Get Mystery Box with random crypto!

ራፋቶኤል ምዕላድ - Rafatoel Initiative

የቴሌግራም ቻናል አርማ rafatoelinitiative — ራፋቶኤል ምዕላድ - Rafatoel Initiative
የቴሌግራም ቻናል አርማ rafatoelinitiative — ራፋቶኤል ምዕላድ - Rafatoel Initiative
የሰርጥ አድራሻ: @rafatoelinitiative
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.48K
የሰርጥ መግለጫ

ጥንታዊ ታሪክ።
ኢትኤል :ለኢትዮጵያ ትንሳኤ

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-01-02 18:32:46

4.0K viewsRafatoel Worku, 15:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-08-09 17:56:27
ዘመኑን የሚዋጅ #ምእራፍ ይዘን እየመጣን ነው። የትኛውንም ዓለምአቀፍዊ ተፅእኖ ተቋቁመን ኢትዮጵያዊ ራዕይን እውን ማድረግ የምንችለው ኢትዮጵያዊ ንቃተ ህሊናን በማጎልበት ነው። ለዛ ደግሞ እንዲረዳን ጥንታዊ እና አገራዊ የሆኑ ታሪኮችን ፣ ፍልስፍናዎችን ፣ እውቀቶችን ፣ ጥበቦችን ፣ ተረቶችን ፣ ትርክቶችን እና የህይወት ዘይቤዎችን ይዘንላችሁ እየመጣን ነው። #ጠብቁን #ኢትኤል #ምእራፍሁለት #አርትስቴሌቭዥን. #ራፋቶኤልምዕላድ
5.2K viewsRafatoel Worku, 14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-27 04:24:56 የ "Quantum jumping" ፅንሰ-ሀሳብ አንድምታን የተመለከቱ የተለያዩ ፕሮግራሞችን አቅርቤላችሁ ነበር። ብዙዎች በህይወታችሁ ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ እንዳያችሁበት አካፍላችሁኛል። ይህ በጣም ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው። ዛሬ ይህን ፅንሰ ሀሳብ ድጋሜ ያመጣሁት አጭር መልእክት ላጋራችሁ ስለፈለኩኝ ነው። ምን አልባት ከዛ አስቀድሞ ሀሳቡ አዲስ ለሚሆንባችሁ ወዳጆቼ : በእለት ተእለት የህይወት ውጣ ወረድ ውስጥ የማንፈልገው የማንመኘው የኑሮ እና የአእምሮ ሁኔታ ውስጥ እንዘፈቃለን። ጎበዝ ተማሪ ሆነን መገኘት ፈልገን ሰንፈን እራሳችንን እናገኘዋለን። በስራ ገበታችን ውጤታማ መሆን ፈልገን ውጤት ሊርቀን ይችላል። ጥሩ የፍቅር ህይወት እየተመኘን ያልሆነ የሚጎዳን የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ራሳችንን ልናገኘው እንችላለን። ደስታ ፈልገን ሀዘን ፤ ሰላም ፈልገን ጭንቀት ውስጥ ልንዳክር እንችላለን። ታድያ የሁላችንም ጥያቄ እንዴት ነው ከነኝህ ከማፈልጋቸው አሉታዊ የህይወት እና የአእምሮ ሁኔታዎች ወደ አዎንታዊው መሄድ የምንችለው የሚለው ጥያቄ ነው። እንግዲህ "Quantum jumping" የሚመጣው እዚህ ጋር ነው። "Quantum jumping" ከህክምና መንገዶች እንደ አንዱ ተደርጎ ተወስዶ አገልግሎት እየተሰጠበት ሲሆን የአእምሯችንን ሀይል በመሰብሰብ በምንፈልገው ሀይል የማንፈልገውን አሉታዊ ሀይል የምንተካበት እና ህቡዕ አእምሯችንን አዎንታዊ ሀይል የምናለማምድበት ዘርፍ ነው { ከዚህ ጋር ተያይዞ ተጨማሪ ሀሳብ ከፈለጋችሁ የሰራኋቸውን ቪዲዮዎች የዩቱብ ገፄ ላይ ማድመጥ ትችላላችሁ}




የአእምሮ ሀይላችንን አዎንታዊ በማድረግ እና ትኩረት በማድረግ የምንፈልገውን ነገር ወደእኛ ማቅረብ እንችላለን። በዚህ ረገድ በርካታ አገር በቀል የሆኑ ጥበቦች ፣ ፍልስፍና ዎች እና ልምዶች አሉ። እነኝህን በማህበረሰባችን ዘንድ የቆዩ የአእምሮ ልምምዶችን በማወቅና በመተግበር ለግል ህይወታችን ፣ ለቤተሰባችን እና ለአጋራችን የምንፈልገውን ሀይል ማቅረብ እንችላለን። { መንገዶቹን ለማወቅ }

በቴክኖሎጂ ምሳሌ ለማስረዳት የጉግል / የዩቲዩብ ስልተ-ቀመርን እናንሳ። ዩቱብ ላይ ስትገቡ በፊት ለፊት ገፁ የሚያቀርብላችሁ የእናንተን ፍላጎት ነው። የዩቱብ algorithm ከዚህ በፊት የፈለጋችሁትን ይዘት መዝግቦ ይህ ሰው የሚፈልገው እንዲህ አይነት ይዘቶችን ነው ብሎ ተረድቶ መዝግቦ የበለጠ ይህንን ይዘት ለእርስዎ ያደርሳል ፡፡ ተፈጥሮም የራሷ የሆነ algorithm አላት። በአእምሯችን አማካይነት ደጋግመን ህቡዕ አእምሯችን ላይ የምናስቀምጥላትን ይዘት ነው መልሳ መላልሳ የምትሰጠን።

ስለአገር ስናስብ እንደ ማህበረሰብ እሳቤያችን መፍረስ ፣ መበተን ፣ ግጭት ፣ እልቂት ከሆነ የተፈጥሮ algorithm መልሶ ለዚህ ማህበረሰብ የሚሰጠው እልቂትና ግጭት ነው። ማህበረሰባዊ ንቃተ ህሊናችን በአዎንታዊ ሀይል ካልተቃኘ እየሳብን የምናመጣው ሀይል አሉታዊ እየሆነ መሄዱ አይቀሬ ነው። የምናስበውን ነው የምንሆነው። የምናስበውን የተፈጥሮ algorithm ተረድቶ መልሶ መላልሶ የሚሰጠን። ስለዚህ እንደ ማህበረሰብ ትኩረታችን የሚጠቅሙን አዎንታዊ ሀይሎች ላይ ይሁን እላለሁ።

እንዴት ለሚለው ጥያቄ የሚከተሉትን ፕሮግራሞች ያድምጡ :

"Emotional intelligence" - የስሜት ብስለት አስፈላጊነት ከዶክተር አበበ ሐረገወይን ጋር



የሀሳብ የበላይነት ከዶክተር ሰለሞን ጋር

4.7K viewsRafatoel Worku, 01:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ