Get Mystery Box with random crypto!

Art of motivation

የቴሌግራም ቻናል አርማ skbbepositivethinker — Art of motivation A
የቴሌግራም ቻናል አርማ skbbepositivethinker — Art of motivation
የሰርጥ አድራሻ: @skbbepositivethinker
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 81
የሰርጥ መግለጫ

Public channel
Always be positive
Be self motivated

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-05-28 10:48:07 ሰዉ
222 viewsSha z Maan, 07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-28 10:31:12 Sugar & Salt may be mixed together, but ants reject the salt and carry away only sugar.

So select the right people in life and make your life sweeter...

Two simple lines:
Don't make any close relation without full understanding
And don't break any close relation with small misunderstanding!
240 viewsSha z Maan, 07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-20 21:55:07 Just 20 minutes of exercise three days a week will increase your happiness by around 10 to 20%
234 viewsSha z Maan, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-05 20:37:36 Martin Luther king says that
" not everybody can be famous, but everybody can be great because greatness determined by service "

Service make you a famous and success
@skbbepositivethinker
297 viewsSha z Maan, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-03 17:23:07 You can't be attached to a living thing like the running waters of a river or the moving mind. A living thing is a moving and changing thing; how can you be attached to it? You may have a feeling for a living thing,but you cannot be attached to a river which
is a moving thing.

እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ

ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች።ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል።ጊዜው ሲደርስም ይጎላል

ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው

ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል ገላችን፣ አእምሮአችን ይታመማል እንረበሻለን፣ እንጨነቃለን።

ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው

ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል።ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ። መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው

የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ።ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ እንደሚለወጥ ስለማውቅ!

'የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ ' ሲሉ አዛውንት 'ዝናቡን ፍራው ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው።ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው። አይመስልህም እንዴ?''
333 viewsSha z Maan, 14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-02 10:15:50
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳችሁ::
መልካም በአል።

Art of motivation wishesh a wonderful easter celebration for y'all Christians celebrating today.
@skbbepositivethinker
220 viewsSha z Maan, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-05-01 19:50:54 ነብሴን ጨፈለ‘ኳት ~ ስጋዬ አስገድዶኝ
ለኔ ብሎ ሲሞት ~ ለእርሱ መኖር ከብዶኝ
===||===
204 viewsSha z Maan, 16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-04-29 20:53:53 የበታችነት ስሜትን ማሸነፍ (ክፍል አንድ)
--------------------------------------


የበታችነት ስሜት ምንድነው?

የበታችነት ስሜት ማለት ስለራስ ማንነት፣ ብቃት፣ ችሎታ ወይም በሌሎች የህይወት ገጽታዎች ከሌሎች ሰዎች በታች እንደሆኑ ማሰብና ስሜቱንም መለማመድ ነው፡፡
ይህ ከሌሎች በታች እንደሆኑ ማሰብ በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በተለያዩ አሉታዊ ጫናዎች የተፈጠረ አስተሳሰብና ስሜት ነው፡፡ የበታችነት ስሜት ለራስ ዋጋ አለመስጠት፣ ስለራስ ብቃትና ችሎታ መጠራጠር እንዲሁም በማንኛውም መለኪያ ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል እንዳልሆኑ ተቀብሎ መኖር ነው፡፡

የበታችነት ስሜት በተጨባጭ ነባራዊ እውነታዎች ላይ መሠረት በማድረግ የሚሰጥ ምላሽ ሳይሆን ትክክለኛ ባልሆኑ በአብዛኛው መሠረተ-ቢስ በሆኑ ነጥቦች ላይ በመመርኮዝ ሰዎች ለራሳቸው የሚሰጡት የግምገማ ውጤት ነው፡፡
የበታችነት ስሜት ሰዎች ለራሳቸው የሚሰጡት ዋጋ በመሆኑ ውጫዊ ነገሮችን በመቀያየር የሚለወጥ ነገር አይደለም፡፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር እኩል ለመሆን በስራ እጅግ ስኬታማ መሆን፣ ገንዘብ ሊገዛ የሚችለውን ነገር ሁሉ መግዛት፣ መዝናናት፣ …..የበታችነት ስሜትን አያጠፋም፡፡ መንስኤው የሰዎች አስተሳሰብ በመሆኑ፣ ራሳቸውን የሚያዩበት መስፈርት መለወጥ አለበት፡፡

ራሳችንን የምናይበት ሁኔታ በአካባቢያችን ያለውን ዓለም የምናይበትን መነጽር ይሰጠናል፡፡ ራሳችንን የምንመለከትበት መነጽር ትክክለኛ ካልሆነ፣ ዓለምንም የምናይበት መነጽር የተሳሳተ ነው፡፡
የበታችነት ስሜት ሌሎች ሰዎች በእኛ ላይ የሚጭኑት አስተሳሰብ ሳይሆን እኛው ራሳችን የምናሳድገው አስተሳሰብ ነው፡፡ ሰዎች ለአስተሳሰቡ መንስኤዎች ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን እኛ እሺ ብለን ካልተቀበልን በስተቀር ሌሎች ምንም ያህል ስለእኛ መጥፎ ነገር ቢናገሩ በእኛ ላይ ኃይል እንዳይኖረው ማድረግ እንችላለን፡፡ ከበታችነት ስሜት ለመውጣትም ከፍተኛው ድርሻ የእኛው ይሆናል፡፡

የበታችነት ስሜት ምልክቶች

1. የበታችነት ስሜት እንደ በሽታ ነው፡፡ አንድ በሽታ የራሱ የሆነ ምልክት እንዳለው ሁሉ፣ የበታችነት ስሜትም እንደ ስነ-ልቦና ችግር የራሱ ምልክቶች አሉት፡፡ በዚህ ክፍል የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች በህይወታቸው የሚያሳዩትን ምልክቶችን አብረን እንመለከታለን፡፡
በህይወታቸው ውስጥ መልካም ነገር እንዳለ አያምኑም፡- እያንዳንዱ ሰው በህይወቱ ጠንካራና ደካማ ጎኖች አለው፡፡ የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ያለውን ደካማ/ የጎደለውን ነገር እንጂ ያላቸውን መልካምና ጠንካራ ነገር አያዩም፡፡ ሌላ ሰው ሲነግራቸው እንኳ እውነት እንደሆነ አምነው አይቀበሉም፡፡ ምክንያቱም እነርሱ ስለራሳቸው ከንቱ፣ ምስኪን፣ የሁሉ የበታች፣ ምንም ዋጋ የሌላቸው፣ …. አድርገው ደምደመዋል፡፡

2. ሰዎችን ለማስደሰት መኖር፡– የበታችነት ስሜት የሚያጠቃቸው ሰዎች ዋጋ እንዳላቸው ሌሎች ሰዎች እንዲያረጋግጡላቸው ይፈልጋሉ፡፡ ስለራሳቸው ጥሩ ነገሮችን በሚሰሙበት ጊዜ ደስ ይላቸዋል፡፡ ትንሽ ትችት ሲሰሙ ደግሞ እጅግ በጣም ይከፋቸዋል፡፡ ስለዚህ ሰዎች ስለእነርሱ ጥሩ ጥሩ ነገሮችን እንዲናገሩ ሌሎች ሰዎችን በማስደሰት ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ የመልካም ግብረ-መልስ ረሃብተኞች ናቸው፡፡ የሰዎችን ፍላጎት ለማርካት ከሚጠበቅባቸው ዕርምጃ አልፈው ይሄዳሉ፡፡ ይህን የሚያደርጉት በጎ ነገር ማድረግ በራሱ ስለሚያስደስታቸው ሳይሆን ሰዎች ያንን አይተው እንዲያሞግሱአቸው ነው፡፡

3. በራስ የመተማመን መንፈስ ማጣት፡– በተጨባጭ እነዚህ ሰዎች ብቃት፣ ችሎታ፣ ልምድ ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከውጭ የሚያዩአቸው ሰዎች እንደ እነርሱ ችሎታ ቢኖራቸው ይመኙ ይሆናል፡፡ የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ግን ችሎታቸውንና ብቃታቸውን ለመግለጽ የሚያስችል በራስ የመተማመን መንፈስ የላቸውም፡፡ ከዚህም የተነሣ መስራት ከሚችሉት ኃላፊነት፣ መጠቀም ከሚችሉት መልካም ዕድሎች ይሸሻሉ፡፡ እንደ ችሎታቸው ለእነርሱ የሚገባውን መልካም ዕድል ሌሎች በራስ መተማመን ያላቸው ሰዎች ይጠቀማሉ፡፡

4. ከፉክክርና ውድድር መሸሽ፡– የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ውድቀትንና ትችትን በጣም ከመፍራታቸው የተነሣ ከሰዎች ጋር ከሚያወዳድራቸው ነገሮች ይሸሻሉ፡፡ በክንውን ከሌሎች ሰዎች ጥቂት አንሶ መገኘት ቀድሞውንም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያለውን ስለራሳቸው ያላቸውን ግምት ክፉኛ ይጎዳል፡፡

5. ነገሮችን በወቅቱ አለመሥራት፡– አንዳንድ የበታችነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች ተገቢውን ሥራ በተገቢው ጊዜ ለመስራት የተነሳሳ መንፈስ የላቸውም፡፡ ምክንያቱም ‹‹ምንም ብሠራ፣ ውጤቱ ያው የማይረባ ነው፤ እኔ ጥሩ ነገር መስራት አልችልም›› የሚል አስተሳሰብ ስላላቸው ነው፡፡ ስለዚህ አሁን መስራት የሚችሉትን ነገር ‹‹ነገ እሰራለሁ›› እያሉ ቀጠሮ ይሰጣሉ፡፡

አንዳንዶች ደግሞ የሚሰማቸውን የበታችነት ስሜት ለማካካስ ማለትም በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ብለው መስራት ከሚገባቸው በላይ ይሰራሉ፡፡ ከዚህም የተነሳ በሚሰሩት ስራ የተከናወነላቸው ስኬታማ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሆኖም በውስጣቸው ለራሳቸው የሚሰጡት ዋጋ በዚህ ስኬት አይለወጥም፡፡

6. ስህተት ፈላጊዎች ናቸው፡– እነዚህ ሰዎች በህይወታቸው ውስጥ ካለው አዎንታዊ ነገር ይልቅ አሉታዊውን የማየት ልማድ አላቸው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በሌሎች ሰዎች ህይወት ውስጥም ጥሩ ነገር ከማየት ይልቅ መጥፎ ነገሮችን ማየት ይቀናቸዋል፡፡ ለሰዎች የማይታያቸው ስህተት ለእነርሱ ይገለጣል፤ ነገር ግን ግልጽ የሆኑትን መልካም ነገሮች ለማየት አይቀናቸውም፡፡

የበታችነት ስሜት መንስኤዎች

ለበታችነት ስሜት ዕድገት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል ዋና ዋና የሆኑትን ጥቂት ነጥቦችን እንመለከታለን፡፡

ሀ.ክፉ የአስተዳደግ ሁኔታ፡– ወላጆች ልጆቻቸውን ለማሳደግ የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች አዎንታዊ ካልሆኑ ልጆች ስለራሳቸው ያላቸው አስተሳሰብ አሉታዊ ይሆናል፡፡ ልጆች ስህተት ሲፈጽሙ፣ ሙከራ አድርገው ሳይሳካላቸው ሲቀር፣ አንድን ነገር ለመስራት ጥረት ሲያደርጉ …. ወላጆች የሚሰጡት አስተያየት አሉታዊ ሲሆን ልጆች የሆነ ችግር እንዳለባቸው ያስባሉ፡፡ ለምሳሌ ወላጆች የሚሰጡት ምላሽ ‹‹አንተ ደደብ ነህ፣ ይህን መስራት ያቅትሃልን! አንተ አትችልም፤ እንደ ሌሎች ልጆች ጎበዝ አይደለህም›› በሚሉበት ጊዜ ልጆች እንደተባሉት እንደሆኑ ያስባሉ፣ በዚያውም አስተሳሰብ ያድጋሉ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከወላጆቻቸው የሰሙአቸውን ነገሮች በድጋሚ ከመምህራንና ከሌሎች ሰዎችም ይሰማሉ፡፡ ይህ ሲሆን አባባሎቹ እነርሱን እንደሚገልጹ አድርገው ይቀበላሉ፡፡ የልጅነት ጊዜ ቢያልፍም፣ በልጅነት ስለራሳቸው የሰሙአቸው መጥፎ ነገሮች ከእነርሱ ጋር ዕድሜ ልክ ይቆያሉ፡፡

ይቀጥላል
@skbbepositivethinker
228 viewsSha z Maan, 17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ