Get Mystery Box with random crypto!

በግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ። ግንቦት 29-2014 የራያ ቆቦ ኮምዩ | Raya kobo communication

በግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ።

ግንቦት 29-2014 የራያ ቆቦ ኮምዩኒኬሽን (ራቆኮ)

በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ ልዩ ስሙ 02 ቀበሌ ጢሳ አባሊማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በግለሰብ ቤት ተሸሽጎ የነበረ 23 የሞርተር ተተኳሽ ተያዘ።

ከኀብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት በተደረገ ፍተሻ በአንድ ግለሰብ ቤት በመፀዳጃ ቤት ውስጥ 23 የሞርተር ተተኳሽ (ቅንቡላ) ተከዝኖ መገኘቱን የአምባሰል ወረዳ ሚሊሻ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

ተተኳሹ የተገኘበት ግለሰብም በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተጠቁሟል። መረጃው የዞኑ ኮምዩኒኬሽን ነው።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ