Get Mystery Box with random crypto!

ሻሚል - shamil

የቴሌግራም ቻናል አርማ shamilunkamil — ሻሚል - shamil
የቴሌግራም ቻናል አርማ shamilunkamil — ሻሚል - shamil
የሰርጥ አድራሻ: @shamilunkamil
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 940
የሰርጥ መግለጫ

ወደ ፊት!
ልቅና እና ክብር ለአሏህ ፣ ለመልክተኛው እና ለሙእሚኖች ይሁን።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-09-21 15:43:10
መውሊድ በዑለማዎች መካከል ኺላፍ (ተቃርኖ) ያለበት ጉዳይ አይደለም።

መውሊድን ማክበር ይቻላል አለማክበርም ይቻላል ሲባል መውሊድን መቃወም ይቻላል ማለት አይደለም።

በዶክተር ሸይኽ አቡበክር ሱለይማን
አሏህ ይጠብቃቸው


:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil

https://t.me/shamilunkamil
498 viewsedited  12:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 15:13:54 መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ
(ክፍል 9)

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil
186 viewsedited  12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-21 15:13:40
መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ

(ክፍል 9)

መውሊድ መልካም ሱና ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያከበሩት ሙስሊሞች ናቸው እንጂ፤ አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት የነቢያችንን ሞት ያከብሩ ከነበሩ ሰዎች የተወሰደ አይደለም

ሓፊዞች፣ የታሪክ ባለቤት ዓሊሞችና ሌሎችም እንደጠቀሱት መውሊድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመሩት ሙዘፈር የተባሉ ኢርቢልን ያስተዳድሩ የነበሩ ንጉስ ናቸው። እሳቸውም አሏህን ፈሪ፣ ሷሊህ፣ ዓሊምና ጀግናም ነበሩ። መውሊድን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመሩት እሳቸው ናቸው። ከዚያም ዑለማዎች እና የፊቅህ ምሁራኖች በዚህ ስራቸው ተስማሙ። ከነሱም አልፎ በግዛታቸው ያልነበሩ  ዑለማዎች በዚህ ስራቸው ተስማሙ። ይህንንም አልሓፊዝ አስዩጢይ አልአዋኢል በተሰኘው መጽሐፋቸው ጠቅሰውታል። ሙስሊሞች አሁንም ድረስ ከስምንት መቶ አመት በፊት አንስቶ መውሊድን በማክበር ላይ ይገኛሉ።

ማንኛውም የነቢያችን ﷺ ኡመት ዓሊሞች መልካም ነው ብለው በጋራ የተስማሙበት ነገር መልካም ሲሆን፤ ማንኛውም የነቢያችን ﷺ ዓሊሞች መጥፎ ነው ብለው በጋራ የተስማሙበት ነገር መጥፎ ነው።

የነቢያችን ﷺ ኡመት ዓሊሞች ደግሞ በመጥፎ ነገር በመስማማት እንደማይሰባሰቡ የታወቀ ነገር ነው። ምክኒያቱም ነቢያችን ﷺ እነሱን በተመለከተ እንዲህ ብለዋልና፡

«إِنَّ أُمَتِي لَا تَجْتَمِعُ عَلَى ضَلَالَة» رَوَاهُ اِبْنُ مَاجَهْ فِي سُنَنِهِ.

ትርጉሙም፡ «ኡመቴ በጥመት ላይ ተስማምተው አይሰባሰቡም»። ኢብኑ ማጀህ በሱነናቸው ዘግበውታል።

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamilb
482 viewsedited  12:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 16:57:01 መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ
(ክፍል 8)


:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil
186 viewsedited  13:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-20 16:56:46
መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ

(ክፍል 8)


አልሓፊዝ አስዩጢይ <<ሑስኑል መቅሲድ ፊ ዓመሊል መውሊድ >> በተሰኘው መጽሐፍ መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ የሚያሳይ ከሐዲስ ያወጡት ማስረጃ (መሠረት)

ነቢያችን ﷺ እንዲህ ብለው ነበር፦
<<ذَاكَ يَوْمٌ وُلِدْتُ فِيهِ وَفِيهِ أُنْزِلَ عَلَيَّ>>
ትርጉሙም፡ «በዚያ ቀን ነው የተወለድኩት በዚያው ቀን ነው ወሕይም በእኔ ላይ የወረደው» ።

ይህንንም ያሉት ሰኞ ቀን ለምን ትፆማላቹህ ተብለዉ ሲጠየቁ ነበር። በዚህ ሐዲስ አሏህ ለባሮቹ የዋለላቸው ፀጋዎች የሚታዱሱበት (ትውስታቸው የሚደጋገሙበት) ቀናቶችን መፆም የሚወደድ ነገር መሆኑን እንመለከታለን ። አሏህ ለኛ ከዋለልን ታላላቅ ፀጋዎች ውስጥ ደግሞ ነቢያችንን ለኛ ማስገኘቱ እና በመልክተኝነት መላኩ ይገኙበታል። ለዚህም ማስረጃ ከቁርኣን የሚከተለው ነው፦
{لَقَدْ مَنَّ اللهُ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ إِذْ بَعَثَ فِيهِمْ رَسُولًا مِنْ أَ نْفُسِهِمْ} [ آل عمران : 164]

ትርጉሙም፡ «አሏህ  ለምእመናን ውለታ አድርጎላቸዋል፤ ይኸውም ከነሱ የሆነ መልክተኛን ልኮላቸዋልና»

አልሓፊዝ አስዩጢይ በመጽሐፋቸው እንዲህ ብለዋል፡« ኢማም የሆኑት አልሓፊዝ  አቡል ፈድል አህመድ ኢብኑ ሐጀር ለመውሊድ ማስረጃ (መሠረት) ከሐዲስ አውጥተውለታል፤ እኔ ደግሞ ሌላ ሁለተኛ ማስረጃ አወጣሁለት።»

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil
1.2K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 14:11:51
የሚያምሩ የመውሊድ ቲሸርቶች እና ሂጃቦች
እጅየ ያለውም የሌለውም
እንደ አቅምዎ በመካከለኛ ጥራት የተሰሩ ቲሸርቶችም አሉን።

ዋጋ 175 ብር
       200 ብር
       275 ብር
የሂጃቦችንም ዋጋ በቅርቡ የምናስቀምጥላቹህ ይሆናል።
ስልክ ቁጥር +251901885500
ያለው ውሰን ነው እና ቀድመው ይግዙ !

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil
1.5K views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 11:15:00 መውሊድን ማክበር እንደሚፈቀድ እና በማክበሩም ምንዳ እና አጅር እንዳለው የሚገልፅ ብያኔ
(ክፍል 7)

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil
237 viewsedited  08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-17 11:13:47 ከዚህ ሐዲስ የምንጠቀመው አንድ በተወሰነ ቀን አንድን ፀጋ በመለገስ ወይም ችግርን (በላእን) በማንሳት አሏህ ለዋለልን ውለታ አሏህን ማመስገን የሚቻል መሆኑን ነው። ይህንንም ድርጊት እሱን በመሰለ ቀን በየዓመቱ መደጋገም እንደሚቻል ነው። አሏህን  ማመስገን ደግሞ በተለያዩ ዒባዳዎች ማከናወን ይቻላል። ለምሳሌ በሱጁድ፣ በፆም፣ በሶደቃ፣ ቁርኣን በመቅራት አሏህን ማመስገን  ይቻላል። ታዲያ የትኛው ፀጋ ነው የነቢያችንን ﷺ መገኘት ከመሰለ ፀጋ የሚበልጠው!!!

:¨·.·¨: ❀
 `·. ሻሚል-shamil
https://t.me/shamilunkamil
496 viewsedited  08:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ