Get Mystery Box with random crypto!

የ4ኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሃ -ግብር ማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄደ። የትራንስፖርት ቢሮ እና የ | Sheger Mass Transport Service Enterprise

የ4ኛው ዙር አረንጓዴ አሻራ መርሃ -ግብር ማጠቃለያ ፕሮግራም ተካሄደ።

የትራንስፖርት ቢሮ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮች የአረንጓዴ አሻራ ማኖር መርሃ ግብር ላይ ተሳታፋ በመሆን አሻራቸውን አስቀመጡ።

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ "አሻራችን ለትውልዳችን" በሚል መሪ ቃል በአንድ ጀምበር 4 ሚሊዮን ችግኞች ተከላ መርሐ ግብር ነው፡፡

ችግኝ የመትከል መርሃ -ግብሩን በም/ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊዋ ወ/ሮ ነጂባ አክመል ፣የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ሃለፊ አቶ ምትኩ አስማረ ፣ የትራንስፖርት ቢሮ ተጠሪ ተቋማት አመራሮች በጉለሌ ክፍለ ከተማ ድል በር አካባቢ ተገኝተው መርሃ ግብሩን አከናውነዋል ፡፡

በ መርሃ-ግብሩ ላይም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ እና ሌሎች የከተማዋ አመራሮችም ተሳታፊ በመሆን ችግኝ ተክለዋል፡፡
#sheger_bus