Get Mystery Box with random crypto!

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ልቦች ኮምቦልቻን ያስባሉ።ፕሮግራሞች ይሻሻላሉ። | ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ልቦች ኮምቦልቻን ያስባሉ።ፕሮግራሞች ይሻሻላሉ።ጋራ ሸንተረሩን አልፈውን ወንዙን ሸለቆውን ተሻግረው እግሮች ወደ ኮምቦልቻ ያመራሉ።አዎ" ወደ ኮምቦልቻ። ያመራሉ።

~~~~ምን አለ ያላችሁ እንደሁ፦
እነሆ በውቢቷ ከተማ በኮምቦልቻ ምድር  በአይነታው ለይት ያለ የሆነ የኮርስ፣የሙሓደራ እና የተላይ የነሲሃ ፕሮግራሞች መዘጋጀቱን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።ከሀገር ውጪም ይሁን በሀገር ውስጥ ባሉ ዑለመኦች፣መሻይኾች እና ኡስታዞች ፣የተለያዩ ዱዓቶች የሚገኙነት ፕሮግራም ነው።ስለሆነም ወሰን ቀድመህ ፕሮግራምህን አመቻች።አለቀ።ኮርሱ ለተከታታይ 3ት ቀናት የሚሰጥ ስለሆነ ከርቅት የምትመጡ አካላቶች  ከተቻለ አንድ ቀን ቀደም ብላችሁ ብትገኙ በጣም መልካም ይሆናል።ማደሪያ እንዳታስቡ። ልብስ ግን ቀለል ያሉ ለየግላችሁ የሌት ልብሶችን ብትይዙ ደስ ይለናል።ለምግብ እናዳታስቡ ቤት ያፈራውን እንበላለን።
ዋና ፕሮግራሙ የሚጀመርበት ቀን በወርሃ ህዳር በእለት እሑድ ቀን (18/3/2015) ነው።በመሆኑም እናንተ ቀድማችሁ ቅዳሜ ከስኣት ለመግባት ሞክሩ ብለናል።

*በእለቱ ከሚገኙት ዑለማኦች መካከል መቀመጫቸውን በሀገረ ሳዑዲ ያደረጉ  ዑለሞች…

1, የተከበሩ ሸይኽ አቢ ዐማር ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዲላሂ ባሙሳ - فضيلة الشيخ محمد بن عبد الله با موسى - حفظه الله تعالى

2,የተከበሩ ሸይኽ ረሻድ አል-ሑበይሺይ - فضيلة الشيخ  رشاد الورد الحبيشي حفظه الله

3, የተከበሩት ሸይኽ ሙሳ አሕመድ አል ቀጧኒ
فضيلة الشيخ موسى بن أحمد القطاني العفري

*ከሀገረ ኢትዮጺያ ከተለያየ ቦታ የተውጣጡ  መሻይኾች እና ኡስታዞች፦

=>ከደሴ
~ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን
~ ሸይኽ ሙሐመድ ጘዛል
~ ሸይኽ ሃሰን ቃዲ
~ ሸይኽ ሙሀመድ አሚን
~ ኡስታዝ በድሩ
~ ሸይኽ አረቡ
~ ሸይኽ ኢሳ
~ ሸህ ሁሴን

=> ከኩታበር
~ ሸህ ሙጅተባ
~ ሸህ አደም ኩታበር

=>ከኮምቦልቻ
~ ሸይኽ አሕመድ አወቅ ከኮምቦልቻ

=>ከኬሚሴ
~ሸይኽ አቢ ዐማር አወል ቢን አሕመድ አል_ኬሚሴ
~ኡስታዝ አቡ ሓቲም ኸድር ቢን አሕመድ አል_ኬሚሴ

=> ከአፋር
~ ኡስታዝ አቡ ሒዛም

*ሌሎችም ከአዲስ አበባም የሚተሙ እንቁ ኡስታዞች አሉ ለግዜዉ ስማቸውን ይቆያችሁ


ማንቂያ 1፦ወደ ፕሮግራሙ ስትመጡ ማስታወሻ ደብተር እና እስኪርብቶ  ብትይዙ መልካም ነው።በተለይም ተማሪዎች።

ማንቂያ 2፦ማንኛቸውንም  ሹብሃ መሳይ ችግር ፈጣሪ ጥያቄዎችን መጠየቅ ስልምትችሉ ከወድሁ ጥያቄያችሁን ማዘጋጅት እንደምትችሉ ልንጠቁማችሁ እንወዳለን።

ማንቂያ 3፦ ከሩቅ የምትመጡ ወንድሞች ቅዳሜ እንድትገቡ እናሳስባለን በቅርብ ያላቹህ እሁድ በጧት እንድትገኙ እናሳዉቃለን።

ማሳሰቢያ፦በአሏህ ፍቃድ መሻይኾቹ ቅዳሜ ከሰዓት ኮቻ ይገባሉ ቅዳሜ ከመግሪብ እስከ ኢሻ የሙሐደራ ፕሮግራም ይኖረናል። የእሁዱን ፕሮግራም በዝርዝር እናሳውቃለን።

በመቅረታችሁ ብቻ ሳይሆን በማርፈዳችሁም ትቆጫላችሁ።
http://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
http://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea