Get Mystery Box with random crypto!

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ ! ክፍል 10 ========================== አፏ ውስጥ የአ | የፍቅር አለም LOVES WORLD

ባሌ በ50 ብር ሸጠኝ !

ክፍል 10

==========================
አፏ ውስጥ የአፍ ጠረን ማጥፊያ ስፕሬይ ነፋችና በሩን ከፈተችው፡፡በሩ ላይ አንዲት አሮጊት ሴትዮ
ቆመዋል "አቢስ?!" አለቻቸው ፣ ለጥቂት ሰከንዶች ዝም አሏትና "ራሱን ሲስትብኝ ነው ወዳንቺ
የመጣሁት" ሲሏት እየከነፈች ወጣች። ሴትዮ ጭስ ባጨናበሰው አይናቸው እኔን ገርመም
አድርገው አይተውኝ ከቅንድባቸው እስከ አገጫቸው ባለው ሙሉ የፊታቸው አካል አሽሟጠጡና
ተከትለዋት ሄዱ።( ሴትዮዋ ሲያዩኝ ለምን አሽሟጠጡ? ) እኔ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ።
ተከትያት ልሂድ ወይስ ቤቱን ልጠብቅ? የተፈጠረውን ነገር ለማየት ልቤ ስለቋመጠ እግሬ ሳይታዘዝ
ከተቀመጠበት ብድግ ብሎ ከቤት ለመውጣት ተጣደፈ፡፡ በሩን መለስ አደረኩት።
ራሔል ከፊት ከፊት ፣ ሴትዮዋ ከኋላ ከኋላ ፣ እኔ ደግሞ ከሁለቱም ኋላ ሆኜ ከባልደራስ
ኮንዶሚኒየም በስተምሥራቅ በኩል ወደ ሚገኘው ሞቃዲሾ ወደ ሚባለው ሰፈር ሄድን። ከፍርዬ ሱቅ
ወደዚህ ያለ ቆርቆሮ ግቢ ውስጥ ዘለቅን።( ይቺ ፍርዬ ከድሮም ጀምሮ ሳውቃት እንዲሁ እብድ
እንደነበረች ነው። አሁንም ልጆች ወልዳም እዛ ሶስት ዕቃ ብቻ የተደረደረበት ሱቋ ውስጥ
እየለፈለፈች አለች። ድሮ ኮኮበፅብሐ ተማሪዎች እያለን በሷ ሱቅ ጋር ስናልፍ ጆተኒ ስለነበራት
ከቢትወደድ ተማሪዎች ጋር እጃችን እስኪጠቁር ድረስ ቁማር እንጫወት ነበር )
የቆርቆሮ ግቢዋ ውስጥ እንደገባን አንዲት ግድግዳዋም ፣ መሬቷም ፣ ኮርኒሷም ፣ ዕቃዎቹም
ከአፈር የተሰሩባት ቤት ውስጥ ወደ ውስጥ ዘለቅን። ቤት ውስጥ የምትበራው ቢጫዋ አምፖል
በጥላሸት ደብዝዛ ቤቱን ለማጨለም እንጂ ብርሀን ለመስጠት የተቀመጠች አትመስልም። ከበሩ
ትይዩ ባለው የጥጥ ፍራሽ የተነጠፈበት የሽቦ አልጋ ላይ የራሔል ልጅ የአፉ ለሀጭ አየር ላይ
ተንጠልጥሎ ራሱን ስቶ በፀጥታ ተጋድሟል።
ራሔል እቅፍ አድርጋ አነሳችው። "አቢ......አቢ.....ባባዬ....ባባ...." አቤት እንዴት
እንደምትንሰፈሰፍ ብታዩዋት! ያ ስንት ሜካፕ የለመደ ፊቷ በንፍጥና በዕንባ ጨቅይቶ ብታዩት
ሳትወዱ በግድ እንድታዝኑ ታደርጋችኋለች። ሁሏም ሴት ለካ እናት ስትሆን አንጀት ትበላለች። ፊቷ
ላይ ያለው የመረበሽ ፣ የመጨነቅ ፣ የመደናገጥ ስሜት ሴት በመሆን ብቻ የሚገኝ ሳይሆን እናት
ሲሆኑ ብቻ የሚሰጥ ልዩ ፀጋ ነው። ስለዚህ እናቱ የሄደችበትም እናቱ የሞተችበትም ህፃን እኩል
ያለቅሳሉ ብቻ ሳይሆን መባል ያለበት ልጇ የታመመባትም ፣ ልጇ የሞተባትም እናት እኩል
ይደነግጣሉ! የሚል አባባልም ሳያስፈልገን አይቀርም።
ወፍራሙ ልጇ ቀስ ብሎ ዓይኖቹን ገለጣቸው። የደስታ ዕንባ ከዓይኖቿ እየወረደ ሰፊ ፊቱን
እየደጋገመች ሳመችው። ልጇ ግን አሁንም ከአፉ ለሀጭ እንደተቀቀለ የተልባ ውሀ እየተምዝለገለገ
ይወጣል። እዚች አፈር ቤት ውስጥ በቆየንባቸው ወደ አንድ ሰዓት ገደማ አንዲትም ቃል
አልተነፈሰም። ወፍራምና ሰፊ ፊቱ ላይ ምንም አይነት ስሜት አይነበብበትም። ዓይኖቹ አንድ ቦታ ላይ
ብቻ ፍጥጥ ብለው ካዩ አይንቀሳቀሱም።
"ወንዴ ብር ይዘሀል እንዴ?" አለችኝ ራሔል.....ለካርድ መሙያ ብዬ የያዝኩትን ሀምሳ ብር
አውጥቼ ሰጠኋት። ለሴትዮዋ እየሰጠቻቸው
"ማዘርዬ ይሄ የትናንት ነው የዛሬውን ደግሞ ወደ ማታ መጥቼ እሰጥዎታለሁ" ሴትዮ በቀረባቸው
ሒሳብ በስጫ ብለው ነው መሰለኝ ፊታቸውን ከሰከሱት። ብሩን ለመስጠት ከተዘረጋው እጇ ላይ
መንጭቀው ወሰዱት።
"..አ...ይ .....እንዲያው ያንቺ ጣጣ ማብቂያ የለውም.....ለማንኛውም ምግቡም እያለቀ ነው
እሱንም በዛው ይዘሽ ነይ" አሏት። ራሔል ሴትዮዋን በእሺታ መልክ አይታቸው ፣ ልጇን ፊቷ ለሀጭ
በለሀጭ እስኪሆን ድረስ ስማው ከቤት ወጣን። ወደቤቷ እየሄድን መሬት የሚበሳ ዕንባዋን
ታዘንበው ጀመር። ላባብላት ስሞክር ስለባሰባት ዝም አልኳት።
ቤቷ እንደ ደረስን እየተጣደፈች ከቁም ሳጥኗ ውስጥ በሮል የተጠቀለለች አንዲት እስቲክ ጋንጃ
አወጣችና እየተክለፈለፈች መጦዝ ጀመረች። ጦዛ ስትጨርስ ቀስ በቀስ ተረጋጋች። እኔ ሙሉ
ስሜቷን ለመረዳት እሷ እስክታወራ ድረስ ዝም ብዬ ጠበኳት።
"ረበሽኩህ አይደል ወንዴ?"
"ምን አደረግሽኝና!"
"ሁሌም አቢን ካየሁት እንዲህ ነው የምሆነው ቅድም የተደነባበርኩት እሱን ይዛው የመጣች
መስሎኝ ነው። ወንዴ መቼም ብዙ ታሪኮቼን ዘክዝኬልህ ይሄንን ልዋሽህ አልፈልግም ፣ ሌላዋ
የታደለች እናት ልጇ ከአጠገቧ እንዲርቅ አትፈልግም። እኔ ግን ልጄ አጠገቤ ሆኖ ለአንዲት
ሰከንድም ሠላም ስለማላገኝ ይቺ ያየሀትን ሞግዚት ሴትዮ ጊዮርጊስ ሲለምኑ አግኝቻቸው ቤት
ተከራይቼላቸው ፣ ቀለብ እየቆረጥኩላቸው ፣ በቀን 50 50 ብር እየሰጠኋቸው ከሳቸው ጋር እንዲኖር
ነው ያደርኩት። ለሰው እንዲህ አደረኩ ተብሎ ባይወራም ከዛ ህይወት ያወጣኋቸው ሴትዮ የአንድ
ቀን ሒሳብ ሳሳስልፍባቸው ሊበሉኝ ነው የሚደርሱት። ቅድም የመጡት የአቢ ራሱን መሳት
አሳስቧቸው እንዳይመስልህ ፣ የትናንቱን ሒሳብ ስላልሰጠኋቸው እግረ መንገዳቸውን ሊቀበሉኝ ነው
የመጡት እንጂ የሱ ራሱን መሳትማ የለመዱት ነገር ነው።
እንዳየኸው የአእምሮ ህመምተኛ ነው። በሽታው ደግሞ የአእምሮ ብቻ እንዳይመስልህ አምስቱም
የስሜት ህዋሳቶቹ ምንም ነገር ሴንስ ማድረግ አይችሉም። ዓይኖቹ የሚያዩ ይመስላሉ ግን አያዩም
፣ ቆዳውን ብትቆነጥጠው ብትመታው ምንም አይሰማውም ፣ ጆሮው አይሰማም ፣ ምላሱ ምንም
ነገር አያጣጥምም አይናገርም ፣ አፍንጫው ምንም ዓይነት ሽታን መለየት አይችልም......ታዲያ
የእናትነት አንጀቴ አስችሎኝ እንዴት አብሬው ልቀመጥ? አንቺም እንደእናትሽ ያው ጨካኝ ነሽ ብሎ
ታሪኬን የሚያነቡ ሰዎች ሊፈርዱብኝ ይችላሉ። መቼም ያልተነካ ግልግል ያውቃል ፣ በሰው ላይ
መፍረድ በጣም ቀላል ነው። እኔ ግን ከሱ ጋር ስሆን ልቤ እንዴት እንደሚቆስል አምላክ ብቻ ነው::
ከኔ ሲለየኝም ሰላም ስለማላገኝ የማልጠቀመው የሱስ ዓይነት የለም ፣ ራሴን ለመርሳት ብዙ ነገር
ውስጥ ለመደበቅ እጥራለሁ። መፅመፍቶች ውስጥ እመሸጋለሁ ፣ ያንተ ድድ ማስጫ ላይ ተጥጄ
እውላለሁ ፣ ፌስቡክ ላይ ያሉ ፀሀፊዎችን እያሳደድኩ አነባለሁ። በዚህ የተነሳም ነው የማንበብ ሱስ
የያዘኝ።
"ህክምና ለምን አልሞከርሽለትም?"
"ወይ አንተ......ለሱ ስል ምን ያልሞከርኩት ነገር አለ ብለህ ነው? ዶክተሮቹ ብሬን ሊግጡኝ
ይድናል ሲሉኝ ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ስል ከከቤ ዲያስፖራዎች ጋር ሌዝቢያን ሸሌ ሆኜ ሰርቻለሁ::
ዶክተሮቹ ከበዙ ጊዜያት በኋላ ብሬ ማለቁን ስነግራቸው 'ሪች አትልፊ ልጅሽ የመዳን ተስፋ
የለውም' አሉኝ። ታዲያ ለምን መጀመሪያ አልነገራችሁኝም ብዬ ሆስፒታሉን አፍጋኒስታን አደረኩት ፣
ግን ሰሚ አላገኘሁም። አየህ ሀበሻ ይሄን ያህል መሰሪ ፍጡር ነው! እሱ ጥቅም እስካገኘ ድረስ
በነፍስህ ሳይቀር ቁማር ይጫወትብሀል!! እነዚህ ስግብግብ ዶክተሮች ልጄን ለገንዘብ ብለው
የሆነውንም ያልሆነውንም መርፌ እየወጉት የባሰ አጀዘቡብኝ። ያንን ጊዜ ሳስታውሰው የኢትዮጵያን
ህዝብ በሙሉ በጋዝ አርከፍክፌ እያነደድኩ በወላፈኑ ብሞቅ ደስ ይለኛል። ይሄንን ህዝብ
አልወደውም። ህይወቴን በሙሉ ነው የነጠቀኝ። ደግሞ እነዚህ ሰውን እየደለሉ ሀብታም የሆኑ
ከርሳም ዘፋኞች ሀበሻ ኩሩ ነው ደግና ሩሩሁ ሲሉ ይገርመኛል። ይሄ ህዝብ ደግ አይደለም! ደግ
ነውም ከተባለ የሚቀምሰው አጥቶ ደጃፉ ላይ ለሚያድር ምስኪኑ ወገኑ ሳይሆን ለማያውቀው
ሀብታምና ለውጭ ዜጋ ነው የሚያሽቃብጠው!!! ያኔ በጨቅላነቴ መንገድ ላይ ስለምን አዳሜ
ገንዘቡን በድራፍት ከሚጨርሰው ፣ ጮማ
ና ቁርጥ ከሚበ