Get Mystery Box with random crypto!

You can't be attached to a living thing like the running water | Art of motivation

You can't be attached to a living thing like the running waters of a river or the moving mind. A living thing is a moving and changing thing; how can you be attached to it? You may have a feeling for a living thing,but you cannot be attached to a river which
is a moving thing.

እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ

ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች።ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል።ጊዜው ሲደርስም ይጎላል

ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው

ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል ገላችን፣ አእምሮአችን ይታመማል እንረበሻለን፣ እንጨነቃለን።

ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው

ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል።ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ። መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው

የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ።ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ እንደሚለወጥ ስለማውቅ!

'የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ ' ሲሉ አዛውንት 'ዝናቡን ፍራው ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው።ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው። አይመስልህም እንዴ?''