Get Mystery Box with random crypto!

ባንዲራሽ ከፍ ይበል!! ክብርና ዝናሽ ለአለም ይነገር፡ የነብዩ ኢስማኢል የሙሀመድ ሀገር፡ ግርማና | ስኬትን የፈለገ የሰለፎችን መንገድ ይከተል

ባንዲራሽ ከፍ ይበል!!

ክብርና ዝናሽ ለአለም ይነገር፡
የነብዩ ኢስማኢል የሙሀመድ ሀገር፡
ግርማና ሞገስሽ የዑሁድ ተራራ፡
የነብዩ ወዳጅ ያ የጀነት ጎራ፡
የወህዩ መፍለቂያም ከአንች ጋር ነው ሒራ፡
ያለሽ ተአምራት አያልቅም ቢጠራ፡
በዝርዝር በወሳ ቢተረክ ቢወራ።
----------------------------------
ሶፋና መርዋ ደግሞም ሙዝደሊፋ፡
ሐጅ መተግበሪያው እንደት ነው አረፋ፡
በርቀት እያየሁ እያፈሰስኩ እንባ፡
ሀጀረል-አስወዱ ሆድን እያባባ፡
ቅዱሱ ቦታችን እንደምነው ከዕባ፡
-------------------------------------
ባንዲራሽ ከፍ ይበል!!

ለወደደሽ መልካም ለጠላሽ ሴራ አፍራሽ፡
የተዐምር ሀገር አምረሽ የተሰራሽ፡
ሁሌ ትርፋማ ሁኝ አይታይ ኪሳራሽ፡
በሔደሰሽበት ሁሉ ከፍ ይበል ባንድራሽ፡
የጠላሽ ይጠላ ሽንፈትን ይቀበል፡
ሁሌም በሔድሽበት ባንድራሽ ከፍ
ይበል፡
በኑረዲን አል አረቢ
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi