Get Mystery Box with random crypto!

እየደረደርኩ ውስጤ ያቆጠቆጠውን ሚስት የመሆን ምኞቴን ለማጥፋት እሞክራለሁ። ብቻዬን ስሆን ያዳፈንኩ | የፍቅር አለም LOVES WORLD

እየደረደርኩ ውስጤ
ያቆጠቆጠውን ሚስት የመሆን ምኞቴን ለማጥፋት እሞክራለሁ። ብቻዬን ስሆን ያዳፈንኩት ምኞቴ
እሱን ሲያገኝ በፍቅሩ ነፋስ ተቀጣጥሎ "የመጣው ይምጣ ውበትሽ ተመጦ ታኝኮ ሳያልቅ: ጡቶችሽ
ሳይሟሽሹ: ዳሌሽ ቅርፅ አልባ ከመሆኑ በፊት:ወገብሽና ሆድሽ በቦርጭ ሳይሞላ: ዕድሜ ጠላትሽ
በጠረባ ዘርጥጦ ሳይጥልሽ: ቶሎ አግቢውና ለአንድ ቀንም ቢሆን የሚስትነትን ወጉን እይው"
ይለኛል። ሌላኛው ውስጤ በመወሰንና ባለመወሰን ውቅያኖስ ላይ ነፍሴ ማረፊያ አጥታ
ትዋልላለች።
በሌላ በኩል ደግሞ 'አሟልቶ አይሰጥም ጌታ ወይ አፈጣጠር' እንድትል ሀመልማል አባተ
ኤልያስንም አምላክ ልቦናውን ንፁህ አድርጎ ቢፈጥረውም ፣ እንደኛ ከጭቃ ነውና የተሰራው ትዳር
ውስጥ እንዳልገባ የሚያደርገኝ ደካማ ጎን ነበረው " ይህንን እያለችኝ እያለ የቤቷ በር ተንኳኳ።
ከተቀመጠችበት ፍራሽ ላይ ተደነባብራ ስትነሳ ሺሻው ላይ ያለውን የከሰል ፍም ደፋችው። ሁኔታዋ
ግራ አጋባኝ። በር ስለተንኳኳ ይሄን ያህል ለምንድነው የምትደነባበረው? የሺሻ ዕቃዋን ቁምሳጥኗ
ውስጥ ከትታ ደበቀችው። የደፋችውን መዋሰልና የከሰል ፍም ጠራርጋ አነሳችው። በድጋሚ በሩ
ተንኳኳ። ቤቱ ውስጥ ኤር ፍሬሽነር ነፋች።
"ምን ሆነሽ ነው?"
"እሱ ነው" አለችኝ ድምጿን ቀነስ አድርጋ
"እሱ ማን?" አልኳት ድርጊቷ እያወዛገበኝ አፏ ውስጥ የአፍ ጠረን ማጥፊያ ስፕሬይ ነፋችና በሩን
ከፈተችው፡፡

ይቀጥላል....

╔═══❖• •❖═══╗
@silefikrr
╚═══❖• •❖═══╝
4 any comment
@silefikirbot
❥❥________⚘_______❥❥