Get Mystery Box with random crypto!

የእንባ ጸሎት (Prayer of Tears) በጌታ ፊት ተግተው የሚማልዱ ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለ ሌ | ቅኔ እና ዜማ / QINE ENA ZEMA official

የእንባ ጸሎት
(Prayer of Tears)

በጌታ ፊት ተግተው የሚማልዱ ስለ ራሳቸውም ሆነ ስለ ሌሎች የሚያነቡ ሰዎች ያስቀኑኛል። ታድለው እላለሁ! እውነተኛ እንባ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ እንዳለው በጥቂቱም ቢሆን ይገባኛልና!

Gregory of Nassa “እንባ በነፍስ ላይ ላለ ቁስል እንደ ደም ነጠብጣብ ነው።" ብለዋል። አባ አንቶኒ የሚባሉ ቄስ ደግሞ “whoever wishes to advance in building up virtue will do so thru weeping and tears.” ብለዋል!

እንባ የእኛና የዓለሙ ሕዝብ በደል በመንፈሳችን በጥልቀት ሲታወቀን የምንሰጠው መንፈሳዊ ምላሽ ነው። መዝሙረኛው "በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ።" (መዝ.126፥5) ያለውም የእንባን ዋጋ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ነው!

Baslea Schlink የሚባሉ ጸሐፊ ስለ እንባ ጸሎት እንዲህ ብለዋል:- "The first characteristic of the kingdom of heaven is the overflowing joy that comes from contrition and repentance….Tears of contrition softens even the hardest hearts."!

እግዚአብሔር ልቡ የተሰበረውን ትሑት አይንቅም (መዝ.51:17)። እንባ ደግሞ ያንን የማሳያ አንዱ መንገድ ነው። በዚህ ረገድ ሪቻርድ ፎስተር እንዲህ መክረዋል:-

➣“When you cannot weep outwardly, shed tears before God in your intention. Have a weeping heart. Keep your soul in tears. Even if the eyes are dry , the mind and the spirit can be broken before God.”

➣"The fire of sin is intense but it is put out by a small amount of tears for the tears put out a furnace of faults, and cleans out wounds of sin."

(Richard Foster, Prayer, 37-46)

☞"አምላክ ሆይ፥ ሕይወቴን ነገርሁህ፤ እንባዬን እንደ ትእዛዝህ በፊትህ አኖርህ።" (መዝ.56፥8)

☞"እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና።" (ሉቃ.6፥21)

☞"እናንተ ታለቅሳለችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።" (ዮሐ.16፥20)

እግዚአብሔር ሆይ እባክህ
ልባችንን በጸጋህ አለስልስልን!
___
Dr. Bekele birhanu
@nazrawi_tube