በቤት ውስጥ በመጠበቅ የዶሮ አረባብ ዘዴ በቤት ውስጥ በመጠበቅ የዶሮ አረባብ ዘዴ ስንል ዶሮ አረቢዎች ለሚያረቧቸው ዶሮች እንደብዛታቸው መጠን በቂ የሆነ ቤት ሰርቶ ማርባት ማለት ነው ፡፡ አቅም ካለ ከእርባታው ቤት ጋር የተያያዘ ለመናፈሻቸው የሚሆን ቦታ በሽቦ ወይም በቀርከሀና በሸንበቆ አጥር ሰርቶ እንዲናፈሱና እንዲንቀሳቀሱ በማድረግ ዶሮችን ለማርባት የመቻል ዘዴ ማለት ነው ፡፡ በቤት ውስጥ በመጠበቅ ዶሮችን ለማርባት የሚደረግ ጥረት ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ ነው ፡፡ በዚህ ዘዴ በርካታ ዶሮችን በጥቂት ቦታ ላይ በማርባት ዶሮና እንቁላል ለገበያ ለማቅረብና ከፍተኛ ገቢ ለማግኘት ይችላል፡ ለዚህ ነው በቤት ውስጥ በመጠበቅ ዶሮችን ማርባት ጥቅሙ ከፍተኛ ነው የሚባለው ፡፡ አንድ ሰው ቤት ስርቶ ዶሮች ከቤት ሳይወጡ ለማርባት የሚችለው አንድ ካሬ ሜትር ቦታ በ6-8 ዶሮች እንዲይዝ በማድረግ ነው፡ አንድ ሰው በመኖሪያ ግቢው ባዶ ቦታ ላይ ዶሮ ለማርባት ከፈለገ ካሬ ሜትሩን በመለካት ስድስት ወይም በስምንት ዶሮች ቢያባዛው ምን ያህል ዶሮች ለማርባት አንደሚችል ለማወቅ ይችላል 580 views🅑🅛🅐🅒🅚 🄱🄾🅈, 21:29