።ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳልኝ ከቶ የለም ።
ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሽኖዳ