Get Mystery Box with random crypto!

የትግራይ መንግስት ጊዝያዊ ግጭት ለማቆም ወሰነ፡፡ ---- የትግራይ ህዝብና #መንግስት ለሰላም ያ | መንፈሳዊነት እንማርበት የተዋህዶ ፍሬዎች እንሁን

የትግራይ መንግስት ጊዝያዊ ግጭት ለማቆም ወሰነ፡፡
----
የትግራይ ህዝብና #መንግስት ለሰላም ያለው አቋም ከጅምሩ ግልፅ ነው፡፡ ፖለቲካዊ ችግሮች በሰላም እንዲፈቱ ከመጀመሪያው ጊዜ አንስቶ በማያወላዳ መንገድ ለወዳጅና ጠላት ግልፅ ሲያደርግ መጥቷል ምክንያቱም ሰላም የህልውና ጉዳይ አድርገው ያምንበታል ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ እንዲሆንም በየጊዜው ሁሉም ዓይነት ጥረቶች አድርገዋል፡፡

በአጭሩ የትግራይ ህዝብና #መንግስት ካጋጠመው ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ እንዲፈታ ሁል ጊዜ ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን ባለፉት 4 ዓመታት ለሁሉም ባለድርሻ አካላት በተደጋጋሚ ሲገልፅ ቆይተዋል፡፡

ከ17 ወራት በፊት ሳንወድ ተገድደን ህልውናችን ለማረጋገጥ ወደ #ጦርነት የገባንበት ጉዳይ ሁሉም የሰላም አማራጮች በመዝጋት ለትግራይ ህዝብ ከምድረ ገፅ ለማጥፋት የተከፈተው ግልፅ #ወታደራዊ ወረራና የሀይል እርምጃ ስለተወሰደ ነው፡፡

በአጠቃላይ ትላንትም ሆነ ዛሬ የመጀመሪያ አማራጫችን ሰላም እንጂ ጦርነት አልነበረም ዛሬም ኣይደለም፡፡ ስለዚህ በአሁኑ ጊዜ በጦርነት ምክንያት ችግር ላይ የወደቀው ህዝባችን ለመርዳት በዓለም ማህበረሰብ የተላከ ድጋፍ ያለምንም ማደናቀፍ ሊደርሰው ሲገባ በከበበና ክልከላ እስከአሁን የገባ እርደታ የለም፡፡

አሁን ግን ሰብአዊ እርደታ በሚያስፈልግ ዓይነት መጠንና ጊዜ ለህዝባችን እንዲዳረስ የሚያስችል ሁኔታ ከተመቻቸ ከዛሬ ጀምሮ ጊዝያዊ ግጭት ለማቆም የትግራይ መንግስት ወስነዋል፡፡

ለተግባራዊነቱም አስፈላጊ የሆነውን ሁሉ እንደሚያደርግ የትግራይ መንግስትና ህዝብ ለዓለም #ማህበረሰብ በአክብሮት ይገልፃል፡፡
ትግራይ ትስዕር
የትግራይ መንግስት
መጋቢት 15/2014ዓም መቐለ