Get Mystery Box with random crypto!

#ተጅዊድ_ክፍል | ቁርአን ብቻ

#ተጅዊድ_ክፍል
#ተጅዊድ_ማለት_ምን_ማለት_ነው:-
«ተጅዊድ» የሚለውን ቃል እንደ ቋንቋና እንደ የቁርአን አነባበብ ትምህርት መጠሪያነቱ ትርጓሜውን እንደሚከተለው

በሁለት ከፍለን ልንመለከተው እንችላለን። ይኸውም:-

#አንደኛ:- «ተጅዊድ» የተሰኘው ቃል ቋንቋዊ ወይም ቀጥተኛ ትርጓሜ:- «ተጅዊድ» የአረበኛ ቃል ሲሆን ቋንቋዊ ትርጉሙ «ማሳመር ወይም ማስዋብ» ነው ።

#ሁለተኛው:- ተጅዊድ የተሰኘው ቃል አገባባዊ ወይንም ከቁርአን ንባብ ዘይቤ አንፃር ትምህርትነቱ የሚሰጠው ትርጓሜ «ሁሉንም የአረበኛ ፊደላት ከትክክለኛው መፈጠሪያቸው በትክክል በማውጣትና እንደየ ባህሪያቸው ሁኔታ በማንበብ የሚገባቸውንና ትክክለኛ የሆነውን ድምፃቸውን ይዘው እንዲፈጠሩ ማድረግ ማለት ነው።»
.




ለዚህም ማስረጃችን የሚከተለው የኣላህ (ሱ,ወ) ቃል ነው፣
ﻭﺭﺗﻞ ﺍﻟﻘﺮﺍﻥ ﺗﺮﺗﻴﻼ 4
ﺍﻟﻤﺰﻣﻞ 4
«ቁርአንን በዝግታ ማንበብን አንብብ» [አል ሙዝዘሚል 4 ]