Get Mystery Box with random crypto!

ሴራ ታሪክ እና ምርምር

የቴሌግራም ቻናል አርማ sera_tarik_mirmir — ሴራ ታሪክ እና ምርምር
የቴሌግራም ቻናል አርማ sera_tarik_mirmir — ሴራ ታሪክ እና ምርምር
የሰርጥ አድራሻ: @sera_tarik_mirmir
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.46K
የሰርጥ መግለጫ

የጥንት ኢትዮጵያ መንፈሳዊና አለማዊ ስራወች፥ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና የአውሬውን መንፈስ በኢትዮጵያ ላይ ለማንፀባረቅ የሚሸረቡ ሴራወች እንዲሁም የኢትዮጵያና ሌሎች ታሪኮች አስተማሪና ጠቃሚ ምክሮችና መረጃወች ይቀርቡበታል
የዩቲዩብ ቻናላችንን subscribe አድርጉልን
https://youtube.com/channel/UCBtYnl_gnPkD_bpk3qwmRHA አስተያየት ለማድረስ

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-08-22 20:09:15 የቴሌግራም ቻናሉንም ተወዳጁት
https://t.me/sera_tarik_mirmir

አሮጌውን ዓመት አሳልፈን አዲሱን ዓመት ለመቀበል ጥቂት ሳምንታት ቀርተዋል::
መጪው አዲስ ዓመት ካለፈው አሮጌ ዓመት የተሻለ እንደማይሆን ብናውቅም ምኞት አይከለከልምና የተሻለ እንዲሆን እንመኛለን::
ባሮጌው ዓመት ካየናቸው ጥሩ ነገሮች ውስጥ አንዱ "እረኛየ" የተሰኘው ምርጥ ኢትዮጵያዊ ድራማ ነው::ይህም የዓመቱ ምርጥ የኪነጥበብ ስራ ተብሎ ሊመዘገብ የሚገባው ነው::
ሌላው የዓመቱ ምርጥ ቀልድ ሲሆን እሱም ከእረኛየ ድራማ ጋር በተያያዘ በጉምቱው ገጣሚ በበላይ በቀለ ወያ የተቀለደው ቀልድ ነው::ድራማው በእናና ሞት በመጠናቀቁ ምክንያት ብዙዎች በእናና ሞት አዝነውና አልቀሰው ነበርና በላይ በቀለ ወያ ሃዘንተኞቹን ለማጽናናት በፌስቡክ ገጹ እንዲህ ብሎ ለጠፈ::
“ማልቀሱ እናናን ምንም አይጠቅማትም ተጋግዘን ቤተሰቦቿን እንርዳ CBE 1000384530099” በማለት ለእናና ቤተሰቦች በሚል ጎ ፈንድ ሚ አይነት ጫወታ ተጫወተ አካውንት ቁጥርም አስቀመጠ::
ይህም የዓመቱ ምርጥ ቀልድ ተብሎ የተመዘገበ ነው::
ጫዋታው በዚህ አላበቃም ለእናና ቤተሰቦች ያዘኑ ሃዘንተኞች የእናናን ቤተሰቦች ለመርዳት ወደተቀመጠው አካውንት ያቅማቸውን ያህን ገንዘብ አስገቡ::እሱም እንዲህ ሲል ለጠፈ::
"ለማንኛቸውም በእናና ቤተሰቦች ስም ወደ አካውንቴ የገባውን 560 ብር ወደ ሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማሀበር አካውንት ገቢ አድርጊያለሁ ። የአዕምሮ ህሙማንን ማገዝ የምትፈልጉ የሰሊሆምን አካውንት እንካችሁ 1000275107518" በማለት ለጥፎ ቀልዱንም ቁምነገሩንም አዋዝቶ ፈታ አደረገን::
****
አገር እንደ ቆዳ ተወጥራ ህዝቡ በፖለቲከኞች የሴራ ሰንሰለት ታስሮ በሃዘን በሚማቅቅበት ወቅት ከችግሩ ገለል ብለን ነገሮችን ለአፍታ ረስተን ፈታ እንል ዘንድ የሚያደርጉትን እንዲህ ያሉትን ዜጎች ማግኘት መልካም ነገር ነውና እነዚህን የመሰሉ ዜጎች ሊመሰገኑ ሊበረታቱ ይገባል እንላለን::
ይህን ብለን ወደራሳችን የሰብስክራይብ አርጉን ማስታወቂያችን እናልፋለን::
በሉ የዩቲዩብ ቻናሉን ሰብስክራይብ አድርጉ

https://youtube.com/channel/UCBtYnl_gnPkD_bpk3qwmRHA
617 viewsማኢጎ ጉቤ, edited  17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ