Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር ዜና #ነፃ_ጥቅል_ከኢትዮ_ቴሌኮም ! ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብ | ሩሀማ_ዘ_ዑራኤል ቻናል

ሰበር ዜና
#ነፃ_ጥቅል_ከኢትዮ_ቴሌኮም !

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት አመት 61.3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።

ይህም የእቅዱን 87.6 በመቶ ነው ብሏል።

ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።

በዚህም፦

1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል።

(ማስታወሻ ፦ ዓለም አቀፍ የጥሪ ስጦታው የተበረከተው ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል፣ የጹሑፍና የኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ነው)

ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።