Get Mystery Box with random crypto!

'ባጭር ቀረን' ስንል - እድሜ ላበደሩን ቀርፀው ላሳመሩን ለኩሰው ላበሩን ቺርስ!! ።።።። ፊታችን | ነገረ መፃህፍት 📚📗📓📖

"ባጭር ቀረን" ስንል - እድሜ ላበደሩን
ቀርፀው ላሳመሩን
ለኩሰው ላበሩን
ቺርስ!!
።።።።
ፊታችንን ዐይተው
እንደተቸገርን - ካይናችን ላወቁ
ስለማርያም ብለን
እስክንለምናቸው - ቆመው ላልጠበቁ
ቺርስ!!!
።።።።
ወድቀው ለማይጥሉ -ነግሰው ለሚያነግሱ
ነውራችንን ዐይተው
ልክ እንደ ድመት ኩስ ፣ ለሚያለባብሱ
ብድር አበድረው ፣ ፈጥነው ለሚረሱ
ቺርስ!!!!
።።።።።።
ላባ ላረጉልን ፣ የመከራ ሸክሙን
ቀልደው ላሳቁን ፣ ተጫውተው ላከሙን
በቸከ ዘመን ላይ...
ስጋ ለበስ ትንግርት -ሆነው ላስደመሙን
ቺርስ!!!!!
።።።።።።።።።።።
( Bewketu Seyoum )